shewa-youth
News

ለአፋር ህዝብ በተለይም ለወጣቶች/ዱኮ ሂና እኛ የሸዋ ወጣቶች ከጎናችሁ እንደሆንን ለመግለጽ እንወዳለን። – ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር

በአፋር ክልል ጅቡቲና ኢትዮጵያን በሚያዋስነው አፋምቦ ወረዳ ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሶ ከ16 ሰው በላይ እንደሞተ እና ከ30 ሰው በላይ እንደቆሰለ አሁንም ቁጥሩ እንደሚጨምር እየተገለፀ ይገኛል።

በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የአፋር ህዝብ ፣ትናንት በወያኔ ህወህት ቁጥጥር ስር ወድቆ ሲበዘበዝ ቢቆይም ፣ አሁንም ገዥዎች የአፋርን ህዝብ ረፍት በመንሳት ህዝቡ እንዳይረጋጋ እና ለተረኝነት ብዝበዛ እንዲመቻቸው እየሰሩ ይገኛሉ።

መነሻቸውን ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ ያደረጉ ድንበር እያቋረጡ የሚገቡ ታጣቂዎች በአፋር ወንድሞቻችን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ እያከናወኑ እንደሚገኝ እየሰማን ነው።

በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ እስካሁን ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ታጣቂዎች በተሽከርካሪዎች እየታገዙ ጥቃት ማድረሳቸውን ቀጥለዋል።

የምስራቅ አፍሪካን ቀጣና አረጋጋ በሚል የኖቬል ተሸላሚው የኢትዮጽያ መንግስትም እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም ፣ ዜጎቹን ለመጠበቅም ያደረገው ጥረት የለም።

በአዲስ አበባ የምትገኙ የአለም አቀፍ ማህበረሰቦች ፣ ሚዲያዎች ፣ አለም አቀፍ ተቋሟት እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ኢንባሲዎች የጉዳዮን አሳሳቢነት በመረዳት ትኩረት እንድሰጡት ጥሪ እናቀርባለን።

የአፋር ህዝብ በተለይም ወጣቶች/ ዱኮ ሂና / ጎረቤት የሆነው የሸዋ አማራ ህዝብም ሆነ ወጣት ከጎናችሁ እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

October 14, 2019

ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *