embargo
Articles News

የምራባውያን ማዕቀብ በኢትዮጰያ ውስጥ  ጦርነትን ያስቆማል? ሰላምንስ ያስገኛል? ወይንስ ይበልጥ አለመረጋጋትን ይጋብዛል?

ከአክሊሉ ወንድአፈረው (ethioandent@bell.net)

ጥቅምት19: 2014(October 29, 2021)

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባይደን መንግሥት ሥልጣን በያዘ በመጀመሪያው አንድ መቶ ቀናት ውስጥ በአፍርካ ውስጥ ለአሜሪካ የረጅም ጊዜ ወዳጁ በሆነችውና በአፍሪካና በአጠቃላይም በጥቁር ሕዝቦች ደረጃም ታላቅ ትርጉም ባላት ኢትዮጰያ ላይ በትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰው ግጭት አሳስቦኛል በማለት በኢተዮጵያ መንግሥት እንዲሁም በአማራ ክልላዊ አስተዳደር መሪዎች ላይ የአሜሪካ መግቢያ የጉዞ ፈቃድ (ቪዛ) ማዕቀብ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

በመቀጠልም የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ የተጠየቀውን ካላሟላ ብድርን የፀጥታዕ ርዳታንና ሌሎችም ያልተጠቀሱ ማዕቀቦች አሚሪካ ተግባራዊ እንደምታደርግ ተገልጧል። ይህ ብቻ አይደለም የአሜሪካ ወዳጅ ሀገሮች ተመሳሳይ ማዕቀብ እንዲያደርጉም አሜሪካ ጥሪ አድርጋለች።

ከላይ  የተጠቀሱት የማዕቀብ እርምጃዎች አሜሪካ የምትፈልገውን ግብ ማሳካት ያስችላታልን፧ ማዕቀቡ በአጠቃላይ የሚኖረው እንደምታስ  ምን ይሆናል፧የሚለውን በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለሁ።

የማዕቀብ መሠራተዊ ዓላማዎችና ግጭትን በማስወገድ ረገድ ያለውጤታማነት

ማዕቀብ ብዙውን ጊዜ ሁለት ዋናዋና ግቦችን ማስፈጸሚያ መሣሪያ ነው።አንዱ የመንግስታት የውጭ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ሲሆን ( as tools of foreign policywww.gao.gov/assets/nsiad-92-106.pdf) ሌላው ደግሞ ዓለም አቀፍ ሕግን የማስከበሪያ መሣሪያ(as tools of international law enforcementAn Analysis of the Effectiveness of Sanctions as a Law Enforcement Tool in International Law: A Case Study of Zimbabwe from 2001 to 2013 (scirp.org)) ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥታት ማዕቀብን ፖሊሲን ለማሰለወጥ ብቻ ሳይሆን መንግሥታትን ለማናጋትም እንደሚጠቀሙበት በግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ተገቢ ይሆናል።

የኤኮኖሚ ማዕቀብ ግጭትን በመከላከልና በማስወገድ የተፈለገውን ውጤት ያመጣል ወይስ አያመጣም፧የሚለውን ከግምት ባለፈ በተጨብጭ መረጃ ያጠኑ ምሁራን እንደሚያሳዩት ከ1914 እስከ  (እአአ) የተመዘገቡ አንድ መቶ አስራ አራት (114) ያክል የኤኮኖሚ ማዕቀቦች የተጣሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 34% ብቻ ውጤት ማግኘታቸውን ያሳያሉ።ከ1973 ዓም ወዲህ የተካሄዱ የኤኮኖሚ ማዕቀቦችን ስንመለከት ደግሞ ግባቸውን መቱየሚባሉት 20% ብቻ መሆናቸውን እናያለን።

ይህም ሆኖ  ማዕቀብ የሚጠበቀውን ግብ ለመምታት ብዙውን ጊዜ ከ14 እስከ 16 ዓመታት እንደሚወስድ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ።

ይህ አጠቃላይ የአለምአቀፍ ዕቀባን ውጤታማነት ደካማ መሆን የሚያመለክት ሲሆን በአሜሪካ የሚካሄድ የተናጠል ዕቀባ የሚኖረውን ውጤታማነት የመረመሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የውጤታማነቱ መጠን ወደ 21% ዝቅ ያለ መሆኑን ነው።

ይህ ሁሉ ድክመት እንዳለ ሆኖ፣ማእቀብ መጣል ግጭትን ለማስወገድ ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ የሚካሄደውን ግጭት ሰረመሰረትና፣ግጭቱ የተከሰተበትን አውድ እንዲሁም የማህበረስቡንና የግጭቱ ተሳታፊዎችን ታሪክና ሰነልቦና በትክክል መረዳት ከዚህም ጋር ተያይዞ በምድር ላይ የሚገኘውን እውነታ የሚያንጸባርቅ የመፍተሄ አማራጮችን ማቅረብን የግድ ይላል።

የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጰያ ላይ የጣለውን እና ወደፊትም እጥለዋለሁ እያለ የሚናገረውን ማዕቀብ ስንመረምርም ቢያንስ እነዚህን መሠረታዊ ግንዛቤዎች በዕይታችን ውስጥ ይዘን ሊሆን ይገባል።

የአሜሪካና የአውሮፓ መንግሥታትን ማዕቀብ ለማድረግ አስገደደን የሚሉት ምኑን ነው?

ከላይ ከተጠቀስው አኃዝ ባሻገር የአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ ግቡን ይመታል ወይስ አይመታም፧ብሎ ለመመዘን በመጀመሪያ የማዕቀቡ ዋናዋና ምክንያቶችን ምንድን ናቸው የሚለውን መመርመር፣በመቀጠልም ከተለያዩ ሀገራት ልምዶችና ጥናቶችን በማየት አንድን ማዕቀብ ግቡን  መታ የሚባለው ምን ምን ሲሟላ ነው የሚለውን መመልከት ያሻል።

የአሜሪካ ማዕቀብ በዋናነት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና በአማራ ክልል የፖለቲካና ወታደራዊ መሪዎች ላይ ያነጣጠረየ አሜሪካ መግቢያ ፈቃድ ክልከላና  ወደፊት ሊከተል የሚችል የኤኮኖሚ ዕቀባ ናቸው።

ለዚህም ዋናዋና ምክንያቶች የተባሉትና የኢትዮጵያ መንግሥት አቋሙን እንዲለውጥ ለማድረግ የተፈለጉት ጉዳዮች፦

ህወሓትን ወደ ፖለቲካ ምኅዳሩ መመለስ (አጠቃላይ የተለያዩ ፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተ የብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር ይላሉ)፡

  1. ህወሓትን ወደ ፖለቲካ ምኅዳሩ መመለስ (አጠቃላይ የተለያዩ ፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተ የብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር ይላሉ)፡
  2. የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ከወልቃይት፣ጠገዴ፣ፀለምት እንዲሁም ከራያ እንዲወጣ
  3. በትግራይ ውስጥ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ መድረስና የዕርዳታ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ የተመቻቸ ሁኔታን መፍጠር የሚሉት ናቸው።

ህወሓትን  ወደ ህጋዊ ፖለቲካ ምኅዳር መመለስ

ዕቀባ  ግጭትን ለመፍታት ውጤታማ መሳሪያ እንዲሆን በቦታው የሚታየውን ግጭት ከስር መሰረቱ በትክክል የተገነዘበ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የመፈትሄ አማራጮችን ማቀረብ አስፈላጊይሆናል።

የኢትዮጰያ ሕዝብ የሀወሓትን አገዛዝ ቢያንስ ላለፉት 28ዓመታት በጥልቀትያውቀዋል።በሀገራችን ውስጥ ለተፈጠረው መጠነ፡ሰፊ ግፍ በደልና ሰቆቃ በዋናነት ተጠያቂው ሀወሓት እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል።የሀወሓትን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ የተከፈለው ዋጋ በጣም ከባድ ሲሆን ለተፈጠረው የግፍ ተግባርም እስካሁን ከህወሓት በኩል ተጠያቂ የሆነ ግለስብም ይሁን አካል የለም።ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በህወሓት ላይ እጅግ ከፍተኛ ቅሬታ ምሬትና ጥላቻም አለው፡:

የኢትዮጰያ ሕዝብ በዚህ መልክ የሚመለከተውን ሀወሓትን እንደገና ወደ ፖለቲካ ምኅዳሩ ካልመለሳችሁ ማዕቀብ እጥላለሁ  ማለቱ፣በሕዝባችን ዘንድ እጅግ ታላቅ ቅሬታን አስከትሏል። አሜሪካ በፍጹም እኛን የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም ነገር አታደርግም የሚለውንም ስሜትም ያጠናክረዋል።

ሀወሓት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የገባበት የ 27 አመት  ቅሬታ ምሬትና ጥላቻ ወደ ፖለቲካ ምህዳሩ እንደገና እንዲመለስ ማድረኝ   እጅግ አስቸጋሪያ ደርግዋል።ከዚህ በተጨማሪም አሁን የሚካሄደው ውጊያ የተቀሰቀሰው የህወሓት የክልል ጦር በሰሜን ዕዝ ላይ ባደረሰው ቀጥተኛ ጥቃት ምክንያት በመሆኑ፣በሕዝቡም ሆነ በሠራዊቱ ውስጥ በህወሓት ላይ ያለው ስሜት እጅግ የከፋ ብቻ ሳይሆን  እንደ አደገኛ ሀገር ከሀዲም እንዲታይ አድርጎታል።

ይህ ሁሉ ተደምሮ ሲታይ የዶክተር አብይመንግሥት በአሜሪካ የሚሰነዘረውን “ከህወሓትጋር ተደራደሩ ወደ ፖለቲካ ምህዳሩም መልሱ”  የሚለውን ጥያቄ እንዲቀበል የሚገፋፋቸው ነባራዊ ሁኔታና የህዝብ ድጋፍ (  Public buy-inc) እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን እናያለን።በመሆኑም ይህ የአሜሪካ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ27 ዓመታት በሀወሓት የደረስበትን ግፍ እና የግጭቱንም ተፋላሚዎች ሚና በአግባቡ በግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ሰለሆነ ገና ከጅምሩ የመሳካት እድሉን እጅግ የመነመነ ግጭቱንም ለመፍታት የሚኖረውንም  አስተዋጻኦን እጅግ ዝቅተኛ ያደርገዋል።

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እንዲሁም ፋኖ ከወልቃይት፣ከጠገዴና ከፀለምት እንዲሁም ከራያ እንዲወጣ

የወልቃይት ጠገዴ ፀለምትና ራያ የማንነት ትግል ህወሓት መራሹ ኢሀአዴግ ገና ወደ ሥልጣን እንደመጣ ጀምሮ የነበረና ያለ እንዲያውም በአማራ ክልል በህወሓት መራሹ ኢሀአዴግ ላይ ለተካሄደው ታላቅ ተቃውሞና አልገዛም ባይነት በዋናነት ሊጠቀስ የሚችል አንቀሳቃ ሽ ጉዳይ ነው።

ይህ ትግል እንዲሁ ድንገት ከአየር ላይ እንደ ዱብ እዳ ወርዶ መካሄድ የጀመረ አቅጣጫና ዓላማ የሌለው ሳይሆን በአካባቢው በሚኖረውን ሕዝቡ ፍላጎት በመጣስ በጉልበት ወደ ትግራይ ከተካለለበት ጊዜ ጀመሮ የተካሄደ ፍትኅን ና ማንነትን መሠረት ያደረገ ትግል ነው።

የአማራ ህዝብ ከቀደምት ትውልድ የወረሰውን በክብር የመያዝና ለመጭውም ትውልድ ማስተላለፍን ከፍተኛ ክብር  የሚሰጥ የስነ ልቦና ውቅር ያለው ህዝብ ነው፡፡አንድ እርምጃ ሲወስድም ዛሬን ብቻ ሳይሆን ትላንትን እና ነገን በታላቅ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡

ይህ ብቻም አይደለም ቢያንስ 30 ዓመታት ባስቆጠረው  የአካባቢው ትግል  ውስጥ በህወሓት አገዛዝና ሠራዊት እጅግ ብ ዙዎች ተገድለዋል፣  በርካቶች የት እንደገቡ አልታወቀም፣ሌሎች ደግሞእንዲሰደዱሲደረግ፣ንብረታቸውም ተወርሶ ለሀወሓት  ወታደሮችና አባላት ተሰጥቷል።አሁንየ ተከሰተው የአማራ ልዩሀይልና ፋኖ በቦታው መገኘትም እነዚህንና ሌሎችንምታሪካዊ ዳራዎችና ስነልቦናዊ እውነታዎች መሠረትያደረገነው።

ይህ በምድር ላይ ያለው እውነታ ሆኖ ሳለ የአካባቢውን ጉዳይ አሁን ከተፈጠረው የህወሓት መመታት ጋርብቻ አያይዞ፣የአማራ ተወላጅ ታጋዮችን እንደ ባዕድ ኃይሎች በመቁጠር ከቦታው ይውጡ ማለት ቀድም ሲል በህወሓት የተካሄደውን የጉልበት ሰራ ትክክል ነው ብለው ከሚያምኑ ውጭ ለሌሎች ትርጉም የሚሰጥ አይደለም።

ይህ የምእራባውያኑ አቋም  በብዙዎች እይታ ገና ከጅምሩ የግጭቱን ታሪካዊ ዳራ፣ያላጤነ ከተፋላሚዎችን ሰነልቦናና ከእውነታም ጋር ያልተገናዘበ ሆኖእንዲታይ ያደረገ ነው፡፡

ይህም በመሆኑ የአማራ ክልል ልዩሀይልና ፋኖ ከአካባቢው ይውጣ የሚለው የአሜሪካ ጥያቄ የሕዝብን መሠረታዊ የፍትኅ ጥያቄ ያላተገነዘበ፣ቀደም ሲልም የወልቃይት ጠገዴ ና  ራያ ህዝብ የደረስበትን ስቃይና በደል እውቅና ያልሰጠ የአማራ ህዝብን ሰነልቦናም ያላገናዘበ ስለሆነ  በህዝብ የሚታየው በኢፍትኅዊነትና ተበዳይና ተጎጂውን ሕዝብ እንደገና መጉዳትና ለመበደል(revictimization ) ረደርጎ ነው።

፡የአሜሪካን የሰላም እቅድ ይህን በደልና ግፍ እውቅና መሰጠቱን ከቶውንም አያመለክትም እንዲያውም ከአክባቢው ውጡ ካልሆነም ማእቀብ እንጥልባችኳለን  የሚለው ማስፈራሪያ  የሚያሳየውተጻራሪውን ነው፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ ሲመረመር ደግሞ ህወሓት ከትግራይም አልፎ በአማራና በአፋር ክልል ገብቶ እጅግ ሰፊ ቦታዎችን በሀይል በያዘበትና ከአንድ ሚሊዮን ተኩል  በላይ የሆነ ህዝብን ባፈናቀለበት ተቋማትና የክዝቡን ንብረቱንም እያወደመ በሚገኝብት ሁኔታ አሁንም የአማራ ሀይል ከአካባቢው ይውጣ የሚለው ገፊት እጅግ መሰመሩን የሳተና ህወሀትን ለማጠናከር የቀረበ ሆኖ ይታያል፡፡

በዚህ አንፃር የአሜሪካን መንግስት ጥያቄና ግፊት  የነዶከተር አብይን መንግሥት ከሕዝቡ ፍላጎት በተፃራሪ እንዲቆም የሚገፋፋና ክህዝብም የሚነጥለው ሰለሆነ መንግስት የቀረበውን ጥያቄ የሚቀበልበት እድል እጅግ የጠበበ ሲሆን ከተቀበለም ከድጡ ወደ ማጡ እንዲጓዝ የሚያደርገውይሆናል፡፡

እነዚህን ሁኔታዎች ስናገናዝብ የአማራ ኃይል ከተጠቀሱት ቦታዎች ይውጣ የሚለው የማዕቀቡአንዱ ጥያቄ (demand ) ገና ከመጀመሪያው የከሽፈ ቅራኔ ለመፍታትም ከሚኖረው አስተዋጻኦ ይልቅ የማባባስ እድሉ ክፍ ያለ እንደሆne እንገነዘባለን። ከዚህ በተጨማሪም አማራን  ማህበረስብ እንደ ወራሪ የሚያቀርብ በመሆኑ ይህን ህዝብ ለበለጠ ጥቃት ሊያጋልጠው ህወሀትንም የሚያካሂደውን ጦርነት ፍትሀዊና አለምአቀ ፍድጋፍም ያለው አድርጎ በማቅረብ ጦርነቱን ከማብረድ ይልቅ ይበልጥ የሚያበረታ  ያደርገዋል፡፡

በትግራይ ውስጥየ ዕርዳታ ተደራሽነትን እውን ማድረግ

ማዕቀቡ የተጣለበት አንዱ ምክንያት የአሜሪካ መንግሥት መደረግ አለበት እያለ እየደጋገመ የሚያነሳው በትግራይ ውስጥ የእርዳታ ተደራሽነት ጉዳይ ነው።ይህ በርግጥም በሁሉም የሚደገፍ አቋምነ ው።በዚህ አኳያ ዶክተር አብይን የፈለገውን ያክል መቃወም ቢቻልም የኢትዮጰያ መንግስት ሆን ብሎ ለትግራይ ሕዝብ ዕርዳታ እንዳይደርስ አደረገ ብሎ መክሰስ ግን መሰረት የሌለው ጉዳይ ነው።

ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢትዮጰያውያን በላይ አሜሪካም ሆነ አውሮፓውያን ይቆረቆራሉ ብሎ ማስብ እጅግ የተሳሳተ ነው። በትግራይ የሚታየው ግጭት ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በፍጥነት የሚለዋወጥና በዚሁ ምልክ ጦርነቱን ለማስቆምም ሆነ የሰባዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማሳለጥ ፈጣን እና ተመጣጣኝ እርምጃን መውሰድ የሚጠይቅ ነው፡

የእርዳታን ተደራሽነት አስመልክቶ በምድር ላይ የሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ የአሜሪካን መንግስት ቀ ደም ሲል ያቀረባቸው ቅድመሁኔታዎች፣ የማእቀቡ ማስጠንቀቂያ ከተገለጸበት ጊዜ ወዲህ ብዙ የተለየ ነው፡፡

በዋናነት  መንግስት ሰራዊቱን ከመላ ትግራይ ሙሉ በሙሉ አስውጥቷል ይህም በመሆኑ በትግራይ ውስጥ እርዳታ ተደራሽ እንዳይሆን አድርጓል በሚል መንግስት ሊወቅስ የሚያስችል ምክንያት  የለም፡፡የኤርትራ ሰራዊትም ቢሆን ትግራይን ለቆ ወጥቶ ሰፍሮ የሚገኘው በራሱ ግዛት ውስጥ ነው፡፡

ሶስተኛ የህወሀት ሰራዊት ከትግራይ አልፎ በአጎራባች አፋርና የአማራ ክልል ሰራዊት አስገብቶ በወታደራዊ ሀይል ቦታ ተቆጣጥሮ የጅቡ ቲምስመርን ለመቆጣጠር እና ወደ መሀል ሀገር ተጨማሪ የመስፋፋት ሙከራም እያካሄደ እንደሆነ እየታየ ነው፡፡

የህወሀት ሰራዊት አፋርና ወሎ በመግባቱም የአካባቢው ጸጥታ ተናግቶ በዚህ መስመር ወደ ትግራይ ይጓዝ የነበረው እርዳታ እጅግ እንዲደናቀፍ ሆኗል::

ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ከኢትዮጰያ በኩል እርዳታ ይዘው ወደ ትግራይ የተጓዙ ከ400 በላይ ከባድ የጭነት ማመላለሻ መኪናዎች እንዳልተመለሱ ብቻ ሳይሆን በትግራይ ውስጥ የህወሀት ሰራዊትን ለማመላለስ እየተጠቀሙብት እንደሆነ ብዙ በምስል የተደገፉ አስተማማኝ መረጃዎች ይፋ ሁነዋል፡፡

ሰለዚህም የእርዳታ ተደራሽነትን ምክንያት አድርጎ በኢትዮጰያ መንግስት ላይ ያነጣጠረው  የማእቀብ እቅድ ሙሉ በሙሉ መነሻ መረጃው በአሁኑ ሰአት በምድር ላይ ከሚገኘው እውነታ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ  ጦርነቱን ለማስቆም የሚኖረው እርባና ትርጉም የሚሰጥ እይደለም፡፡

የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ ክልከላ ምን ትርጉም ይኖረዋል?

የተለያዩ ጥናቶች የሚያሳዩት በግለስቦች ላይ ያተኮረ የቪዛም ሆነ ሌላ ማዕቀብ ውጤት የሚኖረው የአንድ ሀገር ሀብት ናንብረት በጥቂት ግለስቦች በተለይም በመሪዎቿ እጅ የተሰበስበ ሲሆን ነው።ለምሳሌ አሜሪካናወዳጆቿ አንዳንድ ከእነሱ ጋር ጤናማ ግንኙነት የሌላቸው ግን ደግሞ በሀገራቸው ባንኮች ገንዘብ  ያካበቱትን መሪዎቸና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ላይ ማዕቀብ በማደረግ በየትም ቦታ ያላቸው ንብረት እንዳይንቀሳቅስ በማደረግ አስጨንቀዋቸዋል።

ይህ ሁኔታ አሁን ባለው የሀገራችን መሪዎች አኳያ ሲመዘን የሀገር ሀብትና ንብረት በጥቂት ባለሥልጣናት እጅ የተከማቸ ባለመሆኑ የማዕቀቡ ማስፈራሪያ ተጸና ፈጣሪነት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

ኢትዮጰያን ለ27 ዓመታት ያለማንም ተቆጣጣሪ መዝብረው በስሜን አሜሪካ አውሮፓና በተለያዩ የአረብ ሀገሮች ባንኮችና ከተሞች ውስጥ ገንዘብም ሆነ ሌላ ንብረት ያከማቹት በዋናነት የህወሓት ባለሥልጣኖችና ቤተስቦቻቸው ናቸው። ለዚህ ደግሞ መንግሥታዊ ምዝበራን የሚያጠናውን የዓለምአቀፍ ተቋም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል (transparency International) ሪፖርቶች ማየት በቂ ይሆናል።

በህወሓት አገዛዝ የመጨረሻ ዓመት ማለትም በ2017 (እአአ) ኢትዮጰያ በመንግሥታዊ ምዝበራና ንቅዘት ከ 180 ሀገሮች 107ኛ ነበረች።

ከዚህ እንፃር ይ ህማዕቀብ ዶክተር አብይን ጨምሮ አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኙትን ባለሥልጣኖች በምንም መለኩ የማይጎዳ ትርጉም የለሽ ማዕቀብ ነው።

በአጠቃላይ ሲታይ በአሜሪካ የተጣለው ማዕቀብ የኢትዩጵያን ፖለቲካዊ፣ታሪካዊ ሰነልቦናዊ እንዲሁም የመሪዎቿን ኤኮኖሚያዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው።ይህም በመሆኑ በማዕቀብ ጣዮቹ በግልጽ የተነገረው ግብ ውጤት የማስገኘ ትዕድሉ እጅግ ዝቅተኛ ነው።

ማዕቀቡ ምን ያስከትላል ማንንስ ይጎዳል?

የአሜሪካ ማዕቀብ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ወደ አሜሪካ የመግቢያ ቪዛ ከመከለከሉ ባሻገር ከዓለም ባንክና አይኤምኢፍ (IMF) ለአትዮጰያ የሚሰጡ ብድሮችን፣የፀጥታና መስል ድጎማዎችን እንደሚያካትት  ተነግሯል።

ይህ ዕቀባ የሚጎዳው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ይልቅ በተፃራሪው ህዝቧን ይሆናል። ከቪዛ ማዕቅብ ባሻገር ያለው ሁሉ እንደተባለውም የሚቀጥል ከሆነ የሀክምና፣የእርሻ የምርት መሣሪያዎች የመድኃኒትና የምግብ አቅርቦትና የመሳሰሉትም መሠረታዊ የልማት አውታሮች ላይ ታላቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል።

ከዚህ አልፎም የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ አቅም ስለሚያዳክም ኢትዮጵያ ልታከሂደው የ ምታስባቸውን ታላላቅ የልማ ትሥራዎች፣የትራንስፖርት መስፋፋት፣አውራ ጎዳናዎች መገንባት፣ፋብሪካዎችን መክፈት…ወዘተ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ እንደማይቀር የተለያ ዩሀገሮች(ክዩባ፣ቬንዩዜላ፣ሄይቲ …ወዘተ) ልምዶች ያስተምሩናል።

ይህ ግን የመአቀቡ ጠርዝ አሜሪካዊ ናምናልባትም አውሮፓያዊ ብቻ በሆነበት በዚህ የተናጠል እርምጃ ኢትዮጰያን  ከአሜሪካ ያጣችውን ከሌላ የአለም መንግስታት ልታገኝ የምትችልበት  ሁኔታ እጅግ ስፊ ነው፡፡፡ቻይና ቱርክ፣ህንድ ራሽያና አንዳንድ የገልፍ ሀገሮች የአሜሪካ ከኢትዮጰያ ጋር መቃቃር የሚፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት አኮብኩበው እንደሚገኙ ግልጽነው፡፡

ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳ ማእቀቡ የሰባዊ እርዳታን አያጠቃልልም ይባል  እንጂ፣ማእቀቡ ያሚያሳድረው የኢኮኖሚ ተጸእኖ ውጤት በተለይም በደካማው የህብረተስብ ክፍል ላይ እጅግ አስቃቂ ሊሆን ይችላል።ለምሳሌ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ1990 እስከ 2003 በኢራቅ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይሳ ይሆን በኢራቅ ሕዝብ ላይከፍተኛ ስቃይንያ ስከተለ እንደነበር የሀገሪቱን ሕፃናት ሞትበ 100% እንዲጨምር እንዳደረገ በአጠቃላይም  ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ600-800 ሺህ የሚገመቱ ሕፃናት በማዕቀቡ ምክንያት በተፈጠረው መራቆት ሕይወታቸውን እንዳጡ ጥናቶች  ያሳያሉ።

ይህ እንግዲህ የማእቀባ ጣዮችንና  በነዚህ ሀገሮች የሚገኙ  ሰብአዊ ድርጅቶችን  የሞራል የበላይነትና  ሰባዊነትም እጅግ የሚሞግት ይሆናል፡፤

አልሸባብና አይሲስ የማዕቀቡ ተጠቃሚ ይሆኑ ይሆን?

አሜሪካና ሽርኮቿ  እንደሚሉት በማዕቀቡ የሚገፉ ከሆነ ኢትዮጵያ ስትዳከም በተዘዋዋሪ የሚጠቀሙት በዋናነት በአካባቢው የሚገኙ የሽብር  ኃይሎች  ይሆናሉ  አሜሪካም ሆነች አውሮፓ የፀጥታ ዕርዳታ ለኢትዮጰያ  አንሰጥም ቢሉ ወይም ቢቀንሱ  ኢትዮጵያም ያላትን ሀብት በዋናነት በውስጥ ደሀንነቷን  ለመጠበቅ ስለምታውለው  በጎረቤት ሶማሊያ በስፊው  የሚንቀሳቀሱት አልሽባብን  የመስሉ  ድርጅቶችን  እንቅስቃሴ  ለመከታተል፣ለመከላከል  ወይም  ለማጥቃት የምታደረገውን  ጥረት እንድትቀንስ  ትገደዳለች።

በዚህ ሁኔታ አሁን  እያንሰራራ የሚገኘው አልሽባብ ናበአፍሪካ አድማሱን  እያሰፋ የመጣው አይሲስ(ISIS)  በአፍሪካ ቀንድ ብፍጥነት  ሊሰፋፉ  የሚችሉበት ዕድል  በጣም  ይሰፋል።

ይህ ክፍተት በሞዛምቢክ በታንዛንያና ኮንጎ ብቅብቅ ማለት ብቻ ሳይሆን እየተጠናከረ የመጣው ፅንፈኛነት በምስራቅ አፍሪካ በአካባቢው ከኢትዮጵያ ሌላ   ሊመከተው  የሚችለው ኃይል የለምና አሁን ሰላም አገኙ  የሚባሉትን ኬንያንና ጅቡቲን አስጊ  ሁኔታ ውስጥ  ይጥላቸዋል ብዬ እስጋለሁ።ይህ  የአሜሪካ ማእቀብ  ሊያስከትል  የሚችለው  አንዱ  ያልታቀደ  ውጤት  ነው፡፡

የዴሞክራሲን ጭላጭል ማጥፋት

የአሜሪካ ከሀወሀት ጋር  ድርድር  ይካሂደ  ከሚለው አጀንዳ  በተጨማሪ  እስካሁኑ ሳአት በይፋ ለአዲሱ መንግስት እውቅናን አልሰጠችም፡፡ይህ መሆኑ የኢትዮጰያ  ሀዝብ  የዴሞክራሲ ግንባታ ጥረትን እውቅና  አለምስጠት  ብቻ  ሳይሆን፡ከሀዝብ ድምጽ ይልቅ በጉልበት አስገድዶ  ወደስልጣን መምጣትን የሚያበረታታ  ነው፡፡ይህ ታዲያ በረጅሙ የኢትይዮጰያን የዴሞክራሲ ግንባታ ክፉኛ የሚጎዳ እናም በህግና ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ላይ አስተማማኝ መሰረት ከሚኖረው ዘላቂ  ሰላም (sustainable peace)  ይልቅ  በግለስቦችና ቡድኖች ላይ የተንጠለጠለ ለዘላቂ  አለመረጋጋትም  ይበልጥ በር ከፋች  እንዳይሆን  እጅግ  ያሰጋል፡፡

ማዕቀቡ  የስደተኞች  መበራከት

በኢትዮጰያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የሚያስከትለው አንዱተጽዕኖ ወጣቱ ትውልድ አንፃራዊ ስላምየሰፈነበትና የተደላደለ ሕይወትን መምራት እችላለሁ  ብሎ ወደሚያስብበት  ሀገር መሰደድን (push factor) ነው።

ከቅርበቱ  የተነሳ  የኢትዮጵያ ስደተኞች  ዋናው  መዳረሻ  የሚሆኑትም  አውሮፓና  መካከለኛው  ምሥራቅ  ይሆናሉ።ይህ ሁኔታ በትክክል በአውሮፓና በአረቡ አለም ሕዝብና  መንግሥታት ዘንድ  ሊያስከትል የሚችለውን ሥነልቦናዊ ተጽዕኖ ሙሉበሙሉ ቀድሞ  ማወቅ  ባይቻልም፣ ካለው  ልምድ  በመነሳት  በአውሮፓም  ሆነ  በመካከለኛው  ምሥራቅ  ፀረ፡ስደተኛ  ፀረ፡ጥቁር ስሜትን እጅግ  ይቀስቅሳል  ለማለት  ይቻላል።ከዚህ በተጨማሪም  ኢትዮጵያ  ላለፉት  በርካታ  ዓመታት   ከኤርትራ (131 ሺህ)፣ከስሜን ሱዳን (45 ሺህ)፣ደቡብ ሱዳን( 329ሺህ)፣ከሶማሊያ (191ሺህ) አንዲሁም ከሲሪያና  ከሌሎች  የአፍሪካ  አገሮች የመጡ በአጠቃላይ 900 ሺህ ስደተኞችን  ስታስትናግድቆ  ይታለች።

በሀገራችን ውስጥ የሚፈጠር ሰፋ ያለ  ፖለቲካዊ፣ኤኮኖሚያዊም ሆነ የፀጥታ ቀውስ አሁን ያሉትን ስደቶኞች  ወደ ሌላ  ሀገር እንዲሰደዱ  የሚገፋፋ ሁኔታ(push factor)ይፈጥራል።

ሌሎች የወደፊት ስደተኞችም  ጉዟቸውን  ወደ ኢትዮጰያ  ሳይሆን  ወደ  ሌሎች  ሀገሮች  እንዲያደርጉ  ያስገድዳል።ይህ ሁሉ የስደተኛ ፍልሰትም በቀጠናው ሀገሮች ላይ  እንዲሁም  ራቅ  ባሉት  በአውሮፓና የሰሜን  አሜሪካ ሀገሮች ላይ ታላቅ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው።

ታዲያ ምን ይሻላል?

ይህን በሀገራችን በሕዝባችን፣በቀጠናውም ሆነ  ራቅ ባሉ መንግሥታት ላይ  ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻዎች በድጋሚ ራሳቸውን  ሊመረመሩ፣ግጭትንና  ችግርን  የሚያባብስ  ሳይሆን  ሰላምንና ፍትኅን  እውን የሚያደርጉ በምድር ላይ የሚገኘውንም እውነታ መሰረት ያደረጉ ገንቢ  ሀሳቦችንና ዕቅዶችንም ሊያቀርቡ  ይገባል።በተለይም የገላጋይነትና አስታራቂነት ሚናን ለመጫወት የሚሻ አካል ገለልተኝነትን ጠብቆ መታየትእንደሚገባው  በሰፊው የሚታወቅ ነው፡፡

የምእራቡ መንግስታት በተለይም በተሳሳተ መረጃ፣ የሁኔታዎችን ወስብስብነት፣ በበቂ ባለማገናዘብ ወይም ባለመረዳት፣ ጦርነትን ያክል ምስቀልቅል፣ ሊጓዝ የሚችልበትን ውስብስብና ያልተጠበቀ አቅጣጫ በቂ ግምት ባለመስጠት አንዳንድ ጊዜም ሁኔታዎችን እጅግ አቅልሎ በመመልከት የሚወስዱት እርምጃ ክጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ይህም እጅግ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስክፍል ቢያንስ ከሊቢያ፣ ሲሪያ፣ ከአፍጋኒስታን ኢራቅ ወዘተ ብዙ መማር ይቻላል፡፡ እነዚህ ሀገሮች ሁሉ ዛሬ የሚገኙበት ሁኔታ የምእራቡ ሀያላን በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ እጁን ካስገባበት ጌዜ በፌት ከነበረው በብዙ እጥፍ የከፋ ነው፡፡

የም እራቡ አለም  መንግስታት በኢትዮጰያና በቀጠናው ሰፋፊ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፐሎማሲያዊ ጥቅም እንዳላቸው ግልጽ ነው፡፡ ከፍተኛ ባለስልጣናቶችን  መድበውና ትልቅ ትኩረት ስጥተው መንቀሳቀሳቸውም ይህንኑ የሚያመላክት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ሊጠበቅ የሚችለውም ደግሞ አንድን ሀገር  ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል አጣብቂኝ በመፍጠር ሳይሆን በመከባባር ላይ በተመሰረተ ገንቢ ውይይት ሊሆን  ይገባል፡፡ይህ ሁሉንም ሀገሮች አሽናፊ በማድረግ ዘላቂ ጥቅምንም በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲቆም ያደርጋል፡፡

ማስረጃዎች
Using Economic Sanctions to Prevent Deadly Conflict …

https://www.belfercenter.org/publication/using-economic-sanctions-prevent-deadly-conflict

https://www.piie.com/commentary/testimonies/evidence-costs-and-benefits-economic-sanctions

https://knowledgehub.transparency.org/assets/uploads/helpdesk/overview-of-corruption-and-anti-corruption-in-ethiopia_2019.pdf

The impact of economic sanctions | World Finance

Ethiopia Country Refugee Response Plan 2020-2021 – Ethiopia | ReliefWeb

US official: ISIS threat growing in Africa (az24saat.org)

IntelBrief: ISIS in Mozambique Poses Growing Regional Security Threat – The Soufan Center

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *