የምረጡኝ ቅስቀሳ
News Politics

እኔን ብትመርጡኝ ፣ ለሚመጣው ምርጫ ለጠጪዎች ውስኪ ፣ ለቃሚዎች በርጫ

 

የምረጡኝ ቅስቀሳ

(በላይ በቀለ ወያ) ፈገግ ብላችሁ እደሩ😂
.
.
እኔን ብትመርጡኝ ፣ ለሚመጣው ምርጫ
ለጠጪዎች ውስኪ ፣ ለቃሚዎች በርጫ
ለእግርኳስ ክለቦች ፣ ለእያንዳንዱ ዋንጫ
ለፈረሶች ፍጥነት ፣ ለአህዮች እርግጫ
በነፃ አድላለሁ።
።።።
በሚመጣው ምርጫ ፣ እኔን ብትመርጡኝ
ድምፃዊ ሳትሆኑ ፣ ድምፅ ብትሰጡኝ
አንድ ዜማ ሰሪ ፣ አንድ ጊልዶ ካሳ😂
አንዲት ውብ ኮረዳ ፣ አንድ ውብ ጎረምሳ😂
አንድ ካሜራ ማን ፣
አንድ የባህል ቡድን ፣ ክሊፕ የሚሰሩ
ወይም ዘመናዊ ፣ ዳንስ የሚጨፍሩ
አስቀምጣለሁኝ ፣ በየ አንድ ሜትሩ😂
(ግጥሙን ለኔ ተውት😂)
።።።
ለሚመጣው ምርጫ ፣ እኔን ብትመርጡ
በዘር በሀይማኖት ፣ ምትቦጣቦጡ
ሰላም ያልገባችሁ ፣ ለፀብ የምትሮጡ
ከኪሴ መድቤ ፣ ከፍተኛ ባጀት
ጠብመንጃ ገጀራ ፣ ታንክና የጦር ጀት
ከሆነ ቦታ ጋር ፣ ለጦር ሜዳ ምቹ
በነፃ አድላለሁ ፣ እንዲዋጣላቹ😂!
።።።
ለሚመጣው ምርጫ ፣ ብትመርጡኝ እኔን
በምስራቅ ፣ በደቡብ ፣ በምእራብ ፣ በሰሜን
ላሉ ህዝቦች ሁሉ ፣ አንዳች ሳላዳላ
ቀስት የፈላ ውሃ ፣ ክላሽና ዱላ
ለተጠቃሚዎች ፣ በነፃ አድላለሁ
ለእያንዳንዱ ቤት ፣
ቤት ቁጥር አንስቼ ፣ ክልል እሰጣለሁ😂
።።።።
ለሚመጣው ምርጫ
እኔን ብትመርጡኝ ፣ ሔዋኔና አዳሜ
አልጋ ቤት በነፃ
አድላችኃለሁ ፣ ቅዳሜ ቅዳሜ😂
።።።
ለሚመጣው ምርጫ ፣ እኔን ብትመርጡ
ላመት ባል ላመትባል
ነጭ የጤፍ እንጀራ ፣ ጥብሱ ዶሮ ወጡ
ጥሬ ስጋ ቁርጡ
ጠላው እና ጠጁም
በቴሌቭዥን መስኮት ፣ አይታችሁ አትጎመጁም
ሁሉንም በቤታችሁ ታገኙታላቹ
ምርጫ በሌለበት
ምርጫችሁ እኔ ነኝ ፣ ምረጡኝ ባካቹ😂
።።።
ሁሉ እንደ ፈቀደው
ሁሉ እንደወደደው
ሚኖርባት ሀገር
መኖር ብትፈልጉ ፣ ምረጡኝ በሞቴ
ምልክት የለውም ፣ ምርጫ ምልክቴ😂

ምንጭ ፡ የእፀህይወት አበበ (ፌስቡክ) -Etsehiwet Abebe

Election Violence and Voting in Emerging Democracies

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *