Current

የማይገፋውን አትግፋ!!

Mengistu Musieበመንግስቱ ሙሴ

ድል ለተበደለው በጠባብ ኃይሎች ለዘመናት ለተጎዳው ሕዝብ ነው!!!

ጠባብ ኃይሎች እራሳቸውን ከሚወዱት በላይ አማራን ይጠላሉ

ጥቅስ የሌላ ሰው ነው

ሰባት ሚሊዮን አማራ ተፈናቅሎ መጠጊያ የለውም። ይህ ላለፉት አምስት አመታት ብቻ የተፈጸመ ግፍ ነው። አማራ መሆን እርግማን እንዲሆን ከበደኖ እስከ ቀየው መተከል አርደውታል። ወለጋን በአማራ ደም አጨቅይተዋል እስከ 2000 አማሮች በአንድ ሳምንት በወለጋ ተጨፍጭፈዋል። የሀገሪቱ መሪወች በተለይም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዜጎች ያለቁበትን ቀን የዛፍ ተከላ ውሏል።

በዚህ ያላቋረጠ የዘር ጭፍጨፋ ከወለጋ የተፈናቀለው ዜጋ ወደ ደብረብርሐን እና ባሕርዳር እንዲቀመጥ ተደርጎ ብዙወች በበሽታ በርሐብ እና በመጠለያ እጦት ተሰቃይተው አልፈዋል። ይህ ሲሆን የስርአቱ አመራሮች የአማራን ክልል እንወክላለን የሚሉትን ጨምሮ የዜጎችን መውደቂያ የጎበኘ እና ያሉበትን የችግር ልክ ለማየት የሞከረ አንድም መሪ የለም። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህ ወንጀል በእርሱ መንግስት እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል የሌለ ማስመሰሉን ቀጥሏል። በቅርቡ ተፈናቅለው ሰሜን ሸዋ የሰፈሩ የአማራ ዜጎችን እወክላለሁ የሚለው ደመቀ መኮነን የሕዝባዊ አመጽን መነሳሳት ከተኛበት የተቀሰቀሰ በሚመስል ለመጀመሪያ ግዜ አምስት ሚሊዮን ተፈናቃይን ለማየት ተጉዟል።

ስርአቱ ከበደኖ 1984 ዓም ጀምሮ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ዜጎችን በመግደል በማሰደድ አያሌ ግፍ ፈጽሟል። አብይ ምሳሊአህመድ ወደስልጣን ሲመጣ በነቂስ ወጥቶ እና እጁን ዘርግቶ የተቀበለውን ይህን ሕዝብ ዘግናኝ እና ስልታዊ በሆነ የዘር ማጽዳት የበለጠ የበቀል ዘመቻ በመጠመድ እስከ ዛሬ ይህን ሕዝብ ማፈናቀል፤ መግደል አይፈጽሙ ወንጀል አካሂዷል።

የአብይ አህመድ ካድሬወች እና ኦነጋውያኑ በጠቅላላ የአማራ ሕዝብ መገደል ተገቢ መሆኑን በየአገኙት መድረክ ገልጸዋል። ሽመልስ አብዲሳ “የሰበሩንን፤ ሰብረናቸዋል” “አባይን ተሻግረን የሚያምነውን በሰላም፤ ያላመነውን በኃይል” እየሰበርነው ነው ብሏል። ከጃዋር አህመድ በቀለ ገርባ እከ ቅርብ አመታት ኦነግን እቃወማለሁ እስከሚለው መረራ ጉዲና የዚህን ሕዝብ እልቂት ተገቢነቱን አስረግጠው ሲነግሩን የበለጠ እንዲሆንም ሲቀሰቅሱ ኖረዋል።

አብይ አህመድ እና የህወሓት መሪወች በፈጠሩት የስልጣን ግብ ግብ ጦርነት ባለፉት ሁለት አመታት የሁለቱን ጠባብ ቡድኖች ውጊያ ያካሄዱት በአማራ መሬት ነበር። የህወሓት መሪወች ከጌታቸው እረዳ እስከ ትንንሽ ውርጋጥ የህወሓት ካድሬወች በግልጽ ይህን ሕዝብ ማጥፋት ዋና አላማቸው መሆኑን በየአገኙት አደባባይ አሳይተዋል ተናግረዋል። በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝባችን በትግራይ እና በአማራ መሬት የአፋርን ሕዝብ ጨምሮ በሁለቱ ለከት ያጣ የጥላቻ ጦርነት አልቋል። ያም ሆኖ የጥላቻቸው አራራ እስካሁን አልወጣላቸውም። አንድ የፌስቡክ ጓደኛየ እንዳለው ሁለቱ ጠባብ ኃይሎች እራሳቸውን ከሚወዱት በላይ እና በእጥፍ አማራን ይጠላሉ። ዛሬ የምናየው በአማራ ሕዝብ ውስጥ ያለው እራስን የመከላከል መነሳሳት ከብዙ ግፍ እና ከብዙ ኢፍትሐዊነት ካስከተለው የተጠራቀመ በደል የተወለደ ፍትሐዊ ትግል ነው።

መፍትሔው

ሁልግዜ በታሪክ እንዳየነው በትምህርት እንደተማርነው በደል የወለዳቸው የዝብ ጥያቄወች በአፈሙዝ ብቻ እንደማይመለሱ እሩቅ ሳንሄድ ከራሳችን ሐገር ታሪክ ልንማር ይገባል። ለምሳሌ እራስ አበበ አረጋይ እና ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የቀዳማይ ወያኔን ጥያቄ በወታደራዊ የጦርሜዳ ፈትተው የጥያቄው አንሽወችን በማስወገድ ባይደመድሙ እና መሰረታዊ ፖለቲካዊ እና ችግሩን ከስር በሰላማዊ ቢቋጩት ህወሓት የተባለች ጸረ ኢትዮጵያ/ጸረ አማራ ድርጅት ባልተፈጠረች እና የሐገራችንን አንድነት በዚህ ደረጃ ባላደረሰች ነበር።

1- ገዥው የኦሮሞ ብልጽግና የኦሮሞ ሕዝብን አይወክልም እናም እንደመፍትሄ እልቂትን ልክ እንዳለፉት አምስት አመታት ከተጠቀመ። ሐገር መፍረስ ብቻ አይደለም የኦሮሞ ሕዝባችን የመሐል ሐገር እንደመሆኑ መጠን ከባዱ ጉዳትን እወክለዋለሁ በሚለው ሕዝብ ያደርሳል። ይህን ለማስቀረትም ሆነ በታሪክ ሌላ ተጠያቂነትን ለማስወገድ

2- የችግራችን ምንጭ በህወሓት ኦነግ የፖለቲካ ፕሮግራም የተሰራው ህገመንግስት ስለሆነ ሕገመንግስትን ማስወገድ

3- ለእርቅ መቀመጥ ብቻውን ልትምምን በቂ አይደለም። ሕዝብ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል እናም የኦሮሞ ብልጽግና እራሱም የሚወከልበት ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስትን የመፍትሄው አካል ማድረግ

4- የሽግግር መንግስት በተከትታይ መንግስታት የተፈጸሙ በደሎችን ፍትሐዊ ድምዳሜ ያገኙ ዘንድ የእርቅ እና የሰላም ኮሚሽንን የኮሚሽኑ ሊፈጽማቸው የሚገቡ መርሆችን በስራ እንዲውም የሚመለከታቸው የሐገሪቱ ምሁራንን ከሁሉም አካባቢ መርጦ ወደስራ ማሰማራት። ዲሞክራሲያዊ የሆነ ይህን ስርአት ያልተከተለ የአንድ ሰው አንድ ቮት ምርጫ አካሂዶ ቦታውን ለተመረጠ መንግስት መልቀቅ ናቸው።

የአማራ ፋኖ

@ – የሚካሂደው ትግል ፍትሐዊነትን ለማስፈን እንደሆነ ሁሉ ይህን ትግል የደገፈው ሕዝብ ፋኖ የሚልን ስም በመውደድ ብቻ ሳይሆን ለነፃነት የተነሳሳ የመስዋ’እትነት ገድል መሆኑን ስለተገነዘበ ነው። የምናውቀው ፋኖ ከነበላይ ዘለቀ እስከ ኢሕአሰ (የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሰራዊት) ሕዝብን አገልጋይ በሕዝብ ታማኝ ስለሕዝብ የቆመ እንዲሆን ተራ ወንበዴወችን ልክ እንደስርአቱ አሳዶ ማስወገድ

@ – የሚመራበት መርህ እና ዲስፕሊን ለታጋዩ ማሳየት

@ – የራሱን የተበታተኑ እዞች ወደአንድ በአስቸኳይ ማምጣት እና መሐከላዊ አመራር መስጠት። መሪወቹን በተከታዮች ማስመረጥ

@ – በህወሓት እንዳየነው የሐገሪቱን ሰራዊት ለማፍረስ ሳይሆን የሰራዊቱ አካል ለመሆን መሆኑን ማሳየት። በእጁ የሚወድቁ የተቃራኒ ጎራ ሰወችን በፍጹም ኢትዮጵያዊነት መቀበል እና ተገቢውን ለዜጋ የሚደረግን ሁሉ ማድረግ። ዘረኝነትን እንዲያወግዙ በማስገደድ ሳይሆን በማስተማር ማድረግ።

የአብይ አህመድ የኦነጋዊ መንግስት የሰራቸውን ስራወቹን አውግዞ ሐገርን ለመታደግ ከጦርነት ይልቅ ሰላማዊ መፍትሄ አማራጭ የሌለው ብቸኛ መውጫ መሆኑ ከብዙ ይየግራቀኝ ወንድማማች/እህትማማች ሕዝባችን ጉዳት በፊት ለውሳኔ ቢደርስ በታሪክም የቀለለ ተጠያቂነት እንዲኖርበት ያደርጋል።

ድል ለፋኖ!!!

Source: Mengistu Musie facebook account

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *