wolega
Analysis News

እያደባ በመስፋፋት ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል (Creeping Genocide) – በዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ

በዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ
(ከእንግሊዝኛው ጽሁፍ የተተረጐመ)

ይህን መጣጥፍ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በመፃፍ ላይ ሳለሁ አሶሽዬትድ ፕሬስ የተባለው የዜና ወኪል የሚከተለውን መረጃ አሰራጨ፡፡ “የዓይን እማኞች ዛሬ እሁድ ሰኔ 12 ቀን በአብዛኛው የአማራ ተወላጆች የሆኑ ከ2‚000 በላይ ሰዎች በአገሪቱ ኦሮሚያ ክልል መገደላቸውን ገልፀዋል፡፡”

በኢትዮጵያ የሚገኝ ምንጬ እንደገለፀልኝ ከሆነ ደግሞ 400 አማሮች የተገደሉ ሲሆን፣ 6‚000 ሕይወታቸውን ለማትረፍ ተሸሽገው ይገኛሉ፡፡

ሌላ ምንጭ አዛውንት የሆኑ አንድ ሙስሊም አማራን በመጥቀስ የሚከተለውን ዘግቧል፡፡ “ሸሽተን መስጂድ ውስጥ ተደበቅን፡፡ ተከትለውን መስጂዱ ውስጥ በመግባትም 46 ሰዎችን ገደሉ፤ ከተገደሉት ውስጥ 12ቱ የኔ ቤተሰቦች ናቸው፡፡ እኔንም ገድለውኝ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ አላህ ስለምን አተረፈኝ? ከነርሱ ጋር ብሞት በወደድሁ፡፡”

ይህ ጽሁፍ ለሕትመት በበቃበት ጊዜ ተሰብስቦ የተቀበረ የሟቾች ቁጥር 1‚511 የነበረ ሲሆን፣ 300 ያልተቀበሩና ከ10,000 በላይ ሸሽተው በየጥጋጥጉ እንደሚገኙ በቦታው የሚገኙ የሰብዓዊ መብት አንቂዎች ገልጸዋል፡፡

ከዚያም ወዲህ በቄለም ወለጋ ዞን፤ ሮብ ገበያ ወረዳ፣ ለምለም በተባለ ቀበሌ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በ5 ሰዓታት ውስጥ ከ200 በላይ አማራዎች ተገድለዋል፡፡ ብዙዎች ተፈናቅለዋል፡፡

መጋቢት ወር ላይ እንዲሁ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባወጣው መግለጫ፣ የትግራይ ወራሪ ኃይሎች በንፋስ መውጫ፣ ጨና፣ ቆቦ እና ሌሎችም ሥፍራዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀሙትን የጅምላ ጭፍጨፋዎች አስገድዶ መድፈርና ዝርፊያ በፅኑ ኰንኗል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *