Analysis

የተስፋየ ገብረአብ ሲንድሮም

መንግስቱ ሙሴ —

Mengistu Musie

የዘር ፖለቲካ በህወሓት እና ኦነግ የሐገራችን ህገመንግስት እና ስርአተ ፖለቲካ ሆኖ ከተጀመረበት ከ30 አመት ወዲህ ኢትዮጵያዊነት እና አማራነትን በቀጥታ ከሚደርስበት የዘረኛ ድርጅቶች የጥላቻ በትር እና ዘመቻ በተጨማሪ። በሦስተኛ መንገድ ተከታዮች የሚደርስበት የማጥላላት እና የማጥቃት በትር አንዱ ክስተት “የተስፋየ ገብረአብ ሲንድሮም” ነው።

ይህ የተስፋየ ገብረአብ ሲንድሮም ያልሁት ክስተት እንደሚታወቀው ተስፋየ ገብረአብ ድንቅ ጸሐፊ እና ቢሸፍቱ ተወልዶ ያደገ ሆኖም በኋላ ከህወሓት ጋር ተጣልቶ አገር እስከለቀቀበት ግዜ ድረስ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የነበረው በውስጡ ግን ኢትዮጵያዊነትን በእጅጉ የሚጠየፍ እና የሚጠላ የነበረ ሰው ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ወቅት መጀመሪያ የባዴን የፖእለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ የሰራ እና የሚገርመው ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላውን ያልህ አማራን አምርሮ የሚጠላ እና ኦሮሞን እንደነገድ እና ኦነግን እንደድርጅት የሚያደንቅ የሚያወድስ ሰው ነበር። በጻፋቸው መጻህፍት ሁሉ ይህን የጥላቻ እምነቱን በተለያየ መልክ ገልጾታል ለምሳሌ በክፍል አንድ በትልቅ ፊደላት እርእስ ሆኖ የቀረበው “ነፍጠኛ ወዮልችሁ የቡርቃ ዝምታ አብቅቶለታል” በሚል ይጀምር እና በየ ክፍሉ ሁሉ ግለሰብን ወይንም ትቂቶችን ሳይሆን ሕዝብን እንደሕዝብ በጥቅል የሰደበበት መጽሀፉን አስነብቧል። አንድን ትልቅ ሕዝብ ለማዋረድ የተጠቀመባቸው ቃላት ለዚህ ጸሐፊ መጽሐፉን ጨርሶ ለማንበብ ፈታኝ ሁኔታ ፈጥሮበት ነበር።

ልክ እንደተስፋየ ገብረአብ ሁሉ በአንዳንድ ድርጅቶች ውስጥ እራሳቸውን የደበቁ ግለሰቦች የፖለቲካ ልዩነትን ሸህ ግዜ በመለጠጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁነኛ ሚና የሚጫወቱ ግለሰቦችን ለማዋረድ ደገፍሁት በሚሉት የፖለቲካ አስተሳሰብ ተሸሽገው የማዋረድ እና የማጥላላት ዘመቻ ሲያደርጉ እና የሐገራችንን ችግር በጋራ እንዳንፈታ የፖለቲካ ድርጅትን ይሁነኝ ብለው ሲያጥላሉ የሚውሉ ብዙ ኔጋቲቮች የተስፋየ ገብረአብ መሰል ፍጡራን ተከስተዋል። ከገራሚ ስራወአቻቸው እነዚህ መርዝ ነስናሾች አንዱ የሁለተኛ ደረጃ እውቀት መመዘኛን ሳያልፉ ትልልቅ ምሁራንን እና ልምድ ያላቸው በብዙ ልምድ ያለፉ የፖለቲካ ሰወችን ሲያዋርዱ ማየት አስገራሚው ስራቸው ነው።

በአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስቸጋሪ በሆነው እና በሁሉም ጠባብ እና ጸረ ኢትዮጵያ ኃይላት በትኩረት የሚሰራበት አማራውን ማዋረድ ሲሆን የተስፋየ የአሁኖቹ የተስፋየ ገብረአብ ቅጅወች ከኢትዮጵያዊ የፖለቲካ እምነት ካላቸው ድርጅቶች ስም ጀርባ ተደብቀው አማራውን ማጥላላት የአማራውን እራሱን ለ፣እከላከል የጀመረውን የህልውና ትግል ማንቋሸሽ ሲሆን። እነዚህ አይነት ግለሰቦች በሬዲዮ እና ዩቲውብ ጭምር ይህን መርዛማ አላማቸውን ማሰራጨት ቀጥለውበታል። እንቃወመዋለን የሚሊት ኦነጋዊው የአብይ አህመድ መንግስትን በአፍ እና ለይምሰል ልክ ህወሓትን ለአፍ እና ለይምሰል እንደተቃወሙት ሁሉ ይቃወሙ እና የበረታ የማጥላላቱን የማዋረዱን ዘመቻቸውን ግን በዚሁ ተጠቂ ሕዝብ ሌት ተቀን ሲያወርዱ ይውላሉ።

ይህ የተስፋየ ገብረአብ የፈጠረብን (ያመጣብን ችግር ይህን ቆሻሻ ስርአት ያሰፈኑት ቡድኖች ሁሉ የሚጋሩት ሲሆን ለምሳሌ የኦነጋውያኑ ካድሬወች ፋኖን ልክ እንደ እነሱ እንደፈጠሩት ሸኔ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት በሕዝብ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ እንጅ በሄዱበት የፕሮፖጋንዳ ስፋት እና ጥልቀት ቢሆን ኖሮ እነሱ ከፈጠሩት እና በህገወጥ መልኩ የአማራ ዘርን ከወለጋ፤ ከመተከል፤ ከሰሜን ሸዋ ለማስወጣት በኦነጋዊው ፍጡራቸው የሄዱበትን ጎዳና ፋኖ ይብሳል በሚል ሊአጫወቱ ሲከጅሉ ታዝበን ግን ወግዱ ብለን አልፈነዋል።

ለማነኛውም እነዚህ የተስፋየ ገብረአብ ቅጅወቹ ያውም ደናቁርቱ ታጋዮችን በግል በማዋረድ እና በመንስደብ በማህበራዊ ሚዲያወች የሚጫወቱት ሚና እንደቀላል ማየት እንደሌለብን ለማሳሰብ እና ልክ ይህን አፍራሽ ስርአት እየተገልን ባለው መንፈስ ደናቁርት ግልገሎችን ማጋለት እና ማዋረድ የግድ እንዲል ስለሆነ ሁሉም ነቅቶ መከታተል ይኖርበታል።

በቀታይ ግን እነዚህን ደናቁርት የተስፋየ ገብረአብ ቅጅወችን ማጋለት መጀመር የሚያስፈልግ ስለሆነ አንድ የትግል ስልት ሆኖ ሊቆጠር እና ንቀን ልናልፈው የማይገባ እውነታ ነው።

 

 

 

 

 

 

Source: መንግስቱ ሙሴ facebook account

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *