News Press Release

የኢሕአፓ መግለጫ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በተፈጸመ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ላይ

“ያሳምራል ያሉት ኩል ዓይን አጠፋ”
(በምዕራብ ወለጋ በአማሮች ላይ የተካሄደውን ጭፍጨፋ በጥብቅ እናወግዛለን!)

ጥቅምት ፳፫ ቀን ፪ ሺህ ፲፫ ዓ. ም

ምነ ው እንደዚህ ከሰብአዊነት ተራ ወጣን? እስከመቼስ ይህ ዓይነ ቱ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸማል? ኢትዮጵያስ እስከመቼ የደም መሬት ሆና ትቀጥላለች? እኛስ እስከመቼ የ ሀዘን መግለጫ እያወጣን እንዘልቃለን?

በምእራብ ወለጋ የተከሰተው የሰሞኑ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሕይወታቸውን ለነጠቃቸው ኢትዮጵያውያን የአማራ ተወላጆች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን በአገ ቸው ላይ በተለያዩ አካባቢዎች ግፍ እየደረሰባቸው ካሉ የአማራ ተወላጆች ጎን ሁሉም የኢሕአፓ አባላት እንደምንቆም በአንክሮ እንገልጻለን፡ ፡

ፓርቲያችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሰሞኑን በአማራ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አስከፊ ጭፍጨፋ እጅግ ያሳዘነ ውና ያስቆጣው መሆኑን በመራር ሁኔ ታ ይገልጻል። ኢሕአፓ በጭፍጨፋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናቱን ይመኛል።

 

ወደ ሙሉ መግለጫው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *