Articles

ካድሬነት በምክክር እና በእርቅ ስም ተጠርዞ ሲቀርብ

Dr. Mengistu Musie

ዶ/ር መንግስቱ ሙሴ

ከልምድ የተወሰደ

የደቡብ አፍሪካ እውነትን የማውጣት እና የእርቅ ኮሚሽን የተቋቋመው በአፓርታይድ አስተዳደር ነበር? አላማውስ ምን ነበር? Truth and Reconsilation Commission

የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ በጨካኝ እና ዘረኛው የአፓርታይድ አስተዳደር ስር ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ እና አፓርታይድ ስርአት መቀጠል ባለመቻሉ እና የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ በደሙ አቸንፎ ታጋይ መሪ ድርጅቱን ወደስልጣን ሲመጣ እና ሐገሪቱን እና ሕዝቧን በአንድነት እና ነጻነት ወደ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማሸጋገር የሚያስችል አንድ መንገድ በሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን የገዥነት ተገዥነት፤ የአሳዳጅ ተሳዳጅ፤ የጨቋኝ ተጨቋኝ አስተሳሰብን አፍርሶ ወደ አንድ ዴሞክራሲያዊ ሕዝባዊ አስተዳደር ለመውሰድ የአፓርታይድ ስርአት የፈጠረውን ቆሻሻ ሁሉ አክሞ በዳዮችን በፍትህ ፊት አቅርቦ በዳዮችን ተመጣጣኝ ፍርድ ሰጥቶ ይቅር የሚባለውን በይርታ አስታርቆ አዲስ ስርአት ማዋለድ ነው!!

በኛ ሐገርስ እየሆነ ያለው ምንድን ነው? ገዳይ ከሟች ጋር እንዴት ነው የሚታረቅ? ኮሚሽኑን ማን ፈጠረው? በነገራችን ላይ ገዳዩም ሆነ ሟቹ ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ይህ ኮሚሽን ለምን ወደሰሜን አሜሪካ መጣ፡፡ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው የገዳዩ ዘመቻ አሁንም በስፋት እና በትጋት እየቀጠለ ያለበት ሁኔታ እንደሆነ በሰሞኑ “ዘመቻ ማዕበል” የሚለው የፋሽስቱ ወራሪ ስራ አንዱ አሳይ ነው፡፡ ታዲያ ይህን የዘረኛው ፋሽስት ቡድን ቀጣይ ጦርነት ማስቆም ነው ወይንስ ዲያስፖራ ለምን ተቃወመን ለሚል የፖለቲካ ምላሽ ለመስጠት እድሜ ጠገብ ስም ያንጠለጠሉ ዘመናዊ ካድሬወች አመጣጥ?

አገራዊ እርቅ እና ምክክር ካስፈለገ ፍትህን እንደአላማ በሰነድ ተይዞ ነው፡፡ ጦር ሰባቂውን ዘረኛ ቡድን አቁም አይሆንም በሚል ድፍረት የተሞላበት ሰላማዊ ተቃውሞን አንግቦ እና አለማቀፍ እና አገር ወለድ የሰላም ሓይሎችን ከጎን አድርጎ ነው፡፡ እርቅ እና ምክክር በገዳዩ እየተመራ ግን ሰላምን ሊያዋልድ ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ በጎን ጦር ሰብቆ ድሮኖቹን እያዘመተ ንጹሐንን እየገደለ አሁንም በአራቱም ማ’እዘን የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ እና በተለይ ልክ እንደአፓርታይድ ስርአት ዘር ተኮር ግድያን እና ጦርነትን እያካሄደ ይኸው ገዳይ ቡድን በስልጣን ተቀምጦ የሚያዝዝባቸው ግለሰቦች እና የሚያዝዝበት ስብስብ ምክክር እና እርቅ ቢል ሰሚ ሊኖረው አይችልም፡፡

በተመሳሳይ ልክ እንደ ጸረ አፓርታይዱ የደቡብ አፍሪካ የእውነት አፈላላጊ እና የእርቅ ኮሚሽን እንዲሆን ከታሰበ በሕዝብ የተተፋው ገዳይ እና ዘረኛ ቡድን በአሸጋጋሪ መንግስት መቀየር ማለትም ለአገር ከጦርነት አዙሪት መውጣት እና ፍትህ በስራ ተተርጉሞ ገዳዮች በፍትህ ፊት የሚቆሙበት አሰራር እስካልተፈጠረ ልክ ሂትለር ስድስት ሚሊዮን ይሁዳውያንን እየገደለ ሰላም ይስፈን የሚል የውሸት መዝሙር መዘመር ያህል ነው፡፡

ሌላው የዘረኞች እና ወንጀለኞችም ቡድን በዚህ በውጭ ለዘር ልዩነት መጦዝ እና ተካሮ አንድን ዘር እንዲወገድ እሳቱን በማቀጣጠል ልክ እንደአብይ አህመድ የሰሩ ግለሰቦችም የጫሩትን የዘር ፍጅት ተሳስተን ነበር ሳይሉ ለሌላ አዲስ እና ቀጣይ ስርአት በተቃውሞ ስም መዘጋጀትም ሌላው አስጠያቂ እና ሌላ ልክ እንደዚህ የምክክር ኮሚሽን በፍትህ ላይ ማፌዝ መሆኑን ግራቀኙ ሊረዱት ሊያውቁት ይገባል፡፡  ሁሉም ዘረኞች ቋንቋህን ላልተናገረ ገበያም ንፈገው ያሉትም ሆነ በወለጋ በሽሆች በፈጠራቸው እያስገደለ ዛፍ የምተክለው ለሚሞቱት ጥላ እንዲሆን ነው ካለው አብይ አህመድ የተለዩ አለመሆናቸውን አውቀው እና ተጸጽተው እራስን መውቀስ ለመጭው እርቀሰላም ይጠቅማቸዋል አለዚያ እንደ አብይ አህመድ ካድሬ ልኮ የምክክር ኮሚሽን ብሎ እንደማሾፍ ይቆጠራል!!

ባጭሩ የምክክር ኮሚሽን ተብየው ዛሬ በዲሲ ኤምባሲ ያደረገው ስብሰባም አንዱ ማሳያ የዘረኛው እና የአፓርታይዱ ገዳይ የሆነው ቡድን ስራ ፈጻሚወች እንጅ ለሕዝብ አፍ እና ጆሮ ሊሆን የተመሰረተ ስብስብ እንዳይደለ በተዘጋጀለት የመንግስት የውጭ ቢሮ ስብሰባ ከመጥራት ጀምሮ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አሳይቶናል፡፡ በሚቀጥለው የቶሮንቶም ስብሰባ ቢሆን ተመሳሳይ ድራማ ሊያሳዩ መወሰናቸው የተላኩበትን ቢችሉ ለመከፋፈል ካልሆነም የላኪያቸውን ትእዛዝ ለመፈሰጸም መሆኑን ሁሉም አውቆ ተቃውሞው ይቀጥላል እነሱም በይፋ ካድሬ እንጅ ሰላም ለማዋለድ የሚደክሙ አለመሆናቸውን ያሳዩናል!!

ሰላምን እርቅን ለማምጣት ዋናው የመ’አዘን ድንጋይ የአብይ አህመድ መንግስት እንደ ሐይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን አውርዶ በምትኩ የሽግግር እና ፍትህ እና የሽግግር መንግስት ሲቋቋም ብቻ ነው!! ADIOS!!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *