juhar, oromo
Opinion

ከሃያ ቀናት በፊት ደሩ ዘ-ሀረሩ የጀዋር ተንታኝ  ይሁን  ጠበቃ (ታጠቅ  መ .ዙርጋ)

ከሃያ ቀናት በፊት ደሩ ዘ-ሀረሩ የጀዋር ተንታኝ  ይሁን  ጠበቃ  ሳይነገረን  ፤ ጀዋር  በኦሮሞ  መዲያ  አውታር  በ(OMN)ያደረገው  ምጽና  መሳይ ገለጻ  ሁለት  ገጽታዎች

ታጠቅ  መ .ዙርጋ

2 October 2019

ሀ) ለመብት ታጋይ እንጂ ዘረኛ አትበሉኝ እባካችሁ!
በዚህ ገለጻ  ‘’የአዳኙ ካሜራ’  አቶ ደሩ ዘ-ሀረሩ ፤ ጀዋር ዘረኛ አይደለም ሊለን ሞከረ። ዘረኛም ተባል ጠባብ ወይም አክራሪ ብሄርተኛ- በተግባር አንድ ከሆኑ ልዩነቱ የትርጉም ጉዳይ ነው ። ሰርቄአለሁ ግን ሌባ አትበሉኝ፣ገድዬአለሁ ግን ወንጀለኛ አትበሉኝ፣ ሸፍቼአለሁ ግን ሽፍታ አትበሉኝ ወዘተርፈ ዓይነት አሆንምን?

የአገራችን ምድር የሰው ዘር አብቅሎ ማኅበራዊ ሕይወት ከተጀመረበት  ዘመን አንስቶ  በደም፣ በባህል፣ በቋንቋ፣ በታሪክ በአርበኝነት፣ በማኅበራዊ ሕይወት፣በሃይምኖት ወዘተር ተሳስሮና ተቃቅፎ የኖረውን ሕዝብ በጎሳ ተቧድነው  እንዲተላለቁ ፤ጀዋር ራሱ ከተናገራቸውና በጀዋር የጥላቻ አስተምሮት (ዲስኮርስ) ምክንያት ከተፈጸሙትና ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚያውቃቸው እኩይ ተግባሮች ጥቂቶቹን እነሆ ፥
1. ጀዋር እንደ አንድ ጀግና አርበኛ ሲፎክር “እኔ በተወለድኩበት አካባቢ ብዙ ክርስቲያን የለም፤ ቢኖርም በሜንጫ እንጨርሳቸዋልን” ማለቱ
2. የሻሽመኔውን፣ የቡራዩን፣ የለገጣፈውን፣የሱሉልታውን፣የሲዳማውን (የወንድ ብልት እስከ መሰለብ) ግፎችና እልቂቶች
3.  ግንቦት7 ወደ አ/አበባ መግባትን ምክንያት በማድረግ የተሰቀሉትን እውነተኛ ባንድራችንን አውርደው የኦነግ ባንድራ ለመስቀልና የአጼ ምኒሊክን ሃውልት ለማፍረስ ፣ ቄርዎች አ/አበባን በመውረሩበት ወቅት ፤ ያንን የማን  አለብኝነትን የመንጋ የጥፋት ዘመቻ ለማውገዝና ለመከላከል ከወጡት የአዲስ አበባ ወጣቶች በርካታዎቹ ታድነው ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ/ ሲታሰሩ፤ በቁጥር ከ4 -5 የሚሆኑትን በፖሊስ ጥይት ተደብደበው መሞታቸውን ተሰምቷል ። ነገር ግን ከጠብ አጫሪ ቄርዎች የታሰረም ሆነ የተገደለ አንድም ሰው አለመኖሩን ተረጋገጠ ። የአብይ መንግሥትም  የብሄርተኝነት ቀይ ምልክት ገሃድ የወጣው ከዚያ ጋር ነበር ።
4. የኦሮሚያ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሴነዶስ ሥር እንዳይተዳደሩ የማድረግ የአድማ ዘመቻ
5. በኦሮሚያ ክልል በተሰሩ ኮንደምኒየም ቤቶች ከኦሮሞች ሌላ ማንም አይኖርበትም! ብሎ መከልከል
6. ፊንፊኔ የኦሮሞች እርስት ነው ! ብሎ ማወጅ ፣መሟገት
7. ከሃያ ቀናት በፊት የጅማ ቤተክርስቲኖችን ለማቃጠል የቄሮችን መነሳሳት
8. በኦሮሚያ ክልል በአማርኛ ትምህርት እንዳይሰጥ ማገድ ወዘተርፈ ። እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው እንዳሉ ሆኖ ፤ አቶ ደሩ ከላይ በጠቀስኳቸው  ድርጊቶች የጀዋር ተልዕኮ የለበትም ነው የሚለን ። ወይም ከላይ የተጠቀ ስኳቸውና  ሌሎችም ጥፋቶች በእሱ አጋፋሪነት ቢፈጸሙም ጀዋር ዘረኛ አያሰኘውም ነው የሚለን ። አንድ ወንጅል የሚለካው  በስሙ ነው ወይስ በድረጊቱ ?
ጀዋር ጠባብ ብሄርተኛ የተሰኘ ሃርግ እንጂ ‘ዘረኛ’ የሚል ቃል መጠቅም አግባብ አለመሆኑን ሲገልጽ በግረመንገዱ ፤ የጥቁር፣ የብጫና የነጭ የሰው ዘር በሚል መከፋፈል የተጀመረው  መቼና ለምን እንደሆነ ገለጸ ።
አዎን እ.ኤ.አ እስከ 1778 ዓ/ም የስዎች ዘር አንድ ነበር (Human Race) በመባል ብቻ ነበር የሚታወቀ ። በዚህ በጠቀስኩት ዓ/ም ስልታዊ የዘረኝነት ጽንሰ ሃሳብ መሰረት የጣለው ፈራንሳያዊው Buffoons (publication of` Historie Naturelle de l`homme’ –the natural history of human being) ማለት የሰው ልጅ የተፈጥሮ ታርክ በተሰኘው ጽሁፉ ቢሆንም ፤የዘር ፖለቲካ (race politics) ሥራ ላይ የዋለው እ.ኤ.አ ከ1859 ዓ/ም ጀምሮ ነው። ከዚያ ዓ/ም ጀምሮ -ነጭ በተፈጥሮ ንጹህ/ፕዩር  ዘር ነው! ነጭ በተፈጥሮ ብልህ ዘር ነው! ነጭ ሃያል ዘር ነው! ነጭ በተፈጥሮ  ነጭ ያልሆኑትን  ዘሮች ለመግዛት የተፈጠረ ነው ! ወዘተ.. በማለት ቀመሩ/ቲዮሪ/ ነደፉ፣ ሰበኩ ፣ አስተማሩ ፣ሥራ ላይ አዋሉ ወዘተርፈ። ስለሆነም ዘረኝነት ተፈጥሮአዊ  ግኝት ሳይሆን የማኅበራዊ ምህንድስና ውጤት ነው ።

የዘረኝነት ትርጉምና ታሪካዊ አመጣጥ ስለማውቅ- ስለአገሬ ሕዝብና ፖለቲአካ ሳውራም ሆነ ስጽፍ ‘ዘረኛ/ዘረኝነት’ የተሰኙ ቃላት አልጠቀምም።  ፖለቲካዊ/ፖለቲሳይዘድ  ሆነ እንጂ እንኳንስ እኛ ኢትዮጵያውያን -በዚህ ባለንበት ምድር ያለ የሰው ዘር (human race) በሙሉ አንድ መሆኑን ከላይ ጠቅሼአለሁ ። ስለ-ስነስብዕ  ተመራማሪ ሊሂቃን (Anthropologists)  አገራችን ኢትዮጵያ የሰው  ልጅ መገኛ መሆኑን ስለአረጋገጡ ፤ በየትኛውም አሁግር/አገረ  ታሪክ ከሚያውቁ  ሰዎች ባጋጣሚ ስንገናኝ እና የት አገር ሰው መሆናችን ስንገልጽ (Aha! Ethiopia, the cradle of humanity! The birthplace humanity! The origin of humanity!) እያሉ ይመልሱልናል ።

በመማርና በማንበብ ካገኘሁት እውቀቴ በተጨማሪ  ከተለያዩ አገራት ሰዎች ይህንን ስሰማ  በኢትዮጵያዊነቴ የበለጠ እኮራ ለሁ ። በእኔ እምነት በኢትዮጵያ ምድር የሚገኙ -ነገዶች፣ በሄረሰቦችና ብሄሮች ሁሉ ከአንድ ኩሬ/ምንጭ  (genome) የወጡ  ናቸው ፤ ኢትዮጵያዊ/ዊት ዘር (race) ናቸው ። ስለሆነም  ስለአገሬ ሕዝብም ሆነ ስለአገሬ ፖለቲካ ስጽፍም ሆነ ሳወራ ጽንፈኛ፣አክራሪ ፣ ጠባብ እያልኩ እጠቀማለሁ እንጂ ዘረኛ/ዘረኝነት ፣ እያልኩ አልጠቀምም ።

ኢትዮጵያውያን  ዘረኛ/ዘርኝነት እያሉ የሚናገሩትና የሚጽፉት የዘረኝነት ተግባር ሲፈጸም ስለሚያዩ ነው። ጀዋር ያንን ኢ-ስብዕ/ኢ-ሰው  የሆነ የዘር ሽንሸና ታሪክ ማንበቡ ጠቀመው ወይስ ጎዳው ? በእኔ እምነት የጠቀመውም የጎዳውም ይመስለኛል። ምክንያቱም፦

1- የኦሮሞች ጠበቃ ነኝ በማለት የዚያን ግልባጭ እንደ ሞዴል ወስዶ ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ በመተግበሩ ፤አደባባይ እንዲወጣ፣  በየሚዲያው ስሙ እንዲጠራ፣ በየሚዲያው ምስሉ እንዲለጠፍ እና  ግዜያዊ ዝናና እውቅና እንዲያገኝ ረቶታል።

2- ነገር ግን ያንን የዘረኝነት ተልዕኮ በተወልደበት አገር ሕዝብ በማዋሉ የኋላ የኋላ የኅሊና ሰቆቃ ይገጥመዋል፤የውድ -ቀቱንም ምክኒያት ይሆን ይሆናል።

ለ)  በዚያ የጀዋር ገለጻ -የምጽናና የመለስለስ ቃና ይስተዋል ነበር። ከሁለት ሳምንታት በፊት ‘Jewar is making his own demise or fall’ የሚል የአንድ አረፍተ ነገር ጽሁፍ በፌስቡክ ለጥፌ ነበር። እንደ እነዚህ ዓይነት የህዝብ አስተያየቶ፣በአውደ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም “በኦሮመነት አፍረን አናውቅም !ኦሮሞን እንወክላለን በሚሉ ጠባብ ብሄርተኞች ግን እናፈራለን!” ባሉት ክቡር ኩምሳ ደመቅሳ ዓይነት እውቅ የኦሮሞ ተወላጆችን ተቀባይነት በማጣቱ አጥፍቼአለሁ ፣ ሁለተኛ የዚህ አይነት መጥፎ ሥራ አልሰራም ለማለት ይሆን? ወይስ የተነሳበትን ቁጣና ትችት ለግዜው ለማርገብ ወይም ለማስተኛት ይሆን? ምጸናውና መለስለሱ ብዬ አሰቤ ነበር ። ነገር ግን ከዚያ ገለጻው ወዲህ ስከታተለው        ብሶበት እንደ አዶከበሬዎች አለቃ ያደርገዋል  ።

ጀዋር ለኦሮም ሕዝብ መብት ታጋይ ነኝ ይላል። ለመብት መታገል የዚያ ሕዝብ አካል የሆኑትን ሌሎች በመጥላት፣ የዚያ ሕዝብ ወንድም በሆኑትን ሌሎች ላይ በማዝመት፣በማስጨፍጨፍ ወዘተ.. ነውን?
ጀዋር በኦሮሞች ላይ ቆመ እንጂ ለኦሮሞች አልቆመም። ምክንያቱም በኦሮሞችና በሌሎች ወንድሞቻቸው መካከል የማይሽር የጥላቻ ጠባሳ፣የጥላቻ  ቁስል እያሰፀረጸ ነው ። ኦሮሞች ከሌሎች ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸውን አብሮ እንዳይኖሩ እያደረገ የራሱን የታጋይነት ታሪክ እንዲኖረው የሚጥር ሰው ነው ፤ ያውም በውሸት ኦሮመነት።
የጀዋር የተሳሳት የፖለቲካ እውቀት ፥ በኢትዮጵያ ምድር የሚኖሩ የሁሉንም  ነገዶች ፣ብሄረሰቦችና ብሄሮች ፖለቲካዊ  ፣ሰባአዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበ ራዊ መብቶች እስካልተከበሩ ፣ ፍትኅ-ዕርቱ እስካላገኙ ፣ከጭቆናና ከብዝበዛ ነጻ እስካልወጡ ወዘተ.. ለኦሮሞ ወንድሞቻችን ብቻ እነዚህን መብቶች፣ፍትኅና  ነጻነት አስገኛለሁ  ወይም ኦሮሞ የኢትዮጵያ ገዢ ባማድረግ ብቻ የሁሉንም ኦሮሞች ችግሮች ይወገዳሉ ብሎ መዋተት  ፍጹም ጭፍንነት ነው
ጀዋር ጠባብ ብሄርተኛ ነው፣ጀዋር ፖፕሊስት ነው፣ ጀዋር ልቅ/hyper ፖለቲከኛ ነው ። ስለሆነም ጀዋር አዳሃሪ (reactionary) ፖለቲከኛ አንጂ ተራማጅ ፖለቲከኛ አይደለም።

የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በእነ ጀዋር ቅስቀሳ -ከሥልጡን፣ ከብስል፣ ከደግ  ወዘተ..የኢትዮጵያ ሕዝብ እንገንጠል ቢሉ መንገዱ ጨርቅ አይሆንም ። A “far away field looks always green” ሩቅ ያለ ሜዳ ሁሌ አረንጓዴ መስሎ ይታያል እንደማለት ይመስለኛል። መገንጠል ሲታሰብ ኤትራ ውያን ወገኖቻችን  የደረሰባቸውን ማሳተዋል ያስፈልጋል። በይፋ ባይገነ            ጠሉም፣ ከኢትጵያ ባጀት ቢያገኙም፣  ለ27 ዓመታት ከአገራች የተዘረፈ ሃብትና የልጅ ልጆቻንን ከፍለው የማይጨርሱት በስማችን የተበደሩትን ብዙ ብሊዮን (dollar, pound sterling, Euro,yuan etc.) በትግራይ ባይከማች ኖሮ፤ በዚህ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ሕይወት ምን ሊምስል እንደሚችል መገመት ይቻላል። መገጠል ለሚያስቡ (1) ደም የተከፈለበት ባርነት- የኤርትራ አብዮት ህልሞችና ውድቀት <በረዘነ ሃብቴ> (2) (Animals Farm) የእንስሳት አብዮት መጻህፍት እንዲያነቡ እመክራቸዋለሁ ።

የአዳኙ ካሜራ ባለቤት -ደሩ ዘ-ሀረሩ  የጀዋር ተንታኝ ወይስ ጠበቃ?
‘አማራ፣ትግሬ እና ኦሮሞ ያልሆኑ ብሄረሰቦች ለፖለቲካ ሥልጣን ስለማይወዳደሩ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ከእነዚህ ውጭ ካሉት የብሄረሰብ አባላት የፖለቲካ እውቀት ያላቸው የሉም ለማለት ነውን ?ፖለቲካ ይፈራሉ ማለቱ ይሆን? ፖለቲካ አይወዱም ከማለት አንጻር ይሆን? ወዘተርፈ፤ ቢያብራራው ጥሩ ነበር ።

በርግጥ በአገራችን የጠመንጃ ፖለቲካ ባህል እንጂ የዲሞክራሲያዊ ፖለቲካ ባህል ስላነበረና ስለሌለ ፣ በጠመንጃ አፈሙዝ ለበትረ መንግሥት ሲፋለሙ የነበሩትና ያሉት እነዚሁ ስለሆኑ ማለቱ ይመስለኛል። ደርግና ወያኔ በካድሬነት እንዲያገለግሏችው ከመለመሏቸው ያናሳ ብሄረሰቦች አባላትን ሳናካትት፤ በአገራችን የፖለቲክ ታሪክ  በቁጥር ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ አናሳ በሄረሰቦች ከፖለቲካ መድረክ የተገለሉ ነበር ማለት ይቻላል። ቢኖሩም በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ ። የነበራቸው ሚና (አርሰው፣ቆፍረው፣ ነግደው ፣ ሽምነው ፣ አንጥረው ፣ ቀጥቅጠው፣ ገብረው ፣ታዘው ፣ የባዕድ ጠላት ሲመጣ ዘምተው ፣ አገራቸውና  ሕዝባቸውን በፍጹም ታመኝነት አገልግለው ወዘተ.. መኖር ነበር ። ለዚህ የደቡቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ናሙና ማድረግ ይቻላል።

“የማያስቸግር ሕጻን እናቱም ትረሳዋለች ወይም አታስታውሰውም” እንደም ባለው  ባለፉት ጥቂት ዓመታት “አማራና ኦሮም ከተስማሙ ! አማራና ኦሮሞ በአንድነት ከተሰለፉ  ! …” የአገራችንን  ሁለገብ ችግሮች እንደሚፈቱ መፈክር ይዥጎደጎድ ነበር እንጂ ወደ 60 የሚጠጉ  ብሄረሰቦች ስላአቀፈው ስለደቡቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድም ቃል ወይም መፈክር አልሰማሁም።

ጠመንጃ  አንግተው በሽፍትነት ቢያስቸግሩ ኖሮ <አማራ፣ ኦሮሞና  የደቡብ ሕዝብ> ከተስማሙ ! ይባል ነበር ። የወያኔ ጸረ-አንድነት ፖለቲካ ከመጣ ወዲህ አንዳንድ ኢሰብአዊ ድርጊቶች እየታ ነው እንጂ፤ የደቡብ የኢትዮጵያ  ሕዝብ ሲቪካዊና ሲቪላዊ ባህል ያላው ሕዝብ ነበር ፣በዚያው እንዲቀጥሉ  ነገር ግን  ከወያኔ የጎሰኝነት ነቀረሳ ለመላቀቅ መታገል እንዳለባቸ  እመክራለሁ ።

የደቡብ  ሕዝብ (ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ፣መምህር ታዬ ቦጋለ፣ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱና መርሻ የሴፍ መሰል  ፍጹም አገር ወዳድ ምሁራን ያበቀለ ሕዝብ ነው ። ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ሉዓላዊ ኅልውና ሁሉንም በሄረሰቦች የማይናቅ ሚና አላቸው ።

‘ለፖለቲካ ሥልጣን ከሚፎካከሩት ከ(አማራ፣ ኦሮሞና ትግሬ) ብሄረሰቦች  ጀዋርን የሚያህል የፖለቲካ ተጽኖ የሚፈጥር ሰው የለም’ አለ ደሩ ዘ-ሀረሩ ። ጀዋር በወቅቱ የአገራችን ፖለቲካ ምን አውንታዊ ተጽኖ አደረገ ወይም አለው ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀዋርን የሚያውቀው – በአሸባሪነት፣ በከፋፋይነት ፣በጸረ-አንድነት ፣ ቄሮችን ለጠባብ ቤርተኝነት በመኮትኮት  ወዘተርፈ ነው ። በርግጥ  አሉታዊ ማለት የማስቸገር ተጽኖ ሊኖረው ይችላል።እንደውም አረቦች ኢትዮጵያን ስለሚጠሉ ፣ጀዋር በአባቱ የመናዊ መሆኑን ከታወቀ  ወዲህ የአረቦች ተልዕኮ እየከወነ ሳሆን አይቀርም ተብሎም እየተጠረጠረ ወይም በዓይነ ቁራኛ እየታየ ነው ።

ደሩ ዘ-ሃረሩ ‘ዘረኛ/ዘርኝነት’ በተሰኙ ቃላቶች መጠቀም የጀመሩት የ60ዎቹ ናቸው አለ።
ዋሽቷል! ወይም አያውቀም ወይም ጀዋርን ለማስደሰት ፈልጎ ነው ። ቀኝ አክራሪ ፣ ግራ አክራሪ ፣ መሃል ግራ፣ መሃል ቀኝ፣ ጠባብ ወዘተ..  የርዕዮት ዓልም መግለጫ ቅጽሎች ናቸው ፤ታሪካዊ አመጣጥ አላቸው ። በአገራችንም የጠባብ ብሄርተኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ማቆጥቆጥ የጀመሩት  በ60ዎች አካባቢ ስለነበረ የ60ዎቹና የ70ዎቹ  በተማሪዮች ንቅናቄ የነበሩ ሃይሎችና ግራ ፖለቲከኞች ጠባብ ብሄርተኛ/ኝነት በተሰኙ ቃላት  መጠቀም ጀመሩ  እንጂ ዘረኛ/ዘረኝነት ቃላት  በያኔ  ፖለቲካዊ እንቅስቃሴም ሆነ አስተም ሮት ተሰምቶም አይታወቅም ነበር።  ከደቡብ አፍሪክ የአፓርታይድ /የዘር መድሎ ሥርዓት ከመቃወምና ከማውገዝ ጋር በተዛመድ  ብቻ ነበር ስለዘር/ዘረኝነት ይነሳ የነበረው ።  በአገራችን ‘ዘረኛ/ዘርኝነት’ የሚባሉ ቃላት መጠቀም የተጀመረው በዘመነ ወያኔ ነው ፤ ምክንያቱም የአፓርታይድ/የዘር መድሎ  የአገዛዝ ሥርዓት ይጠቀሙ ስለነበረና አሁንም ስለሚጠቀሙ ።

ከዚያ ደሩ ዘሃረሩ የጀዋር ተንታኝ ከሆነበት ቀን አንስቶ ኢትዮጵያውያንን ያስገረመው ደሩ ዘሃረሩ የጀዋር አፈቀላጤ መሆን  ነው። ስዎች ከሚችሉት ቋንቋ ወደ ማይችሉት ቋንቋ  አስተርጓሚ ሲፈልጉ፣ የሃሳብ ማሳካት ችግር ሲኖርባቸው  ከሕግ ጋር የተያያዙ/የተገናኙ ቃላቶችና አንቀጾች በመጥቀስ መግለጽ የሚችል ባለሞያ ሲፈልጉ ፤ባጠቃላይ ራሳቸውን ወክለው የሚፈል ጉትን ጉዳይ ማስፈጸም ሲያቅታቸው  እንደ እነሱ ሆኖ ጉዳያቸውን የሚያስፈጸም ሁለተኛ ሰው ይፈልጋሉ ።
ጀዋር በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የነዚህ ችግሮች እንደሌለበት ቢያንስ ትምህርት ቀመሱን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል፤ ደሩ ዘ-ሀረሩ የጀዋር ጠበቃ ነው እንዳይባል የጥብቅና ሞያ አለው ሲባል አልሰማንም ። ታዲያ ለምን ፍጆታ (motive) ነው የጀዋርን  ሃሳብ ወይም ንግግር ተንተናኝ ሆኖ የቀረበው? አሳብን በማብራራት ከጀዋር እበልጣለሁ ለማለት ነውን? ጀዋር ዘረኛ እንዳይባል ለማማለድ ነውን ? በዚህ ሰበብ ወደ ጀዋር መጠጋት የሚያስገኝ  ጥቅም እንዳለ ታይቶት ይሆን? ከጀዋር ጎን የቆምኩ  ሰው ነኝ ለማለት ነውን? ወዘተርፈ፤ ለዚህ መልስ በፌስቡኬ ሹክ ለሚለኝ ሰው በታርክ መዝገቤ እመዘግበዋለሁ ።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *