Getachew Reda
Uncategorized

ጌታቸው ረዳ የጠራውን ስብሰባ የትግራይ ወጣቶች ረግጠው ወጡ

ጌታቸው ረዳ የጠራውን ስብሰባ የትግራይ ወጣቶች ረግጠው ወጡ ጌታቸው ባለበት ደርቆ ቀረ

አቶ ጌታቸው ረዳ በመቀለ ከተማ የትግራይ ወጣቶች ህብረት አባላትን በወቅቱ የትህነግ አቋም ላይ ለማወያየት  ስብሰባ ጠርተው የነበረ ሲሆን፤ የመደመር ፍልስፍናን ና በብልፅግና ፓርቲን መቀላቀልን አስመልክቶ ትህነግ/ህወሃት የማይቀበለው መሆኑን ና አስፈላጊ ከሆነም ሉአላዊት ትግራይን እስከመመስረት እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑን አስመልክተው እየተናገሩ ባሉበት የስብሰባው ታዳሚ ወጣቶች አቶ ጌታቸው ኃሳባቸውን ሳይጨርሱ የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል። አቶ ጌታቸውም ልዩነት ካላችሁ እባካችሁ ተረጋጉና እንነጋገርበት ብለው እየተማፀኑ ባሉበት፤ ከተሰብሳቢ ወጣቶች መካከል #ክፍሎም #አብርሃ የተባለ ወጣት ከመድረክ ሳያስፈቅድ ንግግር አደረገ ።

የትግራይ ህዝብ ወልዶ፣ አዝሎ አሳድጓችሁ ለአካለ መጠን አደረሳችሁ። እናንተ ግን ውለታውን ከመክፈል ይልቅ ዞር ብላችሁ ሳታዩት በህዝቡ ስም ስትነግዱ ኖራችሁ፤ዛሬ ቀን ሲጨልምባችሁ ለሰራችሁት ወንጀል መደበቂያ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አለያይታችሁ ለመኖር 27 ዓመት የዋሻችሁን ሳያንስ፤ ዛሬም የእናንተ አምላኪ ልታደርጉን አትችሉም! እኛ የትግራይ ህዝቦች የህወሃት አሻንጉሊት ሆነን የምንቀጥልበት ጊዜ አብቅቷል! እናንተ በሰራችሁት ግፍ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አቆራርጣችሁ ባርያችሁ ልታደርጉን አትችሉም! በቅርቡ እንኳን፤ በባህርዳር ስታዲየም በ70 እንደርታና በባህርዳር ከነማ ጨዋታ ጊዜ የባህርዳር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ ያለውን ፍቅርና ክብር በአይናችን አይተናል። እዚህ እናንተ የምትሉንና እዚያ ያለው ነገር እጅግ የማይገናኝ የውሸት ጉዞ እንደነበር አረጋግጠናል።

ብሎ በስሜት ከተናገረ በኋላ በፍጥነት አደራሹን ለቅቆ ሲወጣ ሁሉም ወጣቶች ተከትለው ወጥተው በመሄዳቸው አቶ ጌታቸው በሃፍረት ተሸማቅቆ ብቻዉን አፉን ከፍቶ እንደቀረ በስበሰባው ታዳሚ የነበረው የገጻችን ተከታይ ከመቀለ ልኮልናል።
ፍቅር ያሸንፋል!! ማለት ይህም አይደለ?

እናት ሀገር

Source: ZeHabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *