BirhanuAbegaz
Opinion Perspective

ግብፅ በአባይ ላይ የምታሳየው ትዕቢትና እብሪት የውሃ ጥቅሞቿን አያስከብሩላትም – ብርሃኑ አበጋዝ

ግብፅ በአባይ ላይ የምታሳየው ትዕቢትና እብሪት የውሃ ጥቅሞቿን አያስከብሩላትም ብርሃኑ አበጋዝ* (ግንቦት 9/2012)

በድንበር አላፊ ተፋሰሶች የመጠቀም ሉዓላዊ መብትን በተመለከተ የግብፆች ተረትና የሥነ-ልቡናዊ ዕምነት ከሁሉም ማስረጃዎች አንፃር በተቃርኖ የሚያዝ ከንቱ ስሜት ነው። በሥነ-ልቡና አገላለጽ እውን ያልሆነ፣ ማስገረሙ አንዳንዴም ማሳቁ ያልቀረ፤ ለላይኛው የናይል ተፋሰስ አገር ህዝቦች ዕድለ ቢስነት በጭራሽ የማያቋርጥ ደንታ አልባ የሆነ፣ በሌሎች ሃብት የብቻ ተጠቃሚነት አመለካከትን ያቀፈ ፤ እንዲሁም የቅኝ-ግዛታዊ ስሜት የለከፈው አዕምሯዊ የመዛባት ስብዕናን የሚያጋልጥ ነው።

ይህ ጉዳይ ደግሞ ነፃነት ወዳጆች በሆኑት ኢትዮጵያውያን ምልከታ በጎስቋላው ድህነታቸው አቅም ለሺህዎች ዓመታት ለዛሬዎቹ ሱዳንና ግብፅ ዕድገትና ልማት ያደረጉት የውድ ግዴታ ድጎማ በገንዘብ ቢተመን አስደንጋጭ ነው። ይታያችሁ፦ ከጥንት ግሪኮች ጀምሮ ግብፅ የአባይ ስጦታ ትባላለች። ሆኖም አባይ ደግሞ የኢትዮጵያ ስጦታ ነው። አማራጭ የለሽ ድምዳሜው ግብፅ የኢትዮጵያ ስጦታ ናት ማለት ነው! 80 በመቶ የሚሆነውን ውሃዋንና በምንም የማይተመነውን ውድ አፈር በየአመቱ የምትቀበለውና ምስጋና ቢሷ ግብፅ ኢትዮጵያን እንደ እናት ማየት ተስኗት ይባስ ብላ ስታቆረቁዛት ቆይታለች። ቀጥላለችም።

ሙሉውን ለማንበብ . . .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *