TPLF
News

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዓመቱ ከማለቁ በፊት ምርጫ እንዲደረግ ወሰነ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑ ተሰማ።

Source: BBC/amharic

ምክር ቤቱ ክልላዊ ምርጫው ይህ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት አንዲካሄድ ይወስን እንጂ ምርጫው መቼ እንደሚካሄድና በማን እንደሚከናወን አልጠቀሰም።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታረቀ ምርጫው ከጵጉሜ በፊት እንዲካሄድ መወሰኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የኮሮነቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን አገራዊ ምርጫ ማከናወን አልችልም ማለቱ ይታወሳል።

ኮሮናቫይረስን እየተከላከልን በጥንቃቄ ምርጫ እናደርጋለን፡ ዶ/ር ደብረፅዮን
በዚህም ምክንያት የሕገ መንግሥት አጣሪ የመንግሥትን የሥራ ዘመን ባማራዘም ምርጫው የሚራዘምበትን አማራጮች ካቀረበ በኋላ፤ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ የሚለው አማራጭ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።

ጉዳዩን የመረመረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድስረ ሁሉም የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች በሥራ ላይ እንዲቆዩ እና ምርጫው የበሽታው ስጋት መወገዱ ከተረጋገጠ በኋላ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ሲል ከቀናት በፊት መወሰኑ ይታወሳል።

ህወሓት ክልላዊ ምርጫ ቢያከናውን “ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም”
የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሓት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ምርጫው መካሄድ አለበት ሲል አቋሙን ሲያንጸባርቅ ነበር።

ህወሓት ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል።

ህወሓት ክልላዊ ምርጫ ቢያከናውን “ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም” ወ/ት ብርቱኳን
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚደቅሳ ህወሓት ክልላዊ ምርጫ ቢያከናውን “ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም” ብለው ነበር።

ወ/ት ብርቱኳን ይህን ያሉት ህወሓት ለቀናት ሲያደርግ የነበረውን ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው መግለጫ ላይ “መንግሥት የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ” ማለቱ ተከትሎ ነበር።

“ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ አስበው ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ አይሆንም። ሕገ-መንግሥታዊም አይሆንም” ያሉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመው እርሳቸው የሚመሩት ምርጫ ቦርድ በፌደራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰው ነበር።

ከዚህ ውጪ የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌደራል አስፈጻሚ አካል ተነስተው ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ ቢያስተላልፉ ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንምም ብለዋል።

 

የትግራይ ክልል ምርጫ፤ ስለ ዴሞክራሲ ወይስ አልሞት ባይ ተጋዳይነት? – በፍቃዱ ኃይሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *