ባለ አደራውምክር ቤት የጠራው ሠልፍ
News

ጥቅምት ሁለት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመብት ጥያቄዎች ሠልፍ በመደመር በመከልከል በመተኮስ አይገታም !!!

eskinderየአደባባይ ሰልፍ በሱዳን መንግስት ሲቀይር ሆንግኮንግ ከተማ ሲያንቀጠቅጥ ኢራቅ ወጣቱን ከታጠቀ ሀይል ጋር ሲፋጠጥ እያየን ነው።
 የአዲስአበባ ነዋሪዎች ሌላው ቢቀር በ1997 ያደረጉት መስዋዕትነት ሁላችንም እናዉቀዋለን።
ታዲያ አዲስአበባ የኛ ነው እናንተ የራሳችሁን ዕድል መወሰን የማትችሉ  በኛ ፈቃድ ለመኖር የተፈቀደላችሁ ተብሎ በበቀለ ገርባ ሲፎከር ዝም የሚል የከተማ ህዝብ በዐለም አይኖርም።
ጣሊያን ፋሺስትን ዝም በሉ የሚዋጋ የለም ህዝቡ በጎሣ ዘር የተከፋፈለ መሪ የሌለው ህዝብ ነው ተብሎ የአዲስ አበባ ነዋሪ ለጣሊያን እንዲገዛ መሰበኩን ታሪክ ይነግረናል።
ታዲያ ኢትዮጵያ በታሪካችን ጎበዝ መሪ ሲገኝ መከተል ሲጠፋ ማዘን የተለመደ ነው።
የኦሮሞ ተረኞችዕብሪት ሊተነፍስ የሚችለው በአደባባይ ተቃውሞ መሆኑ ስለሚታወቅ እነርሱም ሆነየነርሱ ሽሪኮች መጪው ጥቅምት ሁለት እንዳይሳካ ከማደናገር ማስፈራራት አይመለሱም።
ባለ አደራውምክር ቤት የጠራው ሠልፍ የመብት ጥየቃ ሰልፍ ነው። ዐቢይ አህመድ በዉጭው ዐለም የዲሞክራሲ ካባ ከለበሰ ዐመት ቢያልፈውም የተቃውሞ ሰልፍ በመከልከል ያው መለስ ዜናዊ ነው።
የፈራ ቤቱ ይቀመጥ አብዛኛው ነዋሪ ሰልፉን ይደግፋል። መደመር መተኮስ ከሆነም በይፋ ዐለም ያውቀዋል።

Tedla Asfaw

source: zehabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *