question mark
News

የአብይ ካቢኔ መናጥ ጀመረ እንዴ!? የሁሉቱ ሚኒስትሮች ይለቃሉ መባል እና አንድምታው!

amirየጤና ጥበቃ ሚ/ሩ አሚር ሊለቁ መሆኑን አስቀድሞ ምንጭ ጠቅሰን ለመዘገብ ሞክረናል።የውሃ ሀብት ሚኒስትሩም እንደሚለው ጋዜጠኛ ዮሐንስ አንበርብር ግምቱን ጨምሮ ጽፉዋል። የአብይ አህመድ(ዶ/ር) ካቢኔ እየተናጠ ይሆን? ግብጽ እንዲህ በግራ በቀኝ በአባይ ጉዳይ ወዲያ ወዲህ በምትልበት ወቅት ሽንጣቸውን ገትረው ሲሟጋቱ የምናውቃቸው ስለሺ በቀለ እውን በግል ምክንያት ነው የሚለቁት?

ይሄ የህዳሴ ግድብ መጨረሻው እንዴት ነው? ዋና ኢንጂነር ምስጢራዊ በሆነ መንገድ ተገደሉ፣የግድቡ ተርባይኖች ይቀንሳሉ ተባለ አሁን ደግሞ የውሃ ሀብት ሚኒስትሩ። የጋዜጠኛውን ምልክት ያንብቡት ሼር ያድርጉት

የግል ምክንያቶቻቸውን በመግለጽ ከስልጣናቸውን ለመልቀቅ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ ያቀረቡት የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) እና የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ አማር አማን (ዶ/ር) ናቸው።

seleshየውሃ ሚንስትሩን ጥያቄን ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ የተቀበሉ መሆኑን ምንጮቼ ነግረውኛል። የጤና ሚንስትሩ አሚር አማን የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ካቀረቡ ወራቶች ቢያልፉም እርሳቸውን የሚተካ ብቁ ሰው እስኪገኝ ድረስ በኃላፊነታቸው እንዲቆዩ ተነግሯቸው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩ አሚር አማንን በስልጣናቸው እንዲቆዩ ፍላጎት ቢኖራቸዎም በፌዴራል መንግስት የስልጣን ክፍፍል ውስጥ የጤና ሚንስትሩ አሚር አማን ቦታ አሁን ላይ የአዴፓ ድርሻ በመሆኑ እና ግለሰቡም በአዴፓ ውስጥ ያላቸው ተፈላጊነት መቀነሱን ተከትሎ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ጫና ሳያደርግባቸው እንዳልቀረ የነገራል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ውሳኔ እስካሁን ባይታወቅም ሚንስትሩ አሚር ግን በቦታው ለመቆየት ፍላጎት የሌላቸው መሆኑን እና ቀጣይ መዳረሻቸውም አሜሪካን ሀገር የሚገኝ አንድ በጤና ላይ የሚሰራ ዓለም አቀፍ የጤና ተቋም እንደሚሆን ምንጮቼ ነግረውኛል።

በተመሳሳይ የውሃ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ ወደዚህ ኃላፊነት ከመምጣታቸው ቀድም ብሎ ይሰሩበት ወደነበረ የተመድ አማካሪነት ስራቸው እንደሚመለሱ ከምንጮቼ አጣርቻለው።
ስለሺ በቀለ የኒውዮርክ የ UN የውሃ ኢነርጂ ጉዳዮች አማካሪ ነበሩ ፣ አሁን ካሉበት የሚንስትርነት ኃላፊነት ከለቀቁ በኃላ አዲስ አበባ በሚገኘው UNECA አጭር ቆይታ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሰምቻለው። ( ስለሺ በቀለ በነበራቸው የሦስት ዓመታት ቆይታ በግሌ የማውቀው የግብፅ ዕራስ ምታት እንደነበሩ ነው። ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ቢያቀርቡም የህዳሴ ግድቡ ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የሚጫወቱትን ሚና እንደሚኖር ሰምቻለው)።

ዮሀንስ አምበርብር

Source: ZeHabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *