ህወሀትን በተመለከተ ምን ይደረግ፣ ሕዝቡ ምን ይላል?
ከጁላይ 10፣ 2020 እስክ ረብኡ ጁላይ 15፣ 2020የተካሄደ የዳስሣ ጥናት ግኝትች
ከባጤሮ በቀለ
ጁን 19፣2020
በሀገራችን በኢትዮጰያ ውስጥ ህወሀት መራሽ መንግስት ለ27 ተከታታይ አመታት በስልጣን ላይ ቆይቷል። ህወሀት በህዝብ ትግል ከአዲስ አብባው ስልጣኑ ተባሮ መቀሌ ከመሽገ ወዲህ እየቆየና እያደር አብሮት ከነበሩት ሌሎች የኢሀአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር ሳይቀር አየተቀራረበና ልዩነቱንም እያጠበበ ከመሄድ ይልቅ በየጊዜው የተካረረ ቀራኔ ወስጥ እየገባ ይገኛል።
እንዳለፉት 28 እመታት ሁሉ አሁንም ትግራይን ለብቻው በማሰተዳደር ላይ የሚገኘው ሀወሀት ባላፉት ጥቂት ወራት የመአከላዊ መንግስቱን (የፌደራል መንግስቱን)ወሳኔዎች ከመቃወም አልፎ የፊደራል መንግስቱን ሙሉ በሙሉ “ በአምባገነንነት ፈርጆ” ርሱንም
ለማስወገድ ሰፊ የቅስቀሳ ሰራ እየሰራ ይገኛል።
በቅርቡ የሀገር አቀፉ የፓርላማ ምርጫ መራዘምና የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ህወሀት ከፊደራል መንግስቱና ከገዥው የብልጽግና ፓርቲ ጋር ይበልጥ ወደ ተካረረ ቅራኔ ገብቷል።
ህወሀት የህዝብ ድጋፍ አለኝ አሁንም የኔን ራአይ ህዝብ ይደግፋል ይላል። ትላንትም ዛሬም ተወዳጅ ነኝ ይላል። በሌላ በኩል ሌሎች ይህ ሀስት ነው ሀውሀት እጅግ የተጠላ ድርጅት ነው ያላሉ፡ ህወሀት ክፋፋይና አጥፊ ድርጅት ነው ይላሉ። በአሁኑ ሰአት በሀገሪቱ
የተላያዩ ቦታዎች የሚታዩት ግጭቶችና አለመረጋጋቶች በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ የህወሀት እጅ አለበት የሚለው አመለካከት በስፊው ይደመጣል።
እነዚህንና ሌሎችንም ሁኔታዎች በሚታዩበት በአሁኑ ሰአት የህዝቡ አመለካክት ምንድን ነው ፣ የሚለውን በአራት ቁልፍ ጥያቄዎች ዙሪያ በዚች አጭር የዳሰሣ ጥናት ለማየት ሞክሬአለሁ።
ጥናቱ እንዴትና መቼ ተካሄደ