Opinion

የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ለዶክተር አብይ ተጨማሪ አደጋን ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

 

በባጤሮ በለጠ

Friday, December 14 2023

ሀማዝ እስራኤልን አጥቅቶ ከ 1200 የእስራኤል ዜጎችን ከገደለና ከ200 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ጠልፎ ከወሰደ ወዲህ የተቀሰቀሰው ጦርነት፣ የቀይ ባህር ተጎራባች የሆኑ ሀገራትን ልዩ ትኩረት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

የየመን ሁትሲ ( Houthis ) አማጽያን ይህኑ ጦርነት ተከትሎ ወደ እስራኤል የሚያስወንጭፉት የሚሳኤል ጥቃትም ይሁን በተከታታይ በቀይ ባህር ላይ የሚንቀሳቀሡ መርከቦችን ማጥቃት መጀመራቸው አሁን ደግሞ ወደ እስራኤል የሚሄድንም ሆነ ከስራኤል ጋር ግንኙነት አለው ብለው የሚያስቡትን መርከብ ሁሉ በቀይ ባህር ላይ እናጠቃለን ብለው ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው፣ ከፍተኛ መነጋገሪያ ብቻ ሳይሆን ስጋትም ሆኗል፡፡

ይህን ከሁትሲ ( Houthis ) አማጽያን ሊሰነዘር የሚችለውን ጥቃትና በአለም አቀፍ ንግድ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን መደናቀፍና አጠቃላይ ጫና ለመከላከል አውሮፓና አሜሪካ በአካባቢው ጠንከር ያለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አቅደዋል፡፡

በዚህ ቀይ ባህርና ቀጠናውን ከጥቃት የጸዳ የማድረግ ፍላጎትና እቅድ ኤርትራ ልትጫወት የምትችለው ልዩ ቦታ በግልጥ ያልተነገር ቢሆንም በመልካ ምድር አቀማመጧ ምክኛት ቁልፍ እንደሚሆን ግን አያጠራጥርም፡፡

በዚህ ምራእባውያኑ ከቻሉ ከኤርትራ ጋር መወዳጀት መጠናከር ቢያንስ ግን ኤርትራን አለማስቀየም በሚመርጡበት ጊዜ ፣ የ ዶክተር አብይ መንግስት ከ ሸአብያ ጋር የገባበትን ንትርክ እንደምታው ምን ይሆናል ምን ሊያስከትልበት ይችላል ብሎ መመርመር ይገባል፡፡

በዚህ አንጻር በአሁኑ ሰአት በምንም አይነት በኤርትራ ላይ የሚደረግ ትንኮሳ በምራቡም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እንዲሁም በብሪክስ አባል መንግስታት በኩል ምንም ድጋፍ አይኖረውም፡፡ ይህ ታዲያ ዶክተር አብይን በዲፐሎማቲኩ አለም ይበልጥ የተገለለ ምናልባትም ወዳጅ የለሽ ሊያደርገው የሚችልበት ሁኔታ እጅግ ሰፊ ነው፡፡

በትላንትና  እለት የአሚሪካ መንግስትር እና የአውሮፓ ማህበረስብ 23ኛውን የአልጀርስ ስምምነት አስመልክቶ ስምምነቱን አክብር የሚል መልክት ላይ ያነጣጠረ መግለጫም ከዚሁ ጉዳይ ጋር ቢያያዝ አይደንቅም፡፡

መራባውያኑ በቀይ ባህር ላይ ወታደራዊ ስምሪት ሊያደርጉ በተቃረቡበት በአሁኑ ሰአት፣ ዶክተር አብይን አርፈህ ተቀመጥ የሚል ቀጭን ትእዛዝ ሳይሰጡት ይቀራሉ ብሎ ማሳብ ይከብዳል፡፡ ይህ ከሆነም ዶክተር አብይ የ ኤርትራና ቀይ ባህር ጋር በተያያዘ የጀመረውን ሁሉ ወደ ጎን ትቶ ሲሄድ ልናይ እንችላለን፡፡

ሲጠቃለል፣ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በራሱ በድርጅታቸውም ውስጥ ተቀባይነታችው እንደጉም እየበነነ የጦርነትና ችግር ቀፍቃፊ እየተባሉ የሚጠቀሱት ዶክተር አብይ አካባቢያዊው ጂኦ ፖለቲካል ሁኔታውም እያገዛቸው አይደለም፡፡ የእስራኤልና የሀማዝ ጦርነትም ሌላ ተጨማሪ ዶክተር አብይ ላይ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ መጭው ጊዜ የዶክተር አብይ አህመድ የጭንቅ ጊዜ እየተባባሰ እንደሚሄድ መረጃው ሁሉ በየግርግዳው ላይ ተጽፎ ይታያል፡፡

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *