meskerem abera
Opinion

የአማራ ህዝብ የህልውና ስጋት አለበት ሲባሌ…

መስከረም አበራ
ከቃሊቲ ማጎሪያ

መብቱን በከፊልም ሆነ በሙሉ የተነጠቀ ህዝብ ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ ለትግል መነሳቱ
የማይቀር ነው። የዙፋናቸውን አራት እግሮች በህዝብ መብት ላይ ጭነው የተደላደሉ ጨካኝ
አምባገነኖች ደግሞ ይህን አይቀሬ የህዝብ ትግል ቢችለ ለማስቀረት፣ ካልሆነ ለማዘግየት፣
ካልተቻለም የተጀመረ የህዝብ ትግሉን አልከስክሶ ለማስቀረት ደመነፍሳቸው ያዘዛቸውን ሁለ
ያደርጋሉ። ከዚህ ደመነፍሳዊ አካሄድ አንዱ የህዝብን የሚታይ በደል ሸምጥጦ መካድ፣ አሳንሶ
ማቅረብ ወይንም ከሆነው በተቃራኒው አድርጎ አጣሞ ማቅረብ ናቸው። እንዲህ በማድረግ
ህዝቡ በየእለቱ እየኖረ ያለውን የመከራ ኑሮ፣ ሞት፣ ስደት እና መፈናቀለ እውነትነት
እንዲጠራጠር፣ እንዲደናገር እና ለትግለ መነሳቱ ራሱ ትክክለኛ እርምጃ መሆን አለመሆኑን
የመጠየቅ ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ ያደርጋሉ።

ለትግል የተንሳው ህዝብ ለትግል ያስነሳው በደል መነሻው ከየት እንደሆነ፣ ለደረሰበት በደል
ተጠያቂው ማን እንደሆነ ለይቶ አውቆ መታገለ የሚገባውን አካል በግላጭ እንዳይታገል
ብዥታና ድንጋሬ ውስጥ መክተት የጨቋኝ ረጋጭ እና ጨካኝ መንግስታት ባህሪ ነው።

በሀገራችን በህውሀት እና ኦህዳዴ/ኦነግ ቅብብሎሽ ለሰላሳ ሶስት አመታት የዘለቀው አማራ-ጠል
ጨቋኝ ዘረኛ ስርዓት በአማራ ህዝብ ሊይ ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን ፈርጀ፡ብዙ በደል ህዝቡ
ተረድቶ ለትግል እንዲይነሳ ይህንኑ የተለመደ ዘይቤ ይጠቀማል። ይህን ዘይቤውን ገቢራዊ
ለማድረግ የተለያዩ መንገድችን እያፈራረቀ ስራ ላይ ያውላል። ራሱ በሚዘውራቸው ሚዲያዎች
በአማራ ህዝብ ሊይ የሚደርሰውን በደል መካድ፣ በተቃዋሚ ፓርቲ ማሊያ የጭካኔው አጋር
ያደረጋቸውን የስልጣን ጥመኛ ሹማምንት ማናገር፣ ገለልተኛ ሲል የሰየማቸው ተቋማት የዘር
ማጥፋት ወንጀሉን አይተው እንዳላዩ እንዲሆኑ ማድረግ፣ አማራ-ጠለ ስርዓት ከሚጠቀምባቸው
ዘዴዎቹ ዋንኞቹ ናቸው።

 

ሙሉ ጽሁፏን ለማንበብ

 

 

Source: zehabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *