ዴሞክሲያ
News Press Release

ጥላቻ፣ አክራሪነትና ዘረኝነት አንድም ሦስትም ናቸው!

ዴሞክራሲያ ቅጽ 48 ፣ ቁጥር 3

ነሐሴ ፣ 2012 ዓ.ም

ሀገራችን ኢትዮጵያ የታሪክ ባለፀጋ ብትሆንም፣ በዘመናዊ ሥልጣኔ ኋላቀር መሆኗ ያ ትውልድ በመባል የሚታወቀውን ትውልድ እጅግ አስጨነቀው። የኢሕአፓን ቀደምትና የአሁን ጀግኖችን ያቀፈው ትውልድ፣ አገራችን ወደ ሥልጣኔ ማማ በፍጥነት እንድትደርስ ለማድረግ ያልቆፈረው ድንጋይ፣ ያልዘየደው መላ አልነበረም። ይሁን እንጂ ችኩልነቱ ከውስጣዊ ድክመቱ ጋር ተደምሮ ዓለም የነበረችበት ታሪካዊ ኩነትና ሥልጣኑን ለሕዝብ ለማስረከብ ያልፈቀደው ወታደራዊ ደርግ ባካሄደው ወደርየለሽ ጭፍጨፋ፣ አገር እንኳን ወደ ሥልጣኔ ማማ ልትሻገር ይቅርና ብሩኅ አእምሮ የነበረው ትውልድ ያለቀበት ታሪክ እንዲከሰት ሆነ። ያ አገር አፍቃሪ ትውልድ፣ ወደር የሌለውን መስዋዕትነት በሚከፍልበት ወቅት፣ ኢትዮጵያችን በአንድ በኩል በጉልበት ብቻ መፍትሄ ለማምጣት ትውልድ የፈጀው ወታደራዊ መንግሥት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ የታጠቁ ጎጠኛ ቡድኖች የሚፋለሙባት የጦርነት አውድማ ሆነች። የጎጠኞች ዓላማ ደርግን አሸንፈው ሕዝባችን የሚፈልገውን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመዘርጋት አልነበረም። በጥላቻ የታጀበውን ፀረ-ኢትዮጵያ ዓላማቸውን መተግበር መሆኑን ለማወቅ ሥልጣን እስቲይዙ መጠበቅ አላስፈለገም። በ1982 መግቢያ ላይ፣ ህወሓት

ሥልጣን ከመያዙ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ፣ በአሶሳ ከተማ ኦነግና ሻዕቢያ የተሳተፉበት ክርስቲያኖችንና አማራዎች የሚሏቸውን ለይተው ቤት ዘግተው በእሳት ማቃጠላቸው የሕዝቡ መፃዒ ዕድል ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች አሰቃቂ ተግባር ነበር። ህወሓት ሥልጣን ከያዘ በኋላ ከሸሪኩ ከኦነግ ጋር በምሥራቅ ሐረርጌ በወተርና አርባጉጉ በርካታ አማራ ያሏቸውን ዜጎች ገደል ውስጥ በመወርወር ጭምር ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን መፈጸማቸውን የወቅቱ ፓርላማ ተብዬው ሳይቀር ያመኑት እኩይ ተግባር ነበር። ህወሓት በኦነግ ሲያመካኝ፣ ኦነግም ህወሓት ነው ግድያውን የፈጸመው እየተባባሉ በፈጸሙትና ባመኑበት ወንጀል በሕግ ሳይጠየቁ ይህንኑ እርኩስ ተግባራቸውን ሕጋዊ ወደሚያደርግ ሕገ-መንግሥት ቀረፃ ተሸጋገሩ። ህወሓት ሲመሠረት ጀምሮ የአማራ ብሄረሰብን በ1968ዓ.ም ባወጣዉ የትግል ማኒፌስቶ በጠላትነት ፈርጇል። በለስ ቀንቶት ሥልጣን እስኪይዝ ድረስ ትግሌ የመገንጠል ነው ይልም ነበር። ህወሓት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር በተንሸዋረረ መንገድ በመተርጎም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዋናው ቅራኔ በብሄረሰቦች መካከል ያለው ነው አለ። ኢሕአፓ፣ ህወሓት የተንሸዋረረ አተያዩን እንዲያስተካክል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *