ሙስሊም ኦሮሞ
Opinion

“ባለ አደራው ም/ቤት”፣ ቄሮ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ? – ባይሳ ዋቅ-ወያ

“ባለ አደራው ም/ቤት”፣ ቄሮ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ? – በአገራችን በተንሰራፋው ያለመረጋጋት ምክንያት ለወራት ፊታችንን አጨልመን እና ነገ ደግሞ ምን ይፈጠር ይሆን ብለን በስጋት መኖር ከጀመርን ከአንድ ዓመት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ አንዳንድ ልብ የሚያረኩ ዜናዎች ተሰምተው ለብዙ ጊዜ ቸር ወሬ ለመስማት ሲጓጓ የነበረውን ሕዝባችንን ልብ አርክቶ ነበር፡፡ የዶ/ር ዓቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማት፣ የፍሬወይኒ የሲኤንኤን “የዓመቱ ጀግና” መባል እና የሳሙእል ተፈራ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ተብለው በዓለም አቀፍ መድረክ ቀርበው ሽልማታቸውን ሲወስዱ ማየቱ አንዳች ዓይነት የተስፋ ብርሃን ያሳየን ሳምንት ነበር።

በተቃራኒው ግን ያው እንደተለመደው፣ ከወደ አሜሪካ የሚነፍሰው ወሬ ደግሞ የባለ አደራ ምክር ቤት አባላት “ቄሮን በሽብረተኝነት ፈርጀውና በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰሰ” አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን በዋሺንግተን ዲሲ ለደጋፊዎቻቸው ማብሰራቸውን ነው። በስብሰባው ወቅት፣ የባላደራው ምክር ቤት አባላት በሚቀጥለው ምርጫ ተካፋይ ለመሆን ፓርቲ ለመፍጠር ዝግጅት ላይ መሆናቸውንና ቄሮን ደግሞ በተባባሩት መንግሥታት ደረጃ በአሸባሪነት ለማስፈረጅና በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ አስተባባሪ ኮሚቴ መፍጠራቸውን አስታውቀዋል። አስተባባሪ ኮሚቴውም ከጥቂት ቀናት በኋላ ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ

“ባለሥልጣናት” ጋር ተገናኝተው ቄሮ ሽብረተኛ መሆኑንና ባገሪቷ ውስጥም የጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀል Genocide ፈጽሟል ብለው አስፈላጊውን ማብራርያ መስጠታቸውን አብስረዋል።

የአስተባባሪው ኮሚቴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “ባለሥልጣናት” ጋር ተገናኝቶ ስለ ቄሮ ሽብርተኝነትና ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጽሟል ስላላቸው የጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀል “አስፈላጊውን መረጃ” የመስጠታቸውን ዕውኔታ ባለፉት ሶስት አሥርተ ዓመታት በመንግሥታቱ ድርጅት በሠራሁባቸው ጊዜያት ከማውቀው ተነስቼ፣ ያገኟቸው ባላሥልጣናት በምን ደረጃ ላይ እንደሆኑና ለቀረበውም ጥያቄ አንዳችም መልስ የመስጠት ሥልጣን እንደሌላቸው ስለማውቅ ብዙም አላሳሰበኝም። የባላደራው ምክር ቤት ግን አቋቋማለሁ ስላለው የፖሊቲካ ፓርቲና ለሚቀጥለው ምርጫም ከዚህ የተሻለ “የቅስቀሳ ሸቀጥ” ሊያገኝ ስለማይችል፣ ደጋፊዎቹን ለማስደሰት ይህንን “ታሪካዊ ድል” ለመጎናጸፍ መሞከሩ ማንም የፖሊቲካ ድርጅት ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ ምንም አያስገርምም።

አዎ ያገራችን ጉዳይ ማንናችንም ሊያሳስበን ይገባል። በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ መፈናቀልና በጅምላ መገደል እየተከሰተ ነው። በጽንፈኞች ቅስቀሳና አነሳሽነት ምክንያት ለዘመናት አብረው ይኖሩ በነበሩ የሶማሌና የኦሮሞ ሕዝቦች፣ በጌዴዎና የኦሮሞ ሕዝቦች፣ የጉሙዝና የኦሮሞ ሕዝቦች፣ በጉሙዝና በአማራ ሕዝቦች እንዲሁም ባማራ ክልል ውስጥ በተነሱ የማንነት ጥያቄዎች ሳቢያ በአጠቃላይ ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የታጠቁ ኃይላትን እንቅስቃሴ ለመግታት ታስቦ መንግሥት የኮማንድ ፖስትን አውጆ በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው፡፡ ከጉሙዝ በኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉትን የአማራ ብሄር ተወላጆችን አስመልክቶ በተፈጸመው የአጸፋ እርምጃ በጣም ብዙ የጉሙዝ ብሄር ተወላጆች በጅምላ ተገድለዋል። በዚሁ በያዝነው ሳምንት የጎንደር ከተማ አዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞላ መልካሙ እንደ ገለጹት፣ በመስከረም ወር ብቻ በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳና በአካባቢው በተከሰተ

ግጭት 43 ሰላማዊ ሰዎች በጅምላ ሲገደሉ ከ8,000 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ከቄያቸው ተፈናቅለዋል። በቅርቡ ከጃዋር የጸጥታ ጥበቃ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በተከሰተው ሁከት 86 ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ ተገድለዋል። በተለያዩ የአገሪቷ ዩኒቬርሲቲዎች በጽንፈኞች የታቀደ ነው ተብሎ በሚታመንበት የተማሪዎች የርስ በርስ ግጭት ሳቢያ 6 ተማሪዎች ተገድለዋል። ሌላም ብዙ ግድያዎችና የንብረት ውድመት በተለያዩ ክልላት እየተከሰተ ነው።

Full stores

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *