የአዲስ አበባዋ “150 ዓመት” አሰልቺ ትርክቷ
ወንድሙ መኰንን UK 09 Novembere 2024
መግቢያ
ይኸንን ጉዳይ አንድ ጓደኛዬ አማክሮኝ እኔም ከንክኖኝ ከዓመት በፊት ነበር ለመጻፍ የጀመርኩት። ኦሮሞ ጓደኞች ይቀየሙኛል ብዬ በይሉኝታ ታሥሬ እስከዛሬ ተውኩት። ይሉኝታ አይደል የሚግለን? ዳሩ ግን፣ ውሸት በውሸት ላይ ተቆልላ አብጣ ዕውነት ልትሆን ምንም አለቀራት። በዚያም ብታቆም ባልከፋም። ሌላ አደጋ ይዛ ብቅ አለች። በብልጽግና ሥር የተሰገሰጉት የኦሮሙማ ፍልስፍና አቀንቃኞች፣ ጭርሶ አማራን ለማጥፋት በግልጽ አውጀው ተነሱ። በየቀኑ እየባሰባቸው ሲሂድ፣ በቃኝ። የፈሩት ይደርሳል፣ የናቁት ይወርሳል ይባል የለ? ከአዲስ አበባ፣ ኦሮሞ ያልሆነውን ጠራርገው ሊያስወጡን ያላንዳች ሀፍረት አውጀው እየተገበሩት ነው። ጅምላ ጭፍጨፋ በወለጋ ከጀመሩ ሰነባበቱ (BBC, በቄለም ወለጋ ሌላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ, 2022)። “ወላሂ፣ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” እያለች የታረደች ሕጻን አኢሻ ሠይድ ምንጊዜም ከልባችን አትጠፋም። 1600 አማሮች በቄለም ወለጋ በአንድ ጀምበር ተረፍርፈዋል። ይኸን ግድያ የፈጸሙት፣ “ሸኔ ነበር” ይበሉን እንጂ የብልጽግና የአካባቢው ባለሥልጣናት በጭፍጨፋው ላይ መተባበራቸውን የሚግልጹ መረጃዎች ሞልተውናል። የዘር ማጽዳት (ethnic cleaning) ዘመቻ ነበር ያካኼዱባቸው። በየጊዜው፣ ምክኒያት እየፈጠሩ፣ አማራውን በያለበት ጨፈጨፉት። 18 የአማራ ሴት ተማሪዎችን ጠልፈው ደብዛቸውን አጠፉ። ዝም አልናቸው። በትርክት ላይ ተመሥርተው፣ መጀመሪያ ሸገር የምትባል ነገር ቀርፈው አወጡና፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የእሳት ገጠገጡ። የኦሮሞ ያልሆኑ የመኖሪያ ቤቶችን ሲያፈርሱ መስኪድም አልቀራቸው። ዛሬ፣ አዲስ አበባ፣ ልክ እንደኮንስታንቲኖፕል፣ በሸገር የተከበበች ከተማ ናት። መውጣት ይቻላል። ኦሮሞ ያልሆነ ተመልሶ መግባት አይችልም። የእሳት አጥር ናት። ብሶባቸው፣ ዓባይን ተሻግረው፣ የአማራ ክልል የተባለውን በእግረኛ መድፈና፣ በሰማይ፣ በድሮንና በጄት ገበሬ፣ ሴት፣ ሕጻን ሳይሉ እየጨፈጨፉት ነው። ዝምታችን እስከመቼ ይቀጥል?
የሸገር አስተዳደር ሹመኝች ግን፣ አዲስ አበባ ላይ ጉብ ብልው ነው የሚያስተዳድሯት። ነባሩን አሻራ አጥፍተው፣ አዲስ “ፊንፊኔን” ለማዋለድ፣ የኦሮሞ የልሆነውን ቤት እያፈራረሱት ነው። ምነው፣ የኦሮሞውን ቤት ዘለላችሁትሳ ሲባሉ፣ “የኢንዲጂኒየስ” ቤት አናፈርስም አሉን። አታምኑኝም? ይኸን ጉዳችሁን ስሙት!