News

‹‹ የእርሰ በእርስ ጦርነት ይብቃ ›› በሚል መፈክር ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ በአስቸኳይ ወደ ካምፕ ይግባ! በሚል መሪ ቃል ለህዳር 30 /2016 ዓ/ም ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ ተጠራ ። 

በዛሬው ዕለት ህዳር 19/2016 ዓ/ም በሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች በተረፈመ ደብዳቤ ጦርነት እንዳቆም መከላከያ ሠራዊቱ ከዘመተባቸው ክልሎች ወጥቶ ወደ ጦር ካምፑ እንዲመለስ እና ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲከፈቱ የሚጠይቅ ሕዝባዊ የአደባባይ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል ። 

በአስተባባሪዎቹ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት የማሣወቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል ። ሕዝባዊ ሰልፉ መነሻውን አራት ኪሎ የድላችን ኃውልት አድርጎ በተለያዩ ጎዳናዎችንና አደባባዮችን በማለፍ መዳረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የዕለቱን መልዕክት በማስተላለፍ ይጠናቀቃል ። 

መላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሠልፉ በነቂስ እንዲታደሙ እና አገር የማዳን የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አስተባባሪዎቹ ጥሩ አስተላልፈዋል ። 

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናትም በፕሬስ ኮንፈረንስ ዝርዝሩን እንደሚገልጹም አስተባባሪዎቹ አሣውቀዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *