Raya
News

ኢትዮጵያ፣ በስምሽ የራያ ህዝብ ሰቆቃ

ከዚህ በታች ያሉትን መረጃዎች ከራያ ራዩማና ከጎዳዳ ፌስ ቡክ የተገኘ መሆኑ አንባብያን እውቅና ከምስጋና ጋር ይስጡልን፥፥ ወደፊት ለህዝብ መድረስ ያለባቸውን መልዕክቶች በ በትልኩልን በቀጥታ ይደርሰናል፥፥

Rayarayuma
ራያየ !!
ሲቃ እምባሽን ባላብስ
ውለታ የፍቅርሽን ባልመልስ
ሲከፋሽ
ሲጨንቅሽ
እያየሁ እየሰማሁ
ጆሮ ዳባ
ከተቻለኝ
ሰው አትበይኝ
ሰውም አልሆንኩ ።
Daood Nh
 
 
 
ራያ ላይ !!
ጥቁር ሸማ የለበሰ
ለምለም ምድር ተዘርግቷል
ምድሩ ውስጥ
ህዝብ አንቀላፍቷል
ህዝቡ ውስጥ
ታሪክ ተኝቷል
ታሪክ ውስጥ
እውነት አዛግቷል
እውነት ውስጥ
አርነት አለ
ይነጋል እንዲህ እያለ ።
Nati
Rayarayuma-
ይቅር በይኝ
ልጅ ሁኜልሽ በእቅፍሽ አድጌ
ዛሬ ሰው ሀኜ እንባሽን አለመጥረጌ
ይቅር በይኝ
ሰነፍ ነኝ ልጅሽ አደራሽን የቀረጠፍኩ
እንቅልፍ አጥተሽ
እንቅልፍ ጣለኝ ጎኔን አሳረፍኩ
ምኑን አረፍኩ ሲነጋ አፈርኩ።
ይቅር በይኝ
ባዶ ሆድሽ እየታየኝ የአንጀትሽ እጥፋቱ
እራፍ አጥተሽ
መራቆትሽ እያወቅኩኝ እርዛቱ
ምን ጠቀምኩሽ ሁኜ ከንቱ
መች ደገፍኩሽ ሁኜ ብርቱ
ርሀቤን ሽሬ ደርቤ ለበስኩኝ
ይቅር በይኝ መች ጠቀምኩኝ።
እንዳላደግኩ እንዳልፈሰስኩ ባንቺ መንገድ
ጥቃትሽን ሳልመክተው ድኩም አቅሜ ቢንገዳገድ
ተስኖኝ ነው ይቅር በይኝ ስለመውደድ።
ጥር 30/2014 ዓ.ም

Mohammed Kenya

ከአላማጣና አካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቆቦና ሌሎች ከተሞች እየገቡ ነው።
የሰብዓዊ ቀውሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው።
የመንግሥትን ትኩረት ይፈልጋል‼

Rayarayuma
Rayarayuma

Abuki Musa

በቆቦ ከተማ በተለያዩ ት/ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ የራያ አላማጣ ዋጃና ጥሙጋ ተፈናቃዮች በምግብ እጥረት ምክኒያት ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንዲደርግላቸውም ጠይቀዋል።
ከራያ አላማጣ ፤ ከሙኽኒ፤ ከኮረም ፤ ከዋጃ እና ከጥሙጋ ከሀያ ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሕወሓትን ጥቃት በመሸሽ ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ገብተዋል ።
አብዛሀኛዎቹ ሕጻናት እና ሴቶች ሲሆኑ ወጣቶች እና ጎልማሶች በሕወሓት ታጣቂዎች እየተጋዙ የጉልበት አግልግሎት እየሰጡ መሆኑን እየተሰማ ነው።

Rayarayuma
Rayarayuma

Moha Mohammed is feeling sad.

ትኩረት ለራያና ለዓፋር ህዝብ የመንግስት ዝምታ እስከመቼ ነው!!

Moha Mohammed is feeling sad.

ትኩረት ለራያና ለዓፋር ህዝብ የመንግስት ዝምታ እስከመቼ ነው!!

RayaRayuma

Eyassu Berhie Chekole  · በራያ ህዝብ ላይ በትህነግ የሚፈፀሙ ግፎች በትንሹ

1. የትህነግ ወታደሮች ህብረተሰቡን በቀንም በለሊት መዝረፍ ፣መድፈር ፣መግደል ፣ማሰር (የት እንደሚወሰዱ አይታወቅም)

2. በሓይል ወስን (ከቤት ወንድ ይሁን ሴት እስከ ሳስት ልጅ እንዲዘምቱ ማስገደድ) ፡ መዋጮ(ገበሬው እስከ አንድ ኩንታል ጤፍ እንዲሁም በብር 600-1500 ) አውጣ

3. ህብረተሰቡ የጤና ግልጋሎት አንዳያገኝ ማረግ በአሁኑ ሰዓት አዲስ ወረርሺኝ ተከስቷል ልክ ወባ አይነት ዝምድና ያለው ። በአሁኑ ሰዓት ሆስፔታሉ ስራ አቁሟል:: የሚወልዱ እናቶች ፡ የቆየ ህማም ( ስኳር ፡ ደም ግፊት ፡ HIV እና የልብ ህመምተኞች) መድኃኒት እጦት እየረገፉና እየተሰቃዩ ነው፡፡

4. የኑሮ ወድነቱ በርበሬ 1500 ፣ጨው 330 ፣ዘይት 5 ሌትር 1700፣ ሻማ 70፣ ሳሙና ላይፍ ቦይ 50፣ኪርቢት 25 ወዘተርፈ …

5. በፈለጉበት ሰዓት መብራትና ወሃ ማጥፋት ፡ ህብረተሰብን ወሃ እንዳያገኝ በተላላፊ በሽታ እንዲጠቃ ማድረግ

6.አከባቢው የጦር ቀጠና እንዲሆን ራያ ውስጥ በዶዘር የተቆፈረ ከባድ ምሽግ የተሰራባቸው አካባቢዎች ዝርዝር ፤ ጨርጨር፣ ባላ፣ ገደራ ጎቱ፣ ኩቢድርባ፣ ኅብረት፣ ህሞ( ማሩ)፣ ከረን ኩቤ ጣፌ፣ ጫማሮ፣ ቃርሶሌ፣፣ ታኦ፣ አዲስቅኝ፣ ባሶ፣ ኮስም፣ባንድራ፣ ጋውር ሻምተ፣ ገንዳ ጃላ፣ ጎልአጆ፣ ጋርጃለ እና ጠጠቻ ናቸው።

7.ከጋርጃለ እስከ ፋጫ ሃራ በዶዘር የተሰራው ምሽግ ስፋቱ መኪና ያስኬዳል። ዲማ፣ ቆጫ፣ቃጅማ፣ ኩትቸ፣ ስፍራ አሞራ፣ ዓዳቦ ጎልጃ፣ ጋራካሱ – ጽልያ በተጨማሪ ከባድ መሳሪያና መድፍ የጠመዱባቸው አካባቢዎች ናቸው።

8.ህዝቡ በድሮን እንዲጨፈጨፍ ከተማው (ሆቴል ፣ትምህርት ቤት ፣ ፔንሲዮን )ውስጥ ካምፕ ማድረግና አዛዦች ማረፍያ ማድረግ እንዲሁም ገበያ ላይ ያሉት መጋዘኖች የጦር መከማቻ ማድረግ እናም በድሮን ህዝቡ እንዲጨፈጨፍ በማድረግ ፕሮፕጋንዳ መስራት (ካሁን በፊት በገበያና በንግድ ቦታና ሆቴል ቤቶች የተደረገው የንፅሃን ጭፍጨፋ በድምፅ ወያኔ ለፕሮፕጋንዳ ሲያውሉት ተመልክተናል)

Rayarayuma
የኔፓሏ ታራል እና የራያ ክፍል መመሳሰል
.
ታራል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የምድራችን ገሀነም የሚል ስም አላት። ይችን ግዛት አለም አያቃትም።
 
በመጣጥፎች ብቻ ነው የምትታወቀው። የአለማችን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጭምር ይሏታል። እዛች ግዛት ውስጥ ያሉ አባቶችና እናቶች ልጅ የሚወልዱት ለኩላሊቱ ሲሉ ነው።
 
የታራል ግዛት እናት ፈጣሪያዋን የምትለምነው ጌታየ ሆይ እባክህን ሁለት ኩላሊ ያለው ልጅ ስጥኝ ብላ ነው።
 
ግዛቷ በኔፓል አገር ክልል ውስጥ ትሁን እንጅ የኔፓል መንግስት ያችን ግዛት ከ1960 ወዲህ ምንም አይነት መንግታዊ መዋቀር ሰርቶ መርቷት አያቅም። ግዟቷም ለመንግሥት የምትሰጠው ምንም ነገር የላትም።
 
የአለማችን ክፉ ማፊያዎች የሚገኙትም እዛች ግዛት ውስጥ ነው። ማፊያዎቹ ሲፈልጉ ወደ ሩሲያ ወይም ባንግላድሽ ወይም ሲሪላንካ ወይም ወደ ቻይና ህንድ ይሄዳሉ። ታዲያ ማፊያዎቹ ባለረብጣ ዶላር ባለቤት ናቸው።
 
እነዚህ ማፊያዎች ኑሯቸውን የሚመሩት በኩላሊት ንግድ ነው። የታራል ኗሪዎችም የሚታወቁት ኩላሊት በማቅረብ ነው። ታራል ላይ በሁለት ነገር ትሞታለህ አንድም ኩላሊትህን ሸጠህ እሱን ተከትሎ በሚመጣ በሽታ፣ ሁለትም በምግብ እጥረት የወዳደቁ ምግቦችንና ቅጠሎችን በልተህ በመመረዝ።
 
ይች ግዛት የአለማችን ጉድ የሚያሰኝ አሰቃቂ ስራዎች የሚሰሩባት ግፍ እንደ ሰንደቅ አላማ ቆሞ የሚታይባት ግዛት ነው።
ወደዛች ግዛት የሚገባ ማንም የለም። የገባም አይወጣም። እድለኛው የስካይኒውስ ጋዜጠኛ ጀፍሪ ፓልት ብቻ ወደ ግዛቷ ገብቷል። የግዛቲቱን ሁኔታ ዘግቦ ጋዜጦኞቹ በአንድሺ ዶላር ሲቸበቸቡ ነበር። አለም የማያወግዘው የግፍ ምድር የሚል ስም አላት።
 
በአገራችንም ውስጥ ራያ የሚባል የግፍ መሬት አለው። ህወሓት ሲፈልግህ የኔ ነህ፣ ሲያሻው አላቅምህም፣ ከመሬትህ ልቀቅ እያለ ንብረቱን ሂወቱን ማንነቱን ሁሉ እየቀማ ያሰቃየዋል።
 
የሰሞኑ ደሞ ለየት ያለ ነው። ያለ የለለ የቂም ብትሩን እያሳረፈበት ነው። የራያ ቆቦን ግማሹን ክፍል ይዞ ራያ አለማጣን የዋግህምራን ሦስት ወረዳን ጨምሮ በህወሓት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።
 
ከራያ አላማጣ ብቻ በዚህ ሳምንት 30ሺ ሰው ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ገብተዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *