Perspective

የሱማሌ ክልል  ፐሬዚደንት ሙስጠፌ ህመም ምክንያቱ ምን ይሆን?

Aklilu Wondaferewአክሊሉ ወንድአፈረው

 

“ የአፈንጋጭነት የተጠናወተው የሰነ አእምሮ መዛባት” ስያሜና  እና የቀደምት አምባገነኖች ልምድ: ባለፉት ሁለት ቀናት የሱማሌ ክልል ፐሪዚደንት አቶ ሙስጠፌ አህመድ “የአእምሮ ህመማቸው ተነሳባቸው” ተብለው ወደ የአእምሮ ሆስፒታል ለግዴታ ህክምና እንደተወሰዱ አፍቃሪ ህወሀት ዜና በማሰራጨት የሚታወቀው ኢትዮ ፎረም እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ አይን ያወጡ የብልጽግ ና ደጋፊዎች ሲያስተጋቡ ተደምጧል፡፡

እንደሚናፈሰው ወሬ ይህ የሆነው አቶ ሙስጠፌ በአዋሳ ከተማ የብልጽግናን ስብሰባ ይመሩ በነበረበት ወቅት ከድርጅታቸው አቋም ወጣ ያለ ብልጽግናን እጅግ የሚወቅስና የሚከተለውንም ፖለሲ የሚያጣጥል ንግግር ማድረግ እንደጀመሩ“የአእምሮ ህመማቸው ተንስቶባቸው ነው” በማለት ከመድረክ በአጃቢዎች እንዲወርዱ ተደርገው በጥድፊያ ወደ ሆስቲታል እንዲወሰዱ እንደተደረገ ይነገራል፡፡

ሙስጠፌ: ይህ ሁሉ ሲሆን የለም እኔ ደህና ነኝ ቢሉም የለም ይህን ያክል ተቃውሞና ትችት በብልጽግና ላይ ማቅረብ የአእምሮ በሽታ ከያዘው ሰው እንጂ ከጤነኛ አእምሮ የሚጠበቅ አይደለም ተብለው አጣድፈው እንደወስዷቸው ተነግሯል፡፡

ይህ ሁሉ ታዲያ እኔን ያስታወሰኝ የተለያዩ አምባገነን መሪዎች በነገሱባቸው ሀገሮች ለምሳሌም የሶቭየት ህብረት ፣ በ ምስራቅ ጀርመን በሩማንያ.. ወዘተ ሌሎችም አምባገነን መሪዎች ተቃዋሚዎቻቸውን ያፍኑ የነበረበት አንዱ መንገድ እንደነበረ ነው::

የሶቭየት መሪዎች በመንግስታቸውና በስርአቱ ላይ ግልጽ ተቃውሞና ትችት የሚሰነዝሩ ሰዎችን ጤነኛ እንዳልሆኑና ግልጽ ተቃውሞ የሚያካሂዱት የአእምሮ በሽታ ሰላለባቸው ነው በሚል እያስሩ ወደ ግዞት ይልኩ ከስልጣንም ያስወግዱ ነበር፡፡ ይህን ሲያደርጉ የሰነ አእምሮ ምርመራውን የሚያካሂዱት “psychopathological mechanisms of dissent “ ወደ አማርኛ ሲተረጎም “ አፈንጋጭነት የተጠናወተው የሰነ አእምሮ መዛባት “ የሚል ሳይንሳዊ የሚመስል ስም ሰጥተውት እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል፡፡

ለምሳሌ Vladimir Konstantinovich Bukovsky ቭላድሜር ቦኮቭስኪ የተሰኑት ራሽያዊ የፖለቲካ ተቃዋሚ ከ 1950 እስከ 1970ዎቹ ድረስ 12 አመታት በ አእምሮ ህመም ሆስፒታል እብድ ነህ ተብለው በግዳጅ እንዲቆዩ ተደርገው ነበር መንግስትንና የሚከተለውን የፖለቲካ እምነት የሚቃወሙ ሁሉ አሁን በሀገራችን “ጽንፈኛ ነውጠኛ አክራሪ” እንደሚባለው ሁሉ በሶቭየት አምባገነኖችም ጊዜ “የርእዮተ አለማዊ ስካር የተጸናወታቸው” (philosophical intostification ) የሚል ታርጋ በመለጠፍ ተቃውሟቸው እንዲኮላሽ እነርሱም ከህብረተስቡ እንዲገለሉ ይደረግ ነበር ፡፡  እንዲሁም በሩሜንያ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ 1984 በፊት 600 ስድስት መቶ ያክል ተቃዋሚዎች የአእምሮ በሽተኞች ተብለው በአእምሮ ሆስፒታል ታጉረው ይሰቃዩ ነበር፡፡

ይህንንም ተግባር ሳይንስን የተመረኮዘ ለማስመሰል በሀገሪቱ ውስጥ የሚታወቁ ምሁራን የፖለቲካ ባለስልጣኖች በሚፈልጉት መልክ ለተለያዩ የፖለቲካ ተቃውሞዎችን የተለያየ የሳይካትሪ መጠሪያ በማዘጋጀትና በእአምሮ ህመም ስያሜ በመስጠት ተቃውሞውን ሁሉ “የእብደት ምክንያት” አድርገው ያቀርቡ ነበር ፡፡

ለምሳሌ ሀገሪቱ የምትጓዝበት ሂደት መቀየር አለበት: ለውጥ ያስፈልገዋል የሚለውን ክፍል ” delusion of reformism” የተሀድሶ ቅዘት: : ሁለንተናዊ ተቃውሞና ስር ነቅል ለውጥ ያሻል የሚለውን ደግሞ (sluggish schizophrenia) “በተጓተተ ስክቲዞፍረንያ የተያዘ” የተሰኙ ስያሜዎች ተዘጋጅተው ተቃዋሚዎችን በተለያየ ጎራ መድበው ያጣጥሉ ነበር፡፡

ይህ አይነቱ የአእምሮ ህመም ስም በመስጠት የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን አንገታቸውን ቀና ያደረጉ ምሁራንን፣ የመብት ተሟጋቾችን ወዘተ ማሰቃየት ማሰር ከህዝብ ማግለል በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ብቻ ሳይሆን በምስራቅ ጀርመን :በሩሜንያ :በፖላንድ : በቻይና ወዘተ ለረዥም ጊዜ ተግባራዊ የተደረገ ዃላ ቀር የአምባገነኖች መሳሪያ እንደሆነ ታሪክ ይስተምረናል፡

የፐሪዚደንት ሙስጠፊ ጉዳይ በዚህ እውድ ሊመረመር የሚገባው ነው ወይም አይደለም ለማለት ለጊዜው በቂ መረጃ የለኝም፡፡ ለማንኛውም የሀገራችን ገዝዎች ወደዚህ ደረጃ ከተሸጋገሩ በእኛ ዘንድ አዲስ ምእራፍ በይፋ የሚከፍቱ ቢሆንም በአለም ታሪክ ግን ቢያንስ ከ 50 አመት በላይ የታወቀ ያረጀ ያፈጀ ታክቲክ ነው እና ብዙም የሚያስደምም ሊሆን አይገባውም፡፡

 

 

Source-ዋቢ

— Struggle against political abuse of psychiatry in the Soviet Union – Wikipedia
— The Political Uses of Psychiatric Labels | Psychology Today

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *