Aklilu Wondaferew
Opinion

ህወሀት በህግ መታገድ ብቻ ሳይሆን መፍረስም ይኖርበታል ልዩ ጦሩም እንደዚሁ

 

በኖቨምበር 2፣ 2020 ህወሀት ትግራይ ውስጥ፡በሚገኘው የስሜን አዝ እና በፊደራል ፖሊስ አባላት ላይ በሌሊት ወታደራዊ ወረራ አካሄደ። በዚህ ሂደት ውስጥ የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት አሰረኛ አደረገ ብዙወችን በግፍ ገደለ የሀገር ንብረትን ግማሹን አቃጠለ ሌላውን ዘረፈ። ይህ የሆነው ሰራዊቱ ሀገር ስላም በወገኔ መሀል ነው ያለሁት ብሎ ተዝናንቶ በተኛበት ነበር፡፡”ከማንኛውም የሀገሪቱ ክልል ሰላማዊው እኛ ነን ይሉ የነበሩት ህወሀቶች ፣ አካባቢውን ለቆ ይውጣ የተባለውን ሰራዊት በፍጽም ጥሎን መውጣት የለበትም ብለው ሲጮሁ የከረሙት የህወሀት መሪዎች የፈጸሙት ግድያን የጨመረ ወንጀል  ድንገት የመጣ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተጠነሰሰና የተቀነባበረ ( Premeditated)    እንደሆነ ግልጽ ነው።

ድርጊቱ ከተፈጸጸም ውሽት ነው ሰበብ ፈልገው ትግራይን ሊወጉ ነው ወዘተ  በማለት ለማድበስበስ ሙከራ ቢያደርጉም ሴኩቱሬ የተባለው የህውሀት ባለልጣን ሀውሀትን ከእስራኤል ጋር በማመሳስል  ከአረቦች ጋር በተደረጉ ወጊያዎች እስራኤል እንዳደረገችው እኛም በ 45 ደቂቃ አኦፐሪሽን  ቀድሞ በማጥቃት 30 ሽ ስራዊት ከጥቅም ወጭ አደረግን ሲል ተሳለቀ።

ይህ ሁኔታ ሀወሀት በሀጋዊ መንገድ የሚሰራ የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን ፖለቲካውንና ወታደራዊ ተግባርን አቀነባብሮ ይጓዝ የነበረ ሀይል እንደሆነ፣ የትግራይ ልዩ ሀይልም ለሀገራችን ህገመንግስት ታማኝ ሆኖ የቆመ ገለልተኛ ሰራዊት ሳይሆን የአንድ ፓርቲ ሰራዊት እንደሆነ በግልጽ ያስመሰከረበት ነው።

ይህ ሁኔታ ሁለት እውነታዎች አስቸኳይ ውሳኔን እንደሚጠይቁ ያሳያል።

አንደኛው በሀገርና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ክህደት የፈጸመው ህወሀት በፖለቲካ ፓርቲነት ሊቀጥል የሚችልበት አግባብ በፍጹም እንደሌለ ነው። የፖለቲካ ፓርቲነትን ሽፋን የተጠቀመው ለማስመሰያ እንጂ፣ የራሱ ወታደራዊ ሀይል ያዘጋጀ ፣ በሀገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲውች ሀግ ክልክል የሆነን ተግባር አጣምሮ የሚጓዝ ወታደራዊ ድርጅት ሰለሆነ በፖለቲካ ፓርቲነት ሊታይና ሊቀጥልም አይገባውም።

የደርጅቱ ተራ አባላት የተለያየ የፖለቲካ ድርጅት አባል በመሆን ራሳቸውን በሚፈልጉት ፓርቲ ውስጥ ተቀላቅለው ሀሳባቸውን ፤ሊያራምዱ ግንዛቤን መውስድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ህወሀት እንደድርጅት የፈጸመው ወንጀል እጅግ የከፋ  ከሀጋዊ የፖለቲካ ፓርቲምተግባራት ጋርም  እጅግ የሚጻረር በመሆኑ  በህግ መታገድ ብቻ ሳይሆን በህግ መፍረስም ይኖርበታል ማለት ነው።

ሁለትኛው  ህወሀትና ልዩ ሀይሉ የሰሩት  የሀገር ሰራዊትን ማጥቃት ታላቅ ወንጀል ነው፡ ይህን ያደረግ ድርጅት ምን ጊዜም ህጋዊነት ተስጥቶት ሊቀጥል አይገባም። ይህ የድርጅቱ ጥቂት መሪዎች ያደረጉት ስህተት ሳይሆን ድርጀቱ እንደድርጅት መክሮ ዘክሮ ከቅርብም ከሩቅም ተጠራርተው፣ በተቀነባባረ ሁኔታ ሆን ተብሎ የተፈጸመው ነው። ሰለሆነም ወንጀለኞቹ መሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ደርጅቱም  ጭምር ነው። በመሆኑም ይህ ልዩ ሀይልም ሙሉ በሙሉ መፈረስ ብቻ ሳይሆን በቀጣይም ሊቋቋም አይገባውም፡ ትግራይ የሚያስፈልጋት አቅሙ የተመጠን ህግ አስከባሪ ፖሊስ እንጂ ስራዊት ሊሆን አይገባውም።

ወንጀለኛ ፖለተካ ድርጅትን በህግ አግባብ የማገድና የማፍረስ  ተመሳሳይ ጉዳይ በሱቨየት ህብረት ውስጥም ተከስቷል። በአውሮፓውያን አቆጣጠር በኦገስት 1991፣ በሶቨየት ሀብረት ኮሚኒስት ፓርቲ አቀናባሪነተ በሰራዊቱ ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር በመመሳጠር ለውጡን ይመሩ የነበሩትን ሚካአኤል ጎርባቹቭንና መንግስታቸውን ለመገልበጥ ሙከራ አደረጉ። ይሀን የቅልበሳ ሙከራ በመቃወም ሀዝብ ሆ ብሎ ወጣ፡፣ ቦረስ ያልሰን የተባሉ የራሲያ ሪፐሊክ የውቅቱ ፐሪዚዳንትም ሀላፊነት ወስደው ተቃውሞውን በማሰተባበር መፈንቅለ መንግስቱን በአጭር ጊዜ  አከሽፉት።

ይህን ተከትሎም የረዥም ጊዜ ታሪክ የነበረው ኮሚኒስት ፓርቲ ሀገውጥ ተብሎ በመንግስት ተወስነ። ከአንድ ወር በኹላም ይህ ውሳኔ በፓርላማው ጸድቆ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ ተደርጎ ሞቶ ተቀበረ።

በአሁኑ ሰአት በሩስያ ውስጥ የኮሚኒስት ፓርቲ በህጋዊነተ ይንቀሳቀሳል፡ ሆኖም ይህ ፓርቲ በአዲስ መልክ የተዋቀረና የተመዘገበ እንጂ  የመንግስት ግልበጣ ያካሄደው ተቋም ተቀጣይ አካል አይደለም።

በሀገራችንም  መንግስትም ፓርላማውም ሆነ የፓርቲዎች ጉዳይ የሚመለከተው ምርጫ ቦርድ በዚህ አኳያ የማያዳግም ህጋዊና አስቸኳይ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ማመንታት ይብቃ፡ ማመንታት  የት እንዳደረስን በበቂ አይተናል። ለማስታመም ጊዜ አለ ለውሳኔም እንደዚሁ።

አክሊሉ ወንድአፈረው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *