Opinion

መደራደር ያለብህ ከተበደለ ወገን ጋር ነው

Mulugeta Lemechaሙሉጌታ ለሜጫ

ወይ ድርድር !!! ምን ጉድ ነው የገጠመን።

እውነቱን ለመናገር የኢትዮዽያን በዚህ መጠን መንኮታኮት ስመለከት የጌታ መምጫ የቀረበ ይመስለኛል። ለአፍሪካ የሚበቃ ጦር ተገንብቷል ተብለን ነበረ ።

– ራሺያ ሰላም ጠልታ ይሆን ግን ለታላቋ ራሺያ ክብር ብላ ነው መላ ምእራብአውያንን ገጥማ እየተፋለመች ያለች ።

– ዩክሬንም ለሀገሬ ክብር ብላ ይሆናል እንጅ አገሮቱ አመድ እስክትሆን እየተፋለመች ያለችው እንጂ ከራሺያ ጋር በሰላም መኖር ትችል ነበረ።

– የሱዳኑ ወጣት ጀነራል ሰላም አልገባው ብሎ ነው? ግን ለታላቋ ሱዳን ተጨንቆ ነው። – ኤርትራ ከአሜሪካ ጋር መታረቅ እና ዶላር መቀበል አቅቷት ነው ግን ለሀገሯ ክብር ብላ ነው።

– ትንሿ ሰሜን ኮሪያ ለክብሯ አሜሪካንን ታንቀጠቅጣለች።

– ኢትዮዽያ ለሀገሯ ክብር ብላ አይደል በጦር በጎራዴ ተፋልማ አሸንፋ በክብር የኖረችው።

ሰላም ማለት ለሀገር ክብር ወድቆ ማሸነፍ እንጂ እንደኛ ከባንዳዎችና ከሀዲዎች ፣ የሰው ልጆችን ንፁሀንን ምንም የማያውቁ ህፃናትና ከእርሻ በስተቀር ምንም የማያውቁ ሰዎችን በጅምላ እየገደለ ደማቸውን ሲጠጣ የከረመን ወሮበላ ቡድን መደራደር ለሰላም ዋጋ መስጠት ሳይሆን ደንታ ቢስነትና አገርንና ህዝብን ማዋረድ ነው። ሰው በሰላም ስም ከዳቢሎሰ‍እ ጋር ቢቀልድ ፈጣሪ ግን የንፁሀን ደም ወደ መአበል ቀይሮ ቁጣን ያመጣል።

ልብ በሉ !!!

ዘራፊው ወያኔ ጮማና ውስኪ አስክሮት አላስቆም አላስቀምጥ ብሎት “እንበር ተገዳላይ” ጦርነት ባሀላዊ ጨዋታችን ነው በማለት በትግራይ ምድር አብሮት የኖረውን ወዳጁን የኢትዮዽያ መከላከያ ሰራዊት አገር አማን ብሎ በተኛበት ጥቅምት 24 በአሰቃቂ ሁኔታ የሴት ወታደሮችን ጡት በመቁረጥና ጠ/ሚ አብይ አህመድ እንደነገሩን የሴት ወታደሮችን ብልት በሳንጃ በመውጋት ጭምር ቁጥሩ 20,000 የሚሆን ወታደር ረሸነ።

በዚያ ምክንያት የተጀመረ ጦርነት ወያኔ ጠላቴ የሚለውን አፋርና አማራ አካባቢወችን በጭካኔ ጨፍጭፎ ከባድ ወንጀል ፈፀመ። በወያኔ ምክንያት የተጀመረ ጦርነት የሚሊየን ወጣቶችን ህይወት ቀጠፈ። ከዚያም መሬት ልትሸከመው የማትችለውን ወንጀል ፈፅሞ ሲያበቃ እንደራደር ሲል መንግስት የሚባለው ጉድ በደስታ ተቀብሎ እሽ ሲል ማንም አልቀደመውም። ከዚያም አገር የሚመራ ሳይሆን የሁለት ጎረምሳ ጠብ በሚመስል መልኩ ጥቂት ተላላኪዎች ተሰባስበው ተስማሙ ተባለና በአንድ ሚሊየን ወጣት ደም ላይ እየዋኙ እነሱ በደስታ ተቃቅፈው ይመራረቃሉ ይሸላለማሉ ይገለፍጣሉ።

በእውነት አገሬ እዚህ ደርሳለች? እንጃ የሰው ልጆች ደም እየጮኸ ነው። ቢያንስ ወንጀለኛ መጠየቅ የለበትም? ብቻ ሀጢያተኛው የሰው ልጅ ደንታ ቢስ ቢሆንም በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ፈጣሪ እየሱስ ክርስቶስ የልጆቹን ደም ደመከል አያደርገውም።አንድ ቀን ማእበል ሆኖ ይመጣል።

ሌላው ኦነግ ሸኔ የሚባለው ነው። ከኤርትራ ሲመጣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነበረ ነገር ግን ጫካ ገባ ተባለና ምንም የማያውቁ አርሶ አደሮችን በዘር እየለየ በጅምላ ፍጅት ሲፈፅም 5 አመት ሆነው ። በአምስት አመት ውስጥ በምድራችን ላይ አሰቃቂ የሰው ልጆች ፍጅት የተፈፀመው በዚሁ ኦነግ ሸኔ ነው።ከ2 ሚሊየን በላይ ሲፈናቀል በመቶ ሺዎች ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።አሁን ይህ ወንጀለኛ ቡድን ልደራደር ብሎ ታንዛኒያ ሄደ ተብሎ እንደስኬት ተነገረ። ምን ቀረኝ ብሎ እንደሚደራደር ባላውቅም እንደጎርፍ የፈሰሰው የሰው ልጆች ደም ፈጣሪ ጋ ደርሶ ማእበል ሆኖ ሁላችንንም ያጠፋናል። የፈጣሪ ቁጣ ዶፍ ሆኖ ሊመጣ ቀን እየቆጠረ ባለበት ሰአት መንግስት ሊደራደር መሆኑን ሰማን። ለመሆኑ መንግስት አንድ ሚሊየን ህዝብ ከበላው ወያኔ ጋር በደስታ እየተሸላለሙ ሳለ አዲስ አበባ ላይ ከሌላኛው ወንጀለኛ ጋር ሊደራደር መሆኑን በኩራት ነግሮናል።

እሽ ከወንጀለኞች ጋር እየተደራደረ ነው መንግስት መቼ ነው በዘሩ ምክንያት እና በመንግስት ድክመት ምክንያት ወለጋ ከአለቀው ህዝብ ፣ በወያኔ ለአለቀው ህዝብ ፣ በዘሩ ምክንያት ቤቱ ከሚፈርሰው ህዝብ ፣ በዘሩ ምክንያት በጅምላ እየታሰረ ለአለውና እየተሳደደ ከሚገኘው ማህበረሰብ ጋር ለድርድር የሚቀርበው እና የሚታረቀው?

ከኢትዮዽያውይነቱ እንዲወርድ ተደርጎ አማራ ተብሎ እንዲጠራ ታርጋ ተለጥፎለት በወያኔ አማራ የሚል ክልል ስም ተሰጦት በየደረሰበት ሲገደልና ሲፈናቀል ዘመናት አለፉ። አሁን ባለው አሰላለፍ ግን ክልሉ ልብ ያለው ጀግና ወኪል ቢኖረው ኖሮ ገና ወለጋ ላይ አንድ ሰው መሞት ሲጀምር ሱሪ የታጠቀ መሪ ለሚመራው ክልል ተቆርቋሪ ወገን ኑሮት ቢሆን ህዝብን አስተባብሮ ህዝቤን አትግደል ያለዚያ ወለጋ ገብቸ ህዝቤን እየገደለ ያለውን ቦዘኔ ልክ አስገባለሁ የሚል ጀግና ቢፈጠር ኖሮ መንግስት አጎንብሶ ለምኖ በድርድር ንፁሀንን ከሞት እና ስደት ሰው መግደሉን እና ማፈናቀሉን ያቆም ነበረ። ለምሳሌ እስኪ ተቆርቋሪ ወኪል ያለው የትግራይ ህዝብ አንድ ሰው በኦነግ ሸኔ ተፈናቀለ ወይም ተገደለ ሲባል ሰምታችኋል? ምክነ‍እያቱም መንግስት የትግረ‍ኣይ መሪዎችን ይፈራል። አሁንም መንግስት ከበደለው ህዝብ ጋር ቁጭ ብሎ መደራደር እና ለአጠፋው ጥፋት ሀላፊነቱን መውሰድ አለበት እንጅ ከወንጀለኛ ጋር መሳፈጥ ትርጉም የለውም ።

ይህችን ታላቅ አገር መቀለጃ አታድርጓት። በየትኛው አለም ነው መንግስት የሚባል የአገር መሪ ትልቅ ጦር ያለው በሀገር መከላከያ ጦር ላይ አደጋ አድርሶ ከበላና ሰላማዊ ዜጎችን ሲጨፈጭፍ ከከረመ ማፍያ ቡድን ጋር በፍቅር ሲያብድ የሚውለው? አልገባኝም።

ይልቁንስ ሳይረፍድ ከበደላችሁት ህዝብ ጋር ተደራደሩ ያለዚያ ግን የድርድር እድልም ላታገኙ ትችላላችሁ። አትሰሩ ፣ አትዝረፉ አታፈናቅሉ ። አሁን ቀይ መስመር እየታለፈ ይመስለኛል። የሰው ልጅ መጨረሻ ደረጃ ደርሶ ተስፋ ካሳጣሀው እሱ ጠፍቶ አንተ የምትኖርባት መሬት ትቶልህ አይጠፋም። ከኖርህ በጋራ ነው ከጠፋህም አብረህ ነው። የክልል አጥር አያድንህም ኢትዮዽያን አንተን በሚመች መልኩ መከለል ፈፅሞ አትችልም ምክንያትም የሁሉም ሰው ውጤት ናት ኢትዮዽያ ። እኛ ኢትዮዽያውያንን በሚመቸን መልኩ ነው በኢትዮዽያ ተከባብረን መኖር ያለብን። ልክ አንተ ኢትዮዽያን እንደ ዳቦ ጠፍጥፈህ የሰራሀት ይመስል መሬት ሁሉ ያንተ ብቻ መሰለህ። ግን አይደለም ኢትዮዽያ በሁላችንም ደምና አጥንት የተሰራች አገር ነች። የድርሻየን ቆርሸ ልሂድ የምትለው ዳቦ አትምሰልህ።

ይልቁንስ ከወንጀለኛ ጋር ከምታሽቃብጥ የበደልኸውን ህዝብ ተደራድረህ ይቅርታ ጠይቀህ ሰላሙን ብትሰጠው መልካም ይመስለኛል።

ፈጣሪ ልቦና ይስጣችሁ አሜን

 

ምንጭ፥ የሙሉጌታ ለሜጫ ፌስ-ቡክ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *