Analysis

የነታደሰ ወረደ የጅል ጥሪ ወይስ የፋሽስቷ ህወሓት እና መሪወቿ የድረሱልን ሲቃ

የነታደሰ ወረደ የጅል ጥሪ ወይስ
የፋሽስቷ ህወሓት እና መሪወቿ የድረሱልን ሲቃ
==============================

Mengistu Musieየታደሰ ወረደን መለክት ሰማሁ እና ፈገግ አልሁ። መልእክቱ ሁለት ገጽ አለው በአንዱ ገጽ የህወሓቷን ጭንቀት እና ጥበት ያሳያል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በሌላው ገጽ የአልሞት ባይ ተጋዳይ አንዲስ የጅል ጥሪን ያመላክት እና አሁንም ኃይል አለን እንዲህ ስንጠይቃችሁ የፈራናችሁ እንዳይመስልብን ለማለት ይዳዳዋል።

ለማነኛውም ህወሓት ከፍጥረቷ እስከ ዛሬዋ የጣእር ዘመኗ ያላወቀችው ነገር ከሷ የበለጡ አዋቂወች መኖራቸውን እና ትምህርት መውሰድ ብትፈልግ ኖሮ ዛሬን ያራምድ የነበር ልታገኝ የሚያስችላት ሊሰጧት የሚችሉትን አለማዳመጧ ነው። እናም ታደሰ ወረደ የተባለው ቱባ ወያኔ “የአማራ ፋኖን ላንማርክ እና ላንገል ወስነናል” የሚል መልእክት አስተላለፈ። እኔ እራሴ ደነገጥሁ አበባሉ እና ለመናገር የሄደበት ድፍረት ምን ጭንቅ ላይ ቢወድቅ ይሆን በሚል። ህወሓት የካቲት 1967 ደደቢት ስትገባ መርህ ብላ ያሰፈረችው 1ኛ ጠላት አማራ 2ኛ ኢትዮጵያ የምትባል ተረት ተረት የመቶ አመት ኢምፓየር በሚል ነበር።

ጌታቸው እረዳ የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ እዲወጣ ከታዘዘ በኋላ ከሰሜን ወሎ እና የአፋር ምድርን ሲረግጡ የነገረን “ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሴኦል ድረስ እንገባለን” ሲል በዚያው አዋጁ “ይህ ዘመቻችን በአማራ ላይ ሒሳብ የማወራረድ ዘመቻ ነው” ነበር።

ሌላው ሰሞኑን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በላካቸው አባሳንጆ አስታራቂነት ተጀምሮ የነበረው ድርድር የፈረሰው ሙሉውን ባንሰማም ከፊሉ የህወሓት ቅድመ ሁኔታ ህወሓት 1971 ዓም ከኢሕአፓ እና ከወልቃይት አርበኞች ጋር ተዋግታ የያዘችው የወልቃይት መሬትን “ለድርድር እንደማይቀርብ እና ቀድሞ ይሰጠኝ” በተጨማሪ ራያም ይገባኛል እና ከድርድሩ በፊት ይሰጥ በሚል ነበር። ሌላው ህወሓት እስካሁን ያካሄደችው ጦርነት በአማራ እና አፋር መሬት ላይ ነው። የገደለችው፤ ያፈናቀለችው፣ የዘረፈችው እና ለዘመናት የተገነቡ የጤና – የትምህርት፤ የኢኮኖሚ እና ኢንዱስትሪ ተቋማት ያፈረሰችው ሁሉ የአማራ እና የአፋር ነው።

በአጋጣሚ ባለፈው በዳላስ ከተማ ፋኖን ለማገዝ ተጠርቶ በነበረ ስብሰባ አሜሪካዊው ጄማል የተባለው ወንድማችን “Tears of Wollega” በሚል ያነሳቸው ፎቶወች በግል ከዚህ እጅግ አስገራሚ ሰው ጋር ቁጭ ብየ በጦርነቱ ከጦርነቱ በፊት እና ከጦርነቱ በኋላ ያነሳቸውን የወሎ እስከ ሰሜን ሸዋ አይቻለሁ የሚዘገንን የሚያሳዝን አንድ ሕዝብ አብሮት የኖረውን ለሽህ አመታት ከጉርብትና ባለፈ ተዋልዶ የኖረን ሕዝብ ላይ በህወሓት የተፈጸመው በደል ይቅር የማይባል ቢባልም እጅግ ብዙ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ማየት ችያለሁ። ያነን እንዲሆን ትእዛዝ የሰጠ በጥፋቱ የቀጥታ ተሳታፊ ታደሰ ወረደ በሚዲያቸው ወጥቶ የተናገረው ድፍረትም በሉት ጭንቀት ያሳዝናል በድጋሚ ያናድዳል። እንላለን እኛ ህወሓትን የምናውቅ “ህወሓትን ማመን ቀብሮ ነው!” ይህ የትግራይን ሕዝብ ማዳንም የሚቻለው ይህችን ደመኛ ድርጅት በማስወገድ ብቻ ነው። በተረፈ የገበጣ ጨዋታውን ትቶ መስዋ’እትነት እየከፈለ ያለው ሰራዊት ከአጋሮቹ ጋር አበረታቶ ለአንዴም እስከወዲያኛው ህወሓት ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ካልተወገደች እድገት፣ ብልጽግና እና ሰላም የሚታሰብ አይደለም። የትግራይ እና የአጎራባች የአፋር እና አማራ ሕዝብን ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው ይህችን ጸረ ሰላም ምንደኛ ድርጅት በማስወገድ ብቻ ነው። Adios!!

Source: Mengistu Musie facebook

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *