ዶ/ር አብርሃም ዓለሙና አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው፤ የኢትዮጵያን የ2011 ሽግግር ሂደት በምልሰት በመንቀስ ከ2012 ፊት የተደቀኑ ተስፋና ስጋቶችን ያነሳሉ። አማራጭ የመፍትሔ ሃሳቦቻቸውንም ያጋራሉ። ዶ/ር አብርሃም “ሁሉን አቀፍ የዕርቅና የሽግግር ጉባኤ ማካሄድ የሚያስፈልግ ይመስለኛል” ሲሉ፤ አቶ አክሊሉ “አዲስ ሥርዓትን ለማዋለድ መንግሥት ትናንሽ ሳይሆን መሠረታዊ የሆነ ለውጥ ለማድረግ መጣር አለበት” ይላሉ።
