Zeregna
Opinion

በደደብነት ላይ ዘረኝነት

በቅርቡ ከአንድ ወዳጄ ጋር በስልክ ጨዋታችን መሃል “አንድ ደደብ ሰው ዘረኛ ቢሆንስ?” ብዬ ጠይቄው ሳልጨርስ “ኦ ኦ ኦ ኦ ከአውቶሚክ ቦንብ የበለጠ ጥፋት ያደርሳል” ያለኝ ዛሬ ትዝ ብሎኝ ነው በዚህ የአዲስ መንግስት ምስረታ ቀን ሃሳቤን ላካፍላችሁ የፈለኩት ወቅቱ የአንድ ምዕራፍ ማለቂያና የሚቀጥለው መጀመርያ ቀንስለሆነ፣ባለፉት ዓመታት ስለዘረኝነት የታዘብኳቸውን ባጭሩ ላካፍላችሁ ስወስን፣ እንደአስተማሪ የማታውቁትን ላስተምራችሁ ሳይሆን እንደ ዜጋ የበኩሌን ነግሬያችሁ ከናንተም ለመማር ነው:: ጽሁፉ የተናጠል ጥቃትን ለመከላከል በብሔር ወይም ባመቻቸው መንገድ ለመደራጀት የተገደዱትንአይመለከትም:: በተረፈ ጥቂት የተጠቀምኩባቸው ቃላት ከበድ ካሉ በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ::

በዘልማድ እንደሚባለው፣ መሃይምነት ከስህተት፣ ወይም ከደደብነት ጋርአይገናኝም:: ዘመናዊ ትምህርት ያልተማሩም ሆኑ በጣታቸው ይፈርሙ የነበሩ ቀደምት ወላጆቻችን ለዘመናት ሕግና ስርዓትን አስጠብቀው፣ ዳር ድንበራችንን አስከብረው አስተላልፈውልናል:: መሃይሙም ሆነ ቀለም የቆጠረው ሁለቱም ብልህና ብሩህ ካልሆኑ ደደብ ሊሆኑይችላሉ;; ትምህርት ቤት ስለተሄደ ብቻ ከድድብና ማምለጥ አይቻለም:: ድድብና ሰዎች ከነሱ ውጪ ያለውን ክስተት የሚገነዘቡበት መንገድ እና ሳያመዛዝኑ ሕይወታቸውን ለመምራት ወስነው የሚወስዱት ተግባርንና ተከትሎ የሚከሰተውን ውጤትን ያካትታል;; በአደጋና በተፈጥሮ ምክንያት የአዕምሮ ችግር ያለባቸውን ይህ አስተያየት ወይም ጽሁፉ አይመለከትም::

ሰዎችእንደመሆናችን በሕይወት ዘመናችን ስንሳሳት ከራሳችን ስህተትም ሆነ ሌሎች ነግረው መክረውና ተቀጥተን የምናስተካክለው ስህተት እንጂ ደደብነት አድርጌ አልወስደውም:: ደደብነትን እኔ የማየው ባጭሩ፣በምንም አይነት መንገድ ስህተትን ለማረም የማይፈልጉና በቋሚነት“የሕይወትመመርያቸው” አድርገው መርጠው የሚጓዙትንነው:: እንደዚህአይነት ስብእና ያላቸው ሰዎች በየምንኖርበት ሀገር ለማስተዋል ከሞከርን፣ ብዙቦታ ለመድረስ ዕድል ያለበት ሀገር እየኖሩ፣ እራሳቸውን ባማሻሻል ጥሩ ቦታ ደርሰው ሀገራቸውንና ወገናቸውን ለማገዝ ከሚያጠፉት ጊዜና ጉልበት ይልቅ፣ የሚያስደስታቸው፣ቡድንና ሰፈር እየቀያየሩ፣ወሬ በማመላለስ፣ እርስ በርስ በማጋጨትና በማተራመስ የመርካት ባህሪያላቸው ደደቦች ናቸው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *