TAND
News

የህወሓት አመራርና “የፌደራሊስት” ሃይሎች ጥምረት፣ “ያላቻ-ጋብቻ”

የፌደራሊስት ሃይሎች ነን የሚሉ 35 “ድርጅቶች” በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ከጥር 4-5 ቀን፣ 2012 ዓ/ም
ተሰብስበው ጥር 6 ቀን፣ 2012 ዓ/ም የህብረ-ብሄር ፌደራሊስት ሃይሎች ጥምረት፣ ዓላማ፣ ስትራተጂና የትግል ስልት
(ማኒፌስቶ) አፅድቀዋል። 80% የትግራይ ህዝብ “ሴፍቲ-ኔት” በተባለው ድር ተጠርንፎ በእርዳታ (ምፅዋት) እህል
አስከፊና አስፋሪ ኑሮ እየገፋ ባለበት ወቅት ከድግሱ ወጪ ጀምሮ እስከ የጥምረቱ ቅንብር የቻለው የህወሓት አመራር
ነው። ለመሆኑ የህወሓት አመራር ይህ “የፌደራሊስት” ሃይሎች ጥምረት የሚለው ቅንብር እውነት ፌደራሊስት
ከመሆን ተነስቶ የመሰረተው ነውን? ዋናው ዓላማውስ ምንድነው? የሚሉት ጥያቄዎች ስናነሳ ለመልሱ ብዙ ርቀት
ሳንሄድ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ አገላለፅ “ፌደራሊዝምን የመሰረተው ህወሓት
ይመራዋል።” ይላልና።
ገና ከጅምሩ የአቶ አስመላሽ ህወሓት የመሪነቱን ብሎም የበላይነቱን እርካብ ስላወጀ፣ በእኩልነት መመስረትን
የሚጠይቀው የፌደራሊዝም መርሕ ድራሹ ጠፍቷል። ጥምረቱ የፌደራሊስት ስም ያጠለቀ እንጂ ይዘት የሌለው
“ያላቻ-ጋብቻ” መሆኑ ወደ ዝርዝር ሳንገባ መገንዘብ ይቻላል።
ቀጥሎ የተከሰተው አስገራሚ ጉዳይ አጠቃላይ የጥምረቱ የማንነት ስያሜ ላይ እንደ ጥያቄ ተነስቶ እንደ መከራከሪያ
ነጥብ ሆነ። “የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄር ፌደራሊስት ሃይሎች” የሚሉ ወገኖች ብቅ ሲሉ እነ አቶ አስመላሽና አጃቢዎቻቸው
(የመኢብን- መስፍን፣ የኦብኮ- ቶሎሳ ተስፋዬ፣ የኢዴአን- ጉዑሽ ገ/ስላሴ፣ የቅዴፓ- አጀበው ወርቅነህ፣ የኢድህ- ገብሩ
በርሄ፣ የኢኮፓ-ገረሱ ገሳ፣ የኦአግ- ዶ/ር ፋሪስ፣ የኢትፓ-ሰለሞን ታፈሰ፣ የሲአን- ዶ/ር አየለ አሊቶ፣ የአብሽ-አላምረው፣
የክሃህ-የማነ አሰፋ ወዘተ) የኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ መጨመር የለበትም፤ አያስፈልግም እንዲሁ “ህብረብሄር….ጥምረት” ብቻ ይባል ብለው አጥብቀው ተከራከሩ። ኢትዮጵያዊነትን መጠየፍ እርቃኑ የወጣ የሃገር ክህደት
ይሉታል ይህ ይመስላል። ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ አንዳንዶቹ ሃገር-ወዳድ ግለሰቦች “የኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ
ካልተሰጠው ከዚህ ጥምረት እንወጣለን ብለው ስለዛቱ የህወሓት አመራር እኩይ ዓላማው እንዳይጨናገፍ ከሚል
እሳቤ “የኢትዮጵያ” የሚለው ስያሜ ሳይወዱ ተቀብለውታል።
የዚህ “ጥምረት” ዓላማው ምንድነው? ስንል በሌላ አነጋገር የህወሓት አመራር ዓላማው ምንድነው? ማለትም ስለሆነ
በዚህ አግባብ መጠየቁ ጉዳዩን በሰላ መልኩ ለመረዳት ያስችላል።
በማኒፌስቶው (ከገፅ 8 እስከ 11) እንደተዘረዘረው የጥምረቱ ዓላማዎች፣
ሀ/ ሰላምና የህግ የበላይነት በሀገራችን ማስፈን፣
ለ/ ህገ-መንግስቱን መጠበቅ፣ መከላከልና ህገ-መንግስታዊ ስርኣቱን ማስቀጠል
ሐ/ ህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱን ማስቀጠል፣
መ/ የ2012 ዓ/ምቱ
አገር አቀፍ ምርጫ በምንም ዓይነት ምክንያት እንዳይራዘምና እንዳይጭበረበር
መታገል………. እያለ ይቀጥላል።
“በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ!” አለ አያ ጅቦ ሆነና፤ እነዚህ ከላይ በከፊል የጠቀስናቸው እንደ ዓላማ
የተቀመጡት መርሆዎችን ሲያፈርስና ሲንድ የነበረው አካል ማን ሆኖ ነውና?! አሁን ደርሶ ጠበቃ ሊሆን የሚሞክረው።

ሃገራችን ከባድ ቀውስ ውስጥ የከተተው የነዚህ መርሆዎች ለ27 ዓመታት በተከታታይ ማኮላሸት ያስከተለው ጦስ
አይደለም እንዴ?
መራራ ሃቁ እንዲህ ነው!
1ኛ- የግለሰቦች የበላይነት በመስፈኑ– የህግ የበላይነት ቦታ አጣ። ህግ በግለሰብ የሚቸር፣ በገንዘብ የሚተመን ሸቀጥ
ሆኖ አረፈው። ይባስ ብሎም ህግ ደላላዎች እጅ ወደቀች። ነብሰ-በላ ደላላዎች የሀገሪቱን ፖለቲካና ኢኮኖሚ
በቁጥጥራቸው ስር አስገብተው በቀላሉ የማይሽር ቀውስ ተፈጠረ። ይህም ለስርዓት አልበኝነት በር ከፍቶ አስነዋሪ
የመንጋ ድርጊቶች እንድናይ ተገደድን።
ስለዚህ የህወሓት አመራር በየትኛው መለኪያ ነው የሰላምና የህግ የበላይነት መርህ አራማጅ ሆኖ ለመቅረብ
የሚከጅለው?
2ኛ- “የአሳ ግማቱ ከአናቱ” እንዲሉ ሕገ-መንግስቱን መጠበቅና ማስከበር ተቀዳሚ ስራቸው ማድረግ የነበረባቸው
የህወሓት አመራር እራሳቸው ሕገ-መንግስቱን እየጣሱ ባሻቸው ሰዓት ሕግ ተብዬ ማዘዣ እያወጡ ተፎካካሪ
ፓርቲዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በአጠቃላይ ዜጎችን ሲያፍኑ፣ አስረው ሲያሰቃዩ፣ ሲገድሉ እና
በሙስና ተነክረው ያለአግባብ ሲበለፅጉ የኖሩ አይደሉም እንዴ?! አሁን በምን ተአምር ወይም መለኪያ ነው ለሕገመንግስታዊ ስርዓቱ ተሟጋች መስለው የሚቀርቡት። የራሳቸው ግምገማና የራሳቸው አመራር አባል የነበሩ አቶ ብርሃኑ
ፅጋብ የፃፉት “የኢህአዴግ የቁልቁለት ጉዞ” በተሰኘው መፅሀፋቸው እንደሚያስረዱት በሕገ-መንግስቱ ጥሰትና በሙስና
መስፋፋት ዋናው ተጠያቂዎቹ የህወሓት አመራር ለመሆኑ ፍንትው አድርገው ስላስቀመጡት ሌላ ማስረጃ ፍለጋ
መሄድም የለብንምና። ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማስቀጠል የሚለው ዲስኩር ተራ ማጭበርበር ነው ብለን
እናልፈዋለን።
3ኛ- ህብረ-ብሄራዊ ይሁን ሌላ ዓይነት ፌደራል ስርዓት የሚዋቀረው በአባላቱ ፍላጎት፣ እኩልነታዊና ቀጥተኛ ተሳትፎ

ወደ ዋናው ጽሁፍ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *