jawar-bekele-lemma
Analysis News

የጃዋር ቅዠትና የበቀለ የተላላኪነት ፖለቲካ – የለማ ሃዲድ መሳት

አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ተፈተው አሜሪካ እስከገቡ፣ ከአሜሪካም ሜኖሶታ ከጃዋር ጋር ጫጉል ቆይተው እስኪወጡ የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን የሚያውቁ፣ የሚያመልኩትን አምላክ ተግሳጽ መስማት የሚችሉ፣ በዙሪያቸውም ሆነ በሩቅ ባሉ ክብር ያላቸው ፖለቲከኛ እንደነበሩ ስምምነት አለ።

ይህ ስምምነት ነበር አቶ በቀለን በኢትዮጵያ ለውጥ ቢፈጠር ሁሉንም አቻችለው ወደjawar-bekele በጎ መንገድ እንዲመሩ ከሚታሰቡት መካከል ቀዳሚው አድርጓቸው የነበረው። የዲሲ ነዋሪው ገመቹ በቀለ ከሜኖሶታ “ተሃድሶ” ይለዋል ተመርቀው ሲወጡ “የአንጎል ቀዶ ጥገና ተድርጎላቸዋል” ባይ ነው።

የበቀለ ገርባና የጃዋር ወዳጅነት – የሸዋ ፖለቲካን መግዛት

በአብዛኛው የቄሮ ትግል ተዋናያንና መሪዎች የማዕከላዊ ኦሮሚያ ልጆች ናቸው። የሜጫና ቱለማ ትግል ሸዋ ተወልዶ በጋመ ጊዜ ወደ ወለጋ ተወስዶ ሲርመጠመጥ ከአርባ ዓመት በላይ በመቆየቱ የሚበሳጩ፣ የቄሮ ትግል ማዕከላዊ ኦሮሚያ ላይ ሲተከል “ትግሉ ወደ ትክክለኛ ሰፈሩ ተመለሰ” በሚል አስተያየት የሚሰጡ ጥቂት አልነበሩም። የተባለው አልቀረም ትግሉ ከሌሎች ጋር ተጋምዶ በድል አበቃ።

ጃዋር ትግሉን በሚዲያ እንዲያስተባበር በቅጥር የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክን ሲመራ ጎን ለጎን ኔት ወርኩን የግል አደረገ። ይህ የሆነው ለውጡ የማይቀር ስለሆነ ወደ ስልጣን ለማኮብኮብ መሠረቱን ለመጣል ነበር። የትህነግ መወገድ እውነት እየሆነ ሲሄድ ጃዋር በሚዲያ ያወጀውን ንግሥናውን ተግባራዊ ለማድረግ ሸዋ ላይ መልህቅ መጣል እንዳለበት አመነ። ጉዲና ኃይሉ እንዳለው ለጃዋር የጥድፊያ ዕቅድ በቀለ ገርባ የተመቹ ሰው ሆነው ተገኙ።

“የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”

jawar-merera-bekele

በሜኖስታ ጃዋር መኖሪያ ቤት ጃዋር በቀለ ገርባን ብቻ ሳይሆን ፓርቲያቸው ኦፌኮንም ተጣባው። የኦፌኮ መሪ ዶ/ር መረራ ላይ በድብቅ ሤራ ተገምዶ ኦፌኮን የመግዛቱ ሩጫ ተጀመረ። በቀለ ገርባ ይህንን አደራ ይዘው አገር ቤት ገቡ። ጃዋርም በከፍተኛ ደረጃና ባልተለመደ መልኩ ለመረራ ፓርቲ ሰፊ የአየር ሰዓት ይሰጥ ጀመር። ኦፌኮና መሪዎቹ በኦኤምኤን ቤተኛ ሆኑ።

ጃዋር በአዲስ አበባ  – ሁለት መንግሥት

ትግሉን መረጃ በማደራጀት በሚዲያ እንዲመራ የተቀጠረው ጃዋር በተገኘው አጋጣሚ የቀድሞው ኦህዴድ መዋቅር ውስጥ የመፈንጨት ዕድል አጋጥሞት ስለነበር አዲስ አበባ እንደገባ “ሁለት መንግሥት አለ” የሚል መፈክር ጀመረ።

ወደ ፖለቲካ ሲመጣ “በሜንጫ አንገት እንቆርጣለን” በማለት የሃይማኖት ታፔላ ያነሳው ጃዋር ሸዋ ላይ ልብ የሰጠው ባለመኖሩ በአቶ በቀለ ገርባ አማካይነት ኦፌኮን ጭራውን እየቆላ ገንዘብ አሳይቶ ተቀላቀለ። ፖለቲካ ለምኔ ሲል የነበረው ጃዋር ያልተረጋጋው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ በፈለፈላቸው ሚዲያዎች እንዳሻው መርዝ እየረጨ አገሪቱን አዛላት።

ጎን ለጎን መርራና በቀለን እየያዘ ኦሮሚያን በመዞር የመንግሥትነት ህልሙን ያውጅ ጀመር። በዚህ ዘመቻ ውስጥ ድንገት ከታዩት አቶ ድንቁ ደያስ በቀር ሌሎቹ ሂደቶች የዕቅዱ አካላት ስለነበሩ በኦፌኮ የመካከለኛ አመራሮች ዘንድ ውስጥ ውስጡ ቅሬታ ይሰማ ጀመር።

ድንቁ ደያስና ጃዋር

ቅሬታው ሳይሰፋና ወደ ውጭ ሳይወጣ ጃዋር ኦፌኮን ገዛው። ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት አሁን በቀለና ጃዋር መታሰራቸው እንጂ ቅሬታው ይፈነዳ ነበር። የዚህ ቅሬታ ድምርና እነጃዋር እስር ቤት ሆነው መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር በሚል ድርጅቱ ምርጫ መወዳደር እንዳይችል መደረጉ ቅር ያሰኛቸው “መረራ ዛሬ ላይ አምቦ እንኳን መመረጥ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል” እያሉ ነው።

ጃዋር ኦፌኮን ከገዛው በኋላ በኦፌኮ ታሪክ ተሰምቶ የማያውቁ የፖለቲካ ጨዋታዎች ተጀመሩ። ” የዲቃላ ፖለቲካ” ሚስትና ባልን፣ ቤተሰብን እንዲያፈርስ የሚያዝ ሆኖ መጣ። ይህ ሲባልና መድረክ ላይ ሲቀነቀን መረራ፣ ጃዋርና በቀለ ገርባ ሲስቁና በኩራት የትግሉ መሪ መሆናቸውን በሚያሳይ የእብለት ኩራት ውስጥ መሆናቸውን በሚያጋልጥ ገጽታ በቲቪ ይታዩ ጀመር።

የ”ዲቃላ” ጨዋታው ጠንክሮ ብሄር እየተጠቀሰ “አትግዛ፣ አትሽጥ፣ አታናግር፣ አትመልስ…” በሚል በቀለ ቀለም ቀቢ ሆኑ። ይህኔ ኦፌኮ የፖለቲካ ሞት ሞተ። አቶ በቀለም ቆመውበት ከነበረው የፖለቲካ ሞት ጫፍ ተንሸራተው አሁን ያሉበት ቦታ እንደገቡ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ያምናሉ። እርሳቸውም ቢሆን ጸጸት እንደጀመራቸው እየተሰማ ነው። አስከሬን አግቶ ስልጣን ለመያዝ እስከመገዳደል መድረስ ከሃይማኖተኛው በቀለ ከቶውንም የሚጠበቅ ባይሆንም ከእነ ቤተሰባቸው አደረጉት። ጃዋር የትኛውን የልቦናቸውን ብሎን ፈቶ እንደጣለው ባይታወቅም በቀለ እንዲህ መሆናቸው በርካታ የሚያውቋቸውን ሰዎች ዛሬ ድረስ የገሃድ ታሪክ መስሎ አይታያቸውም። በተለይ ከእምነት መሠረታቸው አንጻር ሲታይ ጉዳዩን ዝቅጠቱ የበለጠ ያጎላዋል።

ለማ መገርሳና በቀለ

ለማ መገርሳና በቀለ ገርባ ወዳጅ እንዲሆኑ ሲደረግ ሆን ተብሎ እንደነበር ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ይናገራሉ። የአንድ አካባቢ ሰዎች እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሁለቱ ፖለቲከኞች በተፈጠረው አጋጣሚ ለመግባባት ጊዜ አልወሰዱም።

አቶ በቀለ ጃዋር ባስቀመጠው ሥሌት መሰረት ለማ መገርሳን ከኦህዴድ ለመለየትና አዲስ በሚቋቋም የኦሮሞዎች ድርጅት ውስጥ መሪ እንዲሆኑ አስማሙ። ብልጽግና የሚባል ፓርቲ እንዳይቋቋም አቋም እንዲይዙና ቢቻላቸው ኦህዴድ ውስጥ ይህን አካሄድ የሚቃወሙ ኃይሎች እንዲበረክቱ የቤት ሥራ እንዲሰሩ ሆኑ። ለሳቸው ይህ የቤት ስራ እየተሰራ በጃዋር ሚዲያዎች “ሚስጢር” ወይም “ሰበር ዜና” እየተባለ የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ውጤቶች ዜና እንዲሆኑ ይደረግ ነበር።

ሙሉውን ለማንበብ

ምንጭጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *