Dr. Zenebu Haile
News

የክብርት ዶክተር ዘነቡ ኃይሉ ኢትዮጵያዊቷ የስደተኞች ተንከባካቢ በሀደርስፊልድ

አውሮጳ/ጀርመን

የክብርት ዶክተር ዘነቡ ኃይሉ ኢትዮጵያዊቷ የስደተኞች ተንከባካቢ በሀደርስፊልድ

Dr. Zenebu Haile

በተሰደዱባት በብሪታንያ ለስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች ባደረጉት እገዛ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የበቁ ኢትዮጵያዊት ናቸው ወይዘሮ ዘነቡ ኃይሉ ። የወይዘሮ ዘነቡ ታሪክ ከተወለዱባትና ካደጉባት ከአላማጣ እስከ ብሪታንያዋ ትንሽ ከተማ ሀደርስፊልድ ይዘልቃል። አስተዋጽኦቸው የሚጀምረው በትውልድ አካባቢያቸው በአላማጣ በድጎማ መምህርትነትና በርዕሰ መምህርነት ከሰሩበት ጊዜ አንስቶ ነው። ከዚያም ለሰባት ዓመት በቆዩባት በሩስያ በላይብረሪና  ኢንፎርሜሽን ሳይንስ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ በጎርጎሮሳዊው 1991 የዛሬ 32 ዓመት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ ተቋም እንዲሰሩ ተመደቡ በቤተ መጽህፍቱ የነበሩት መጻህፍት በሩስያኛ የተጻፉ  ስለነበሩ፣ሌሎች መጻህፍትን ለማሰባሰብና ከታዋቂ ግለሰቦች ፣በሀገር ውስጥ ካሉ ኤምባሲዎችና ቤተ መጻህፍት እንዲሁም በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች እገዛ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ጀምረው መጻህፍት ለማሰባሰብ በቁ ።

ስለ ዶ/ር ዘነቡ የቀረበውን ሙሉ ዜናውን ለማንበብና የራድዮ ዝግጁቱንም ለመከታተል

 

Honorary doctorates for July 2023 announced

ምንጭ፥  DW.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *