Press Release

ኢሕአፓ የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ያወጣውን መግለጫ እንደማይመለከተው አስታወቀ

eprpHeader2020

የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ያወጣውን መግለጫ አስመልክቶ ከኢሕአፓ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ!

እንደሚታወቀው በተደጋጋሚ፣መንግሥት ሕግ የማስከበር ሚናውን መወጣት አለበት!” እያልን ድምፃችንን ስናሰማ ቆይተናል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩትም ሁከቶችና ብጥብጦችም ራሱንየትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት/ግንባርየሚለው ኃይል ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ስለመሆኑ ፀሐይ የሞቀው፣ አገር ያወቀው ሲሆን፣ በመላ ኢትዮጵያ ለተከሰቱት የሠላምና ፀጥታ እጦቶች ከፍተኛውን ሚና ወጫወቱ ዕሙን ነው፡፡ መንግሥትም በዚህ አደገኛና ከፋፋይ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደምንደግፍና አባሎቻችንም ጭምር ከመንግሥት የፀጥታና የሕግ አስከባሪዎች ጎን እንዲቆሙ በጥቅምት 26/2013 . ባወጣነው መግለጫ ላይ በግልጽ አንጸባርቀናል፡፡

አሁንም ሆነ ወደፊት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍንና የዜጎች ተዘዋውሮ የመኖር፣ ሃብትና ንብረት የማፍራት፣ እንዲሁም በፈለጉት አጀንዳና ዓላማ ሥር በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የመደራጀት፣ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንዳላቸው በመግለጫዎቻችንና በጽሑፎቻችንም ውስጥ በአጽንኦት መግለጻችን ይታወቃል፡፡ በአሁኑም የመንግሥትየሕግ ማስከበርእንቅስቃሴ ወቅት ይህ የዜጎች መብት እንዳይጣስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡ ለዚህም ክቡር ዓላማ ዋጋ እየከፈሉ ላሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትና የጸጥታ ኃይሎች በሞላ ከፍተኛ አክብሮት እንዳለን ለመግለጽ እንፈልጋለን፡፡ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችንም ይህንን ክቡር የሆነ ዓላማ እና ግብ ለመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን በድጋሚ እናስተላልፋለን፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት (የጋራ /ቤት) አመራሮች ኢሕአፓ እንደ ምክር ቤት አባልነቱ ለውይይት ሳይጋበዝ፤ ግልጽ አቋም በያዝንበትና ደጋግመን እንዲከበር የጮኽንለትን የሕግ የበላይነት የማስከበር ግብግብበድርድርና በውይይት እንዲጠናቀቅመፈለጋቸውን አይተናል፡፡ ይህን የጋራ /ቤት አመራሮች አቋም ኢሕአፓ እንደ አባልነቱ ያልተወያየበትና ያልመከረበት መግለጫና ማብራሪያ በመሆኑ ፓርቲያችን በጥብቅ ይቃወመዋል፡፡ የጋራ /ቤቱ አመራሮች በም/ቤቱ ስም ከሕወሓት ጋር ድርድር ይካሄድ ማለታቸውንም ኢሕአፓ እንደማይቀበለው አጥብቀን እንገልጻለን፡፡ ከዚህ በኋላም የጋራ /ቤቱ ፓርቲዎች በተናጠል አቋም የያዙበትን አጀንዳና ፖለቲካዊ አቋም ሳያወያይና ምክክር ሳይደረግበት በምንም ዓይነት በመገናኛ ብዙኃን ላይም ሆነ፣ በየትኛውም የማኅበራዊ ድረገጽ ላይ እንዳያወጣ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በተጨማሪም የጋራ /ቤቱ አመራሮች በም/ቤቱ ስም ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳንጸባረቁት፣ በምድር ላይ ያለውን ሁኔታ በአግባቡ ባላገናዘበ መልኩ ሲሆን፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ያደረሰውን እና የሀገርና የሕዝብ ንብረት የሆነውን፣በትግራይ ክልል ውስጥ የነበረውን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሬ ሥር አውያልሁ!” በማለት በሀገወጥ ተግባር እንደተሰማራ በይፋ ከሚናገረው ህወሓት ጋር ድርድር ይካሄድ ማለታቸውንም ኢሕአፓ እንደማይቀበለው አጥብቀን እንገልጻለን፡፡

ኢሕአፓ ስለብሄራዊ እርቅ፣ ስለደርድርና ሀገራዊ መግባባት የነበረውና አሁንም ያለው ቁርጠኛ አቋም የማይናወጥ ነው። ሆኖም እነዚህ ሁሉ አግባብ ባለው ቦታና ሁኔታ ውስጥ ሊታዩ ይገባል የሚል ጽኑ አቋም አለው። የሀገርን መከላከያ ሠራዊት ከረሸኑና የሀገር መከላከያ የሆኑ ንብረቶችንም በጉልበት ከነጠቁ በኋላ፣ጉዳዩ የብሄራዊ እርቅ ጉዳይ ነው፤ማለት አግባብነት ያለው አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥቃት መካችነት ከአስከፊነት ጦርነት ወጣለች

ኢትዮጵያ አንድነቷ ተከበሮ ለዘላለም ትኑር

ኢሕአፓ ለተሻለ ነገ!

ጥቅምት 30/2013  .    አዲስ አባባ


Phone :0911405427/0946240724/0911393535  Email: eprp@eprp-ihapa.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *