News

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ‘ለትግራይ ሕዝብ ያለኝን አማራጭ ሃሳብ እንዳላቀርብ ተቸገርኩ’ አለ

,የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲአ ማራጭ ሀሳቦችን እንዳያይ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ ታፍኖና ነፃነቱ ተገድቦ የሚገኘውን የትግራይ ሕዝብ’ በአማራጭነት ለማገልገል የማካሄደው ሕጋዊ ትግል ተገድቦብኛል ሲል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ከመቸውም ጊዜ የተለየ ጭቆናና አፈና ውስጥ ነው በማለትም ፓርቲው አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንና ምሁራንን በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አወያይቷል።

በውይይቱ ከተሳተፉት ፓርቲዎች መካከል አንዱ በዶክተር አረጋዊ በርሄ የሚመራው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ይገኝበታል።

የፓርቲው አመራሮች አቶ ሙሉብርሃን ኃይሌና አቶ ጊዳና መድህን በውይይቱ ላይ እንዳሉት ፓርቲያቸው ለትግራይ ሕዝብ አማራጭ ሃሳብ ይዞ ለመሥራት ወደማይቻልበት ደረጃ ላይ እየተደረሰ ነው።

What are some negative consequences of dictatorship?

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በተለይ በትግራይ ክልል በመንቀሳቀስ ዓላማውን ለህዝብ ማስተዋወቅ እንዳይችል የማሸማቀቅ ተግባር እየተፈጸመበት መሆኑን አቶ ሙሉብርሃን ይገልፃሉ።

ለፓርቲው አባሎች የተለያዩ የጥላቻ ስያሜዎችን በመስጠት ከህዝብ ለመነጠል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሥራ እየተከናወነ እንደሆነም ተናግረዋል።

ፓርቲው ይህንን ፕሮፓጋንዳ ሀሰት መሆኑን ለህዝቡ በማስረዳት መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል እድል እንደሌለውም ነው ያብራሩት።

በአሁኑ ወቅት ትግራይ ውስጥ ሕዝቡ ከመቸውም ጊዜ በተለየ በጭቆናና አፈና ውስጥ እንዳለ የሚናገሩት አቶ ጊዳና የመብት ረገጣውን እንዲህ ያብራራሉ።

“በትግራይ ውስጥ ጭቆና አለ፣ ግፍ አለ፣ በአሁኑ ወቅት አሁንም የአረና አባላት እየታሰሩ ነው” የሚሉት አቶ ጊዳና ደግሞ የመላው የትግራይ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ ለመብቱ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።

የፌዴራል መንግሥቱም ከትግራይ ህዝብ ጎን መሰለፍ እንዳለበትም አቶ ሙሉብርሃን አሳስበዋል።

ፌዴራል መንግሥት በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት የሚካሄደውን አጠቃላይ የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ አቅጣጫ አስመልክቶ ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመምከር በሕውሓት እየተሠራ ያለውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳና ሕገ-መንግሥታዊ ጥሰት ለማስተካከል የበኩሉን ማድረግ እንዳለበትም አስረድተዋል።

ከዚህ አንፃርም መንግሥት ሕጋዊ አግባቡን ተከትለው የሚሠሩ ፓርቲዎችን ማበረታታት እንደሚገባም አቶ ሙሉብርሃን ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሃት ኢዜአ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ተወካዩን በመላክ እንዲሳተፉ ጥሪ የቀረበለት ቢሆንም ሳይገኝ በመቅረቱ በፓርቲው በኩል ያለውን አቋም ማስተናገድ አልተቻለም።

Source: Zehabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *