የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ
News

ከሃዲው የህወሃት ቡድን የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳሳት በሀገሪቱ ዳግም ስልጣን መጋራት ይፈልጋል … አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

የከሀዲው የህወሃት ቡድን አመራሮች ዓለምአቀፉን ማህበረሰብ በማሳሳት ላለፉት ወንጀሎቻቸው ከቅጣት ለማምለጥና በድርድር ስም ዳግም ወደ ስልጣን መምጣት እንደሚፈልጉ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በፎሬይን ፖሊሲ ድረገጽ ላይ በወጣው ጽሁፍ ገልጸዋል።
ላለፉት 27 አመታት ሃገሪቱን በተንኮል ያስተዳደረው የህወሃት የጥፋት ቡድን በታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ተገፍቶ ሲወድቅ አለም አቀፉን ማህበረሰብ አሳስቶ ዳግም ወደ ስልጣን ለመምጣት እቅድ ስለመንደፉም በጽሑፋቸው አብራርተዋል።

በሰላም ስምምነቶች ወቅት የግጭቶች ትክክለኛ ባህሪና አባባሽ ምክንያቶች እንዲሁም ተሳታፊ አካላት ተዘርዝረው ስለማይታዩ በርካታ ስምምነቶች ዋጋ ቢስ ስለመሆናቸውም ነው የገለጹት።

ከሀዲው የህወሃት ቡድን ያለፈው ጥፋቱንና የሰራው ወንጀል እንዳይጋለጥ የሚፈልገው፤ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት እንዲያስችለው ከፌዴራል መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ በመግባትና በድርድር ስም ስልጣን በመጋራት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ዳግም የጥፋት ተግባሩን ለመፈጸም እንደሆነ ነው የጠቀሱት።

ቡድኑ ይሄን እቅዱን ለማሳካት ሶስት መንገዶችን እየተከተለ እንደሆነ ያብራሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያው በድርድርና በስልጣን መጋራት መፍትሄነት አለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳሳት ያለፉ ወንጀሎች ሁሉ እንዲሰረዙ ማድረግ ነው።

እሳቸው እንደገለጹት ሁለተኛው አንዳንድ የውጭ ሃገራት ተንታኞችን ከፊት በማሰለፍ ራሱን ሰላማዊ አስመስሎ በማቅረብ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ጥላሸት መቀባትና የህግ ማስከበሩን ሥራ ማሳነስ ነው።

ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት ላይ ለበርካታ አስርተ ዓመታት ሲዘራ በነበረው ልዩነትና መከፋፈል ምክንያት ህዝቡና የፌዴራል መንግስቱ ከህወሃት ልዩ ሃይል በሚሰነዘርበት ጥቃት በቀላሉ ይሸነፋል የሚለው እቅድ እንደነበረም ገልጸዋል፡፡
የቡድኑ ዓላማም ግጭቶቹን ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ብሎም ወደ ክፍለ አህጉሩ በማዛመት የፌዴራል መንግስቱንም ሆነ የአካባቢውን ሃገራት ባልተቋረጠ የእርስበእርስ ጦርነት እረፍት መንሳት እንደሆነ የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፤ ህወሃት በሁሉም አቅጣጫዎች በሮች ስለተዘጉበት ይሄን የማድረግ አቅሙ እጅግ ደካማ ነው ሲሉ በጽሑፋቸው አስፍረዋል።

ከመቀሌ በስተጀርባና ከመቀሌ ወዲያ ማዶ – ዶ/ር መኮንን ብሩ

Source: ZeHabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *