ተገኝ ሞገስ-Tegegn Mogus
News

የኢህአፓው አንጋፋ ታጋይ አቶ ተገኘ ሞገሥ (አባዬ) የዓላማ ፅናቱ ወደር የማይገኝለት ጠንካራ ሰው ነበር

 ኢትዮጵያ ሙሉ ህይወቱን ሲታገልላት የኖረው የቁርጥ ቀን ልጅዋን ተገኝ ሞገስ አቦየን በሞት ተነጠቀች – የኢህአፓው አንጋፋ ታጋይ አቶ ተገኘ ሞገሥ(አባዬ) የዓላማ ፅናቱ ወደር የማይገኝለት ጠንካራ ሰው ነበር

አዎ! በርግጥም ጋሽ ተገኘ (አባዬ) ጓዳችንም፤ አባታችንም፤ አሥተማሪያችንም ሁለመናችን ነበር፡፡ ከትግሉ ጎራ ርቀን ሞቅና ቀዝቀዝ ባልንበት ጊዜ ሁሉ ፍቅሩ የማይቀዘቅዝ ብሩህና ርህሩህ የዓላማ ፅናቱ ወደር የማይገኝለት ጠንካራ ሰው ነበር። የድሮው ትውልድ በኃሳብ ልዩነት አብሮት ይታገል የነበረው ሰው ከጎኑ ሲርቅ ምን ያክል አምሮ እንደሚጠላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያለፍን ሰዎች ፈጽም የማንክደው ሃቅ ነው። በትሁቱ ጓድ ተገኝ (አባዬ) ልብ ውስጥ ግን ፈፅሞ ኩርፊያም ይሁን የባህሪ ለውጥ አይታይበትም ነበር። ከሁሉም በላይ የነበረውን ሰባአዊ ፍቅር ይዞ መቀጠል እንደሚቻል ካስተማሩኝ አንጋፋ የኢህአፓ አመራር አባላት ብቸኛው አባዬ ነበር። በዚህም ፍቅሩን የምገልፅበት ከሱ የወረስኩት አባዬ የምትለዋን ቃል ዘወትር እንደምጠቀም የቅርብ ጓደኞቸ ምሥክር ናቸው።
አዎ! ትግሉን ባልቀጠሉም ይሁን አሁን በአባልነት እየቀጠሉ ላሉትም የኢህአፓ ብዙኃኖች በታሪክ የሚጋራኝ የዛሬ ወንድሜ የድሮ ጓዴ ታዘበው አሰፋ እንዳለው፤ የአሟሟቱ ክፋት ተገናኝተን እምባ እንኳ አፍሰን በማንሸኝበት ወቅት በመሆኑ እጅግ ጨለማ ቀን ሆኗል።


እንዲያው በደፈናው!
አማርኛም የለኝ አንደበቴ ዝግ ነው ቃልም አልናገር፤
እስኪ በጥቂቱ ትንሽ ላንጎራጉር።
የወርቃማው ትውልድ ተምሳሌት የነበር፤
መፅሐፍ እማይበቃው ቢነገር ቢዘከር፤
በዓላማ ፅናቱ ስሙን ተክሎ አላፊው ጓድ ተገኝ ነበር።
እንዲያው በሁሉም ቤት ሞት ጥላውን ጥሎ
ገና ነፍስ ሳትወጣ እቤት ውስጥ ቆለፈን ሁሉን አነጣጥሎ።
ወደዚያኛው ዓለም ለተሰናበተው አፈር እንዳንጥል
እንዲያው በደፈናው ሁለመናችንም ሆኗል እርር ቅጥል፡
ሙሾ እንደንድር፤ እምባም እንድናዎርድ
በአይንም የማይታይ በጅ እማይጨበጥ
ሁሉም ብናኝ ሆነ እንደ ቤንዚን አመድ።
አዎ! አባዬ ተግኘ አካሄደህ ሁሉ ሆኖበናል ህልም፤
በመቃብርህ ላይ አፈሩን ሳንጥል ሳናወጣም እርም።
እኛማ ከእንግዲህ!
አልሞተም ነው እምንል ለጠየቀን ሁሉ፤
እዲያው እንደ ድሮዎ የፀና በቃሉ።
ዋሻችሁ አንባል ወይ ፍርድ ፊት ቁሙ፤
እውንት ምሥክር ነው!
ታጋይ ሥጋው እንጅ መች ይሞታል ስሙ።
በ. አ.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *