አቡነ ማትያስ
News

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ አባላት ክህነታቸው ተይዟል ሲል ቅዱስ ሲኖዶሱ አወጀ

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ከየካቲት 9 እስከ 11/2012 ዓ.ም ድረስ ያደረገውን አስቸኳይ ስብሰባ ተከትሎ ዛሬ ከሰዓት ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

የሲኖዶሱን መግለጫ በጽሁፍ ያቀረቡት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ በሚከተሉት ላይ የቅዱስ ሲኖዶሱን አቋም አሳውቀዋል።

የኦሮሚያ ቤተ-ክህነት አደረጃ ኮሚቴን በተመለከተ
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደረጃ ኮሚቴን በማለት የኦሮሚያ ቤተ-ክህነትን ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ሕገ-ወጥ እና ከቤተ ክርስቲያ እውቅና ውጪ የሚከናወን መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታውቋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ጥያቄን አወግዛለሁ አለ
“ከቤተ-ክርስቲያኒቱ ሕግ እና ደንብ ውጪ በመነሳሳት የኦሮሚያ ቤተ-ክህነት እናቋቁማለን በማለት በሕገ-ወጥ መንገድ በቅዱስ ሲኖዶስ ተባርኮ ጽላት ተሰጥቶናል በሚል ቤተ ክርስቲያን አቋቁመናል የሚሉት፤

1. ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፣

2. አባ ገብረማርያም ነጋሳ

3. መምህር ኃይለሚካኤል ታደሰ

4. ቄስ በዳሳ ቶላ

ቤተ-ክርስቲያኒቷ በማታውቀው መንገድ በአመጽ በመነሳሳት መዕመናንን ግራ እያጋቡ እና እያሳሳቱ ከቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ውጪ የክህደት ትምህርት ማስተማራቸው በመረጃ ተደግፎ ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡን ተከትሎ ከድርጊታቸው ተቆጥበው በንስሐ እስኪመለሱ ድረስ ከየካቲት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጣቸው ክህነት ተይዟል” ብሏል።

ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በቤተ ክርስቲያን ስም ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል ሲል ሲኖዶሱ መግለጫ አውጥቷል።

“ግለሰቦቹ ከጥፋት ድርጊታቸው ተጸጽተው ለመመለስ ከፈቀዱ ጉዳያቸው በድጋሚ ሊታይ ይችላል” ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ለግለሰቦቹ ከቤተ ክርስቲያኒቷ የተሰጣቸው ጽላት አለመኖሩን አስታውሶ ምዕመናኑም “ከእንዲህ አይነት ተሳስተው ከሚያሳስቱ ግለሰቦች እራሳቸውን፣ ኃይማኖታቸውን እና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ከምን ጊዜ በላይ እንዲጠብቁ ጉባኤው ያሳስባል።”

ከአምልኮ ቦታ ጋር በተያያዘ ስለተፈጠረው ግጭት
በአዲስ አበባ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአምልኮ ቦታ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ በነበረው ክስተት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶሱም “ጭካኔ ለተሞላበት ድርጊት” የፈጸሙ አካላት ላይ መንግሥት ጥብቅ ምርመራ በማድረግ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡና ውጤቱ ለምዕመናኖቻችን በሚዲያ እንዲገለጽ እንጠይቃለን ብሏል ሲኖዶሲ።

ከአምልኮ ቦታ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ‘ግጭት’ 7 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ
ከዚህ በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶሱ ለግጭቱ ምክንያት የሆነው ቦታ ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗ ለአከባቢው ነዋሪዎች ማምለኪያነት እንዲውል በተደጋጋሚ ለመንግሥትን ጥያቄ ስታቀርብ መቆየቷን አስታውሷል።

ሲኖዶሱ መሬቱ ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንዲሰጥ ጥያቄውን አቅርቧል።

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ካህናት እና ወጣቶች በእሥራ ላይ እንደሚገኙ ያስታወሰው ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ “እስር ላይ የሚገኙት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን” ብሏል።

መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ
ቅዱስ ሲኖዶሱ ኦኤምኤን፣ ኦቢኤስ እና ኤልቲቪ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር እና ልዕልናዋን የሚነካ መረጃ እያሰራጩ ነው ብሏል።

ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . .
የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ከመገናኛ ብዙሃን ደንብ እና ሕግ አኳያ በሕግ እንዲየቁና ከእንዲህ አይነቱ ሕገ-ወጥ ተግባር እንዲታቀቡ እንጠይቃለን ብሏል ቅዱስ ሲኖዶሱ።

የአረብ ኤሜሬቶች የቤተ-ክርስቲያን ግንባታ
ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበርካታ ዓመታት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት ቦታ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ለሚመለከተወ አካል ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰው፤ በቅርቡ የቤተ ክርስቲያኗ ጥያቄ ምላሽ ማግኙትን አስታውቀዋል።

የቤተ ክርስቲያኗ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጠቅላይ ሚንስር ዐብይ አህመድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በማስታወስ፤ ሲኖዶሱ ምስጋናውን አቅርቧል።

“ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ወደ መንበረ ስልጣኑ ከመጡ ወዲህ የቤተ ክርስቲያኒቷን ጉዳይ የራሳቸው ጉዳይ አድርገው እየፈጸሙት ያለው አኩሪ መንፈሳዊ ተግባር ቅዱስ ሆኖ ስላገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ምስጋናውን አቅርቧል” ብለዋል።

ምንጭ፨ ቢቢሲ የአማርኛ ክፍል

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን ወደ ቤታቸው እየሸኘ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *