በትላንት የታሪክ ምርኮኞችና በነገው ተስፋችን ቁማርተኞች ሕልውናዋን የማታጣ ሃገር መገንባት ከሁላችንም የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው!! በምድራችን ካላፉት የሥርዓተ መንግሥታት ታሪክ ውስጥ በራሳቸው ሕዝብ መካከል ተቃርኖን እየሸመኑ አንዱን የማኅበረሰብ ክፍል ከሳሽ፤ ሌላኛውን ደግሞ ተከሳሽ የሚያደርግ ጥልፍ በመጎንጎን የሀገረ መንግሥትነት ሕልውናቸውን ያጸኑም ሆነ ዘላቂ ሰላምና እድገታቸውን ያረጋገጡ መንግሥታት ተብለው ለአብነት ያህል እንኳ ስማቸው የሚጠቀስ ነገሥታትም ሆኑ መንግሥታት የሉም። Read more
ኢትዮጵያ በብልጽግና ግለሰባዊ አምባገነናዊ ዘረ–ፈጅ አገዛዝ እጅ ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ ዋነኛ መገለጫዋ፡ ጦርነት፣ የዘር ፍጅትና እልቂት እንዲሁም ፍፁም ድህነት ሆነዋል። ሀገሪቱ ሕግና ሥርዓት የፈረሰባት፣ ሚሊየኖች የከፋ ድህነት ውስጥ የወደቁባትና የተፈናቀሉባት፣ ለዜጎቿ የሚሆን ተስፋ የጠፋባት፣ ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ሀገር አጥፊ ጦርነቶች የሚታወጁባት፣ አምባገነናዊ አገዛዝ የተጫነባት እና እንደሀገር ከወደቀ ሀገረ–መንግስትነት አልፋ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባት እንዲሁም በቀጠናውና በዓለም Read more
ይህ የኢሕአፓ የወቅቱ የትግል ጥሪ ነው! ሀገር የዜጎቿ እጅ ስራ ናት። የሀገር ህይወቷም፣ ልማቷም፣ ዕድገቷም፣ ሠላሟም፣ውበቷም የሚገኘው ከሕዝቧና በሕዝቧ ጥረት ነው። ያለሕዝቧ ሁለንተናዊ በይነግብር ሀገር ምደረበዳ ነች። ኢትዮጵያን እልፍ አዕላፍ ዜጎቿ ደማቸውን አጉርፈው ውቅያኖስን አቅልመው፣ አጥንታቸውን መርከብ አድርገው፣ ገጣጥመው፣ አያሌ ማዕበሎችንም ተቋቁመው፣ ቀዝፈው፣ ተሻግረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ አስተላልፈዋታል። በቀደሙት ልጆችዋ አርቆ አሳቢነት፣ ቁርጠኝነት፣ ሁኔታዎች ግድ Read more