ከዓለማቀፋዊ የአማራ ሕብረት የተሰጠ መግለጫ:
ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ለሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ የሆኑት እነጅዋር ሙሃመድ ለፍርድ ይቅረቡ::
ዶ/ር ዓቢይ አህመድ እንደመጡ በትኩሱ ያደረጓቸውን ሥራዎችና የወሰዷቸውን ዲሞክራሲያዊ የሚመስል እርምጃዎች በማድነቅ፣ ዘራፊና ገዳይ የነበሩት የወያኔ መሪዎች በመወገዳቸው የተሰማውን ደስታ በመግለጽ አማራው ከየሚኖርበት በሰልፍ እየወጣ ድጋፉን መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ነገር ግን፣ እየቆዬን ስንመጣ፣ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ፣ ስንሞት ኢትዮጵያ” በማለት ተስፋ በሰጡት ጠ/ሚ አገዛዝ የተሰነቀው ተስፋው እየጨለመ፣ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ፣ ህዝቡ ከወያኔ ጊዜ በባሰ እየተፈናቀለና እየተገደለ፣ በሜንጫ እየታረደ፣ ዓይኑ በጉጠት እየተጎለጎለ፣ ምላሱ እየተቆረጠ፣ የቤተክርስቲያንና የመስጊድ ማቃጠል፣ እጅግ ዘግናኝ ኢትዮጵያ ታሪክ ወስጥ ተሠርቶ፣ ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ የብሄርና የሃይማኖት ጦርነት ለመቀስቀስ፣ በተወሰኑ ቅጥረኞችና የተደራጁ አገርበቀል ወንጀለኞች ከፍተኛ ዘመቻ እየተጧጧፈ ይገኛል፡፡
ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞች የተደረገውን ጭፍጨፋ በተመለከተ፣ የጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መግለጫ፣ በጃዋር መሐመድ የጦር አዝማችነት የቄሮ ወራሪ ሠራዊት በአማሮች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በሁለት ተፎካካሪዎች መካከል እንደሚደረግ
ዕለታዊ ግጭት አድርጎ አሳንሶ በማስመሰል “እርስ በርስ ተቧድነው» የሚል ቃል በማኅበራዊ መገናኛ መናገራቸው እጅግ አስደማሚ ነው፣ ይህ አነጋገራችው የሚያመለክተው ወንጀለኛውን ቄሮን ተጠያቂ ላለማድረግ፣ የተጨፈጨፈው ግፍ የተሠራበት አማራው ለሞቱ ተጠያቂው ራሱ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ የተቃጣ ነው፡፡ ይሁን እንጅ፣ ዕውነታው ሌላ ነው፡ ቀንደኛ መሪውን ጃዋርንና ተከታይ ሠራዊቱን፣ ቄሮን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት የሚደረገው ሙከራ ሁሉ እጅግ አሳዛኝና አሳሳቢ ቢሆንም ቅሉ፣ የሰሞኑ የቄሮ ጭፍጨፋ በአማሮች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ መሆኑን ሊለውጠው የሚችል ከቶ ምንም ዐይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም፡፡
በኦነግና በወያኔ ተገንጣይ ቡድኖች ጊዜያዊ ስምምነትና የማያዛልቅ ሴራ፣ የአማራውን ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ለእነ ጅዋር ሙሃመድ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳና በቀለ ገርባ ለመሳሰሉት ከሀዲዎች ቁጥር የሌለው ገንዘብ እያፈሰሱ ድሀውንና ረሃብተኛውን ወጣት ዕውነትነት የሌለውና የተዛባ የሀሰት ታሪክ በመስጠት፣ አዕምሮውን በመበረዝና የጫት መቃሚያ ሣንቲም በማታለል ሥርዓት አልባ የሆነ ሁለተኛ መንግሥት
የሚመስል “ቄሮን” መሥርተው አገር ለማፍረስ በአማራውና በሌላውም፣ ኦሮሞ ባልሆነው ዘር ሁሉ ከፍተኛ ግድያና አሰቃቂ ድርጊት እየፈጸሙ ነው፡፡
ታዲያ የዚህ የቄሮ መንጋ መሪው አቶ ጅዋር ሙሀመድ መሆኑን መንግሥት ጠንቅቆ እያወቀ፣ ጭራሽ እሱን ምንም እንዳይነካው በስፔሻል ፎርስ፣ በሠለጠኑ ወታደሮች እየተጠበቀና በኢሀደግ ውስጥ በሚሠሩ የጦር መኮንኖች ፣ የደህንነት ሠራተኞችና ከፍተኛ ሹማምንት እየተደገፈ የፈለገውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል፡፡
እንግዴህ ኢትዮጵያን መምራት፣ ህዝብን ማስተዳደር ማለት ወንጀለኞችን፣ ያውም የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ የዘር ጥላቻ በመርጨት በገሀድ እየሰበኩ ያሉትን ቅጥረኞች አቅፎ ይዞ በየቀኑ ህዝብ እየታረደ፣ ዕትብቱ ከተቀበረበት ቦታው እየተፈናቀለ፣ እየተባረረና እየተገደለ፣ ድረሱልኝ፣ አድኑኝ በማለት እየተማጸነ፣ በገዛ አገሩ የሚደርስለት አጥቶ፣ የመንግሥት ያለህ እያለ ሲጮህ ጆሮ ዳባ ልበስ፣ ዓይኔን ግንባር
ያርገው አላየሁም፣ አልሰማሁም ብሎ ዝም ብሎ የሚቀመጥ ከሆነ በሀገራችን መንግሥት አለ? የለም በሚያስብል ደረጃ የብዙ ህዝብ ጥያቄ እየሆነ መጥቷል፡፡
አማራው፣ ወያኔን የጅአዙር የግፍ አገዛዝ ቀንበር ተሸክሞ ያለምንም ምክንያት አማራ በመሆኑ ብቻ ሲታሠር ሲገረፍ ሲኮላሽና ሲገደል ለ27 ኣመት ቢኖርም በደሉና ሰቆቃው፣ ግፉ ከመጠን
አልፎ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን ኢሀደግን ያሽከረክር የነበረውን የትግራይ ተገጣይ ቡድን ቁንጮ አባላትን አስወግዷል፡፡ አሁንም፣ አማራው የራሱንና የኢትዮጵያን
የሀገሩን ህልውና ለማረጋገጥ ከሌላው ሀቀኛና ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን እንደአያት ቀድመአያቱ ከባንዳና ከከሀዲ ጋር በመፋለም፣ በአጥንቱና በደሙ የኢትዮጵያን አንድነትና ህያውነት ለማረጋገጥ እንኳን ሜንጫና ቆንጨራ፤ መድፍና መትረጌስ እንደማይበግረው ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይኸ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማተረማመስ በግልጽ እየሠሩ ባሉት በነጅዋር ሙሀመድና ለነርሱም የእኩይ ሥራ አጋር ለሆኑላቸው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ለተሠገሰጉት ሹማምንት፣ የበታች ሠራተኛ፣ የጦርና የፖሊስ መኮንኖች ምንጊዜም ከንደዚህ ያለ አድላዊና ወገንተኛነተኝነት እንዲቆጠቡ አስፈላጊው ተግሳጽና ምክር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
በመቀጠል፣ ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1 – 6 የተዘረዘሩትን በመንግሥት በኩል ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲተገበሩ ቢደረግ ለሀገራችን ደህንነት ይበጃሉ የሚል ፅኑ እምነት አለን፤
1) የመንግሥት ታጣቂ ኃይሎችን ከለላ በማድረግ በቄሮዎችና በተደራጁ የአጥቂ ሀይሎች በጅዋር ሙሃመድ አሳታፊነት በደረሰው አሰቃቂ የሆነ የሰው ዕልቂት ሰለባ ለሆኑት ቀሪ ቤተሰቦች፣ በየቦታው አስቸኳይ የምግብ፣ የዉሃና የመጠለያ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው፣
2) ክ84 ቁጥር በላይ በሠላማዊ ሰው ላይ ለደረሰው የህይዎት መጥፋትና ለንብረት መውደም ዋና ተጠያቂው ጅዋር ሙሃመድ ነው፤ ስለሆነም፣ ነገ ዛሬ ሳይባል ባስቸኳይ ተይዞ በሕግ ፊት ለፍርድ እንዲቀርብ መደረግ አለበት፣
3) በኢትዮጵያ የክርስትና አማኞችና ካህናት በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ያላቋረጠ ጭፍጨፍና እልቂት በአስቸኳይ እንዲቆምና መንግሥት ተገቢውን ጥበቃና መልሶ የማቋቋም ተግባር እንዲያከናውን፣ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው እንደ ሁኔታው አሰቃቂነትና ብዛታቸው መጠንና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው፣ ተመጣጣኝ ካሣ መንግሥት እንዲከፍላቸው አበክረን እንጠይቃለን፤
4) በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረተውን ህገመንግሥት ተገን በማድረግ በአማራው ላይ “ነፍጠኛ/ትምክህተኛ” የሚል ቅጽል ስም በመስጠት፣ ከአማራ ክልል ውጭም ሆነ በአማራ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን ዕልቂትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመግታት ጸጥታና መረጋጋት እንዲኖር፣ ባስቸኳይ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ የህዝቡን ደህንነት በሚያረጋግጥ መንገድ በአዋጅ የህግ የበላይነት እንዲከበር ያደርግ ዘንድ አጥብቀን እናሳስባእን፤
5) ሰውን እንደንስሳ የሚያርዱ በነጅዋር የሠለጠኑ ሥራ ፈቶች ተከታታይ የሰብዓዊነትና በዘረኞቹ ቀጣሪዎቻቸው የሚሰጣቸው የሀሰት ትርክቶችን አስመልክቶ ትምህርት እንዲሰጣቸው፣
6) ባልፉት ሣምንታት ውስጥ በሀገራችን የተካሄደው ኢሰባዊ ድርጊት በተለይም በናዝሬት፣ በደብረ ዘይት፣ በድሬ ዳዋና ሀረር፣ በባሌ ሮቢ፣ በአሩሲ – ዶዶላ፡ በተፈጸመው የህዝብ ዕልቂትና የንብረት ውድመት፣ ከሀገር ውስጥና ከተባበሩት መንግሥታት የተወጣጣ ገለልተኛ ቡድን ባስቸኳይ እንዲቋቋምና ከቄሮ በስተጀርባ ሆኖ የጭጨፋው ተካፋይ የነበረው አካል በምርመራ ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለጽ፤
በማጠቃለል እንደማሳሰቢያ የምናቀርበው፦ በውስጥና በውጭ ያለው ያገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ፣ የጸጥታው፣ የኢኮኖሚ፣ የፖሊቲካና የማሕበረሰባዊ አቋም አስተማማኝ ባለመሆኑ፣ ማሕበረሰቡ እችግር ላይ እንደወደቀ አያሌ ምልክቶች ያሳያሉ፤ ይህንን የማኅበራዊ ቀውስ ወደባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት፣ አሁን በሥራ ላይ ያለው መንግሥት በባላደራ ወይም ጊዜያዊ መንግሥት መተካት የሚችልበትን መንገድ በመቀየስ ከወዲሁ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ሀገሪቱን ካልተጠበቀ ደም መፋሰስና እልቂት ያድናል ብለን በጽኑ እናስባለን፡፡
አማራው ከሌላው ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ ወ ገኑ ጋር በመሆን የራሱንና የኢትዮጵያን ህልውና ያስከብራል