የህወሓት
News

ለህወሓት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ ከትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰጠ ምላሽ

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያ ነው የተባለ አስቸኳይ ጉባኤ ከታሕሳስ 25 እስከ 26፣ 2012 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን ይኸንን በተመለከተም ያወጣውን መግለጫ ፓርቲያችን ተመልክቶት የሚከተለውን መግለጫ ማውጣት ግድ ብሎናል።

በመሰረቱ “አስቸኳይ ጉባኤ” ተብሎ የተጠራው ጉባኤ በተከታታይ ከተካሄዱት ቀደምት ሁለት ስብሰባዎች የተለየ ነገር ያልታየበትና በይዘትም የህወሃት ቁንጮዎች የተለመደና ተመሳሳይ የውሸት፣ የማስፈራራት እና የማወከብ ባህሪያቸውን የተንፀባረቀበት ጉባኤ ነው። ይኸም የማደናገር ስብሰባቸው በሚመለከት እውነታው ምን እንደሆነና አንደምታው ምንድነው የሚለውን ለትግራይ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳወቅ የግድ ይላል።

በመሰረቱ ብዙ አቧራ እያነሱበት ያለውን የውህደት ጉዳይ ስንመለከት እነሱ ራሳቸው ይዘውሩት በነበረው የያኔው ኢህአዴግ ከአስር ዓመታት በፊት ጀምሮ ውህደቱ የሚያሳልጥ ሂደት ተጀምሮ በዚህ ዘርፍ የበቁ ምሁራንና ፖለቲከኞች ያሉበትን የአጥኚ ቡድን አቋቁመው ሂደቱን ጠብቆ ሲካሄድ መቆየቱ እና ጥናቱም መጠናቀቁ ልብ ይሏል። የህወሓት መሪዎች በባህዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ውህደቱ ዘግይቷል የሚል እሮሮአቸውን ሲያሰሙ ታሪክ መዝግቦታል።

ታድያ ጥናቱ እነሱ በቀየሱት መንገድ እና ህጉን ጠብቆ ተጠናቆ ሲያበቃ ለውህደት ሲጠሩ ለምን ተቃዋሚ ሁነው ቀረቡ? በኢትዮጵያ ህዝቦች እና በኢህአዴግ ውስጥ በተፈጠረው የለውጥ እና የአልገዛም ባይነት አመፅ የማእከላዊ መንግስት ስልጣናቸውን ሲያጡ ውህደቱን መቃውም ጀመሩ። በመሆኑም የህወሓት መሪዎች የሚያነሱት የመርህና የአሰራር ጉዳይ ሳይሆን ላለፉት 27 ዓመታት ያላገጡበትንና የጨፈሩበትን የማዕከላዊ መንግስት ስልጣን ማጣታቸው የፈጠረው ስሜት እንጂ የህወሓት አመራሮች የፓርቲ ሕገደንብ እንኳን የማይገዛቸው ዋልጌዎች መሆናቸው የ1993 ዓ/ም 12ቱ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ያባረሩበት ሕገወጥ ሂደት ማስታወስ በቂ ነው። የህወሓት አመራሮች ያለፈ የመንግስትነትም ይሁን የፓርቲ ታሪካቸውን በደንብ ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ የነሱን ፀረ-ዲሞክራሲያዊ እና አምባገነንነት ባህሪይ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብናል።

ሙሉውን መግለጫ ለምንበብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *