Analysis Opinion

የቺሌ ዴሞክራሲ መጨንገፍ – የፋሽዝም መነሳት – የሳልቫዶራ አየንዴ አወዳደቅ

November 8, 2021

 Mengistu Musie  Mengistu Musie

===================

በ CNN ያየሁትን ማመን አቃተኝ ነገሩ አልተሰራም አዲስ ነው ወይም አይሰራም ብየ አይደለም። የሽግግር መንግስት ባዮቹ ጉግማንጉግ ግለሰቦች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ኖረው የማያውቁ ለዘመናት በታገልሁበት ሁሉ ሰምቻቸው አይቻቸው የማላውቃቸው መሆኑ ነው። ስለዴሞክራሲ ለ40 ምናምን አመታት ከታገሉ የኢሕአፓ ታጋዮች ጋር የኖርሁ ስለሆነ ነው። እነዚህ ያየኋቸው ግለሰቦች ግን ስም የሌላቸው ምናልባትም በዩኤስ አሜሪካ እና በህወሓት የዳቦ ስም ወጦላቸው ሐገር ለማደናገር ለመሸጥ፣ ለመከፋፈል የተቀጠሩ ጉግ ማንጉጎች ብሎም ደናቁርት በመሆናቸውም ነው። አፍ ሲከፈት ትናጋ ይታያል ይባላል። እናም ይህን የአሜሪካኖች ትያትር መሰል ነነገር በዚህ ዘመን አያለሁ ብየ አስቤ ስለማላውቅ ይሆናል ያስደመመኝ።

የዛሬውን ነገራቸውን ካየሁ በኋላ አንድ መጽሀፍ እስር ቤት እያለሁ ካገላበጥኋቸው ያች ትንሽ ኩራዝ አሳታሚ የተረጎማት የችሌ እና የሳልቫዶራ አየንዴ ታሪክ ብልጭ አለብኝ። ያ ብቻ አይደለም አፍሪክ እጅግ ውብ የተባሉ ታላላቅ መሪወቿን በአሜሪካ እና በእንግሊዝ ደህንነቶች በአጭር እየተቀጩ እንዲያልፉ ሆነዋል የጋናው ንክሩማህ-የዛየሩ ፓትሪክ ሉሙምባን እና አያሌ ተራማጅ ሰማ’እታት መሪወችን ያስታውሷል። እናም በነዚያ ድንቅ መሪወች ምትኮቻቸው ሰው በላ የሆኑ እንደ ሞቡቱ ሴሴኮ ያሉ መሪወች ተቀምጠውበት ሐገሮቻቸውን ገድለው እና ሕዝባቸው ለማኝ አድርገው አልፈዋል።

የችሌ የሳልቫዶራ አየንዴ አሟሟት የታወሰኝ እንዲህ ነው። አየንዴ የተወለደው ደቡባዊት አሜሪካ ከሆነችው ችሌ ከተባለችው ሐገር 1908 ነበር። የተወለደበት ቤትም ከመልካም ኑሮ ካላቸው ቤተሰብ ሲሆን እንደማንኛውም ቺሌአዊ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ በተገቢው ሰአት ገብቶ በጥሩ እድሜ የዶክተሬት ዲግሪውን ወሰደ። በስራ መስክም ዶክተር ሆኖ እየሰራ ግማሽ የስራ ግዜ ሰጥቶ የማርክሳዊ እርዮት የችሌ ወጣቶችን ያስተምር ነበር። ለተበደሉ፣ ለተገፉ ሁሉ ቋሚ ጠበቃ በመሆን ኑሮው ከሆስፒታል ወደ ድሆች ወደሚኖሩበት መሄድ እና ታሪክ እና ኑሮአቸው መካፈል ሆነ።

በዚህ እንዳለ 1933 እ ኤ አ የችሌን ሶሻሊስት ፓርቲ መሰረተ። የህብረተሰቡን ኑሮ ሊለውጥ የሚችለው የስርአት ለውጥ ሲኖር ብቻ እንጅ ካፒታሊዝም አይን አፍጥቶ ድንበርም እየተሻገረ የድሀ ኑሮን የሚቀማበት ዘመን በመሆኑ ነው።የአየንዴ መፍትሄ አድርጎ የወሰደው ሰራተኛው የላቡን ትክክለኛ ዋጋ ሊያስገኝበት የሚችል ድርጅት መመስረት እና የካፒታልን ስርአት መጣል በመሆኑ ነው።

በ1937 እሱና ጓደኞቹ ባቋቋሙት የችሌ ሶሻሊስት ፓርቲ የ Chamber of Deputies ሆኖ ተመረጠ። በቀጣይ አመታትም የሶሻሊስት ፓርቲ አባሉ ፔድሮ ሴድራ ስልጣን ሲይዝ በካቢኔው የጤና ሚኒስቴር ሆኖ አገልግሏል። በቀጣይ አመታት በ 1950 ወቹ እና 1960 ወቹ ለፕሬዚዳንትነት እየተወዳደረ ሳይሳካለት ቆይቶ። በመጨረሻ በሴብቴምበር 1970 ሶስት ተወዳዳሪ በነበረው የፕሬዚዳንት ውድድር 36% ቁጥር በማግኘት ከሁለቱ ተወዳዳሪወቹ በልጦ ስልጣን ያዘ። 50 ፕርሰንት የመራጭ ቁጥር ባለማግኘቱ የአየንዴ መመረጥ ውሳኔ ወደ ችሌ ምክርቤት ሄዶ በብዙ ክርክር ጸድቋል።

የአየንዴ እና የችሌ የግራ እንቅስቃሴ መሪወች ጥምር ወደስልጣን ከመጣ ማግስት በሰሜን አሜሪካ ድንጋጤ ተከሰተ። ሪቻርድ ኒክሰን ፈጽሞ ችሌ ከአሜሪካን ምህዋር መውጣት የለባትም በማለት ዘመኑ የቀዝቃዛው አለም ጦርነት በመሆኑ ኒክሰን የአየንዴን ስልጣን ይዞ እንዳይቀጥል በነጩ ቤተመንግስት የአሚሪካ ደህንነት መስሪያቢቤት ሹም ሪቻርድ ሄልም ጠርቶ አንድ ነገር እንዲደረግ አየንዴ ላይ ተወሰነ። ሚሽኑን የተቀበለው የደህንነት መስሪያቤቱ ዳይሬክተር ሄልምስ አየንዴ በማነኛውም መልክ ስልጣን ይዞ መቆየት የለበትም የሚለው የነጩ ቤተመንግስት ውሳኔን ተግባራዊ ለማድረግ ስራ ተጀመረ። እየንዴ ከምርጫው በፊት ለችሌ ሕዝብ የአሜሪካ ፋብሪካወች ተወርሰው ለሕዝብ እንደሚሆኑ ቃል ገብቷል።

በችሌ የሶሻሊስቱ ካምፕ በጠቅላላ እና ሶሻል ዴሞክራቶች በተለየ ለአየንዴ ሙሉ ድጋፍ ቢቸረውም። የችሌ ሕዝብ አየንዴን ብርቅ ድንቅ አርጎ የሚያየው ተወዳጅ መሪ ቢሆንም ጥቅሟ የተነካው አሜሪካ ፈጽሞ ስልጣን ላይ እንዳይቆይ ስለወሰነች በማነኛውም ሰአት እና ግዜ ለማስወገድ ስራ ተጀምሯል። ሌላው በደቡባዊ አሜሪካ ከፊደል ካስትሮ እና ከቸ ጎቬራ የተሳካ የስርአት ለውጥ በኋላ ሌላ ተመሳሳይ መንግስት ስልጣን ላይ እንዳይወጣ የአሜሪካ ፖሊሲ ነበር በመሆኑም የአየንዴ ቀናት መቆጠር ጀምረዋል።

አየንዴን ለማጥፋት የነጩ ቤተመንግስት የግዜው ፕሬዜዳንት ኒክሰን 10 ሚሊዮን ለኦፕሬሽኑ መፈጸሚያ አዝዘው ደህንነቱ ስራውን ጀምሯል። አስገራሚው ደግሞ ሳንቲያጎ ያሉት የአሜሪካ አምባሳደር እዳያውቁ መደረጉ ነበር። ደህንነቱ የመጀመሪያ ሙከራው የአየንዴን ስም ማጠልሸት እና በኮንግረሱ እንዲወረወር መስራት ነበር። በአለማቀፍ የአሜሪካ ደህንነት ዘመቻ አየንዴን የማጠልሸቱን ፕሮፖጋንዳ ተያያዙት። ብዙ ችሌአውያን አሳዘናቸው ግን ሊሰማ የሚችል የለም። ቀጥሎ ወግ አጥባቂ ለነበረው የቺሌ የጦር ኃይሎች አዛዥ ለጄኔራል ሬኔ ሸንደር ጉዳዩ ተገልጾ መፈንቅለ መንግስት እንዲያደርጉ ቢጠየቁ ይህ ሐገር መክዳት በእኔ ፈጽሞ አይሞከርም በማለት ጀኔራሉ አሜሪካንን አስደንግጠው መለሱ። በኋላ የአሜሪካ ደህንነት እንቅፋት መሆናቸው ስለተገነዘበ ጄነራል ሬኔን በ ጀኒራል ሮቤርቶ በተባለ ቅጥረኛ አስገደሉ። ከሀዲው ጄኔራም ስለፈጸመው የሀገር ክህደት በአሜሪካ ደህንነት $35000 ዶላር በወሩ ተሸለመ።

የችሌ ኮንግረስ አየንዴን ፕሬዚዳንት ብሎ ሊሰይም አንድ ሳምንት ብቻ ሲቀረው። ሰአታት የቀደሙት የአሜሪካ ደህንነት ወደ ሳንዲያጎ ቢሮአቸው ኬብል አድርገው በየትኛም ሰአት በአጭር ቀናት ከምክርቤቱ ስብሰባ በፊት አየንዴ አንድ ነገር መደረግ እንዳለበት ቀጭን ትእዛዝ ተላለፈ። ሆኖም ቀኑም ደርሶ ያውም ወግ አጥባቂው ምክርቤት የአየንዴን ፕሪዜዳንትነት በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። በኦክቶበር 24 ፕሬዚዳንት አየንዴ በሁሉም ቻምበር ተቀባይ ሆኖ ወደስልጣን ሄደ። ሆኖም የዴሞክራሲ ቀንዲል ነኝ የምትለው አሜሪካ ከልክ ያለፈ መሸበር ውስጥ ገባች። ወጣም ወረደም አየንዴ ምንም ሳይደረግ ቀረ አንዱ እና ዋነኛው ለአሜሪካ ደህንነት ችግር የነበረው አየንዴ ተወዳጅነቱ ከአይዲዮሎጅ በማለፉ ወግ አጥባቂወች እና የካፒታሊዝም ስርአት ደጋፊ የሆኑ የወታደሩ መሪወች ዙሪያውን በመክበብ አቅፈው እና ደግፈው ስለያዙትም ነበር። አየንዴም ከአላማ ጽናት እና መርህ ጋር ለሦስት ታላላቅ አመታት ለችሌ ሕዝብ ሰራ። ታላላቅ ለውጦችም አመጣ።

ከምንም በላይ አየንዴ የሶሻሊዝምን ሰብአዊነት በበሰለ ተግባራዊ ስራው አሳየ። ህግ እና ደብ ተከበሩ። ሰው ያለፍርድቤት ትእዛዝ መታሰር መንገላታትቱ እንዲቆም ሆነ። የላባደሩ አንባ ገነንነት የሚለውን ሌሊናዊ ጽንፍ ትቶ ዴሞክራሲያዊ ሶሻሊዝምንም አስተማረ በተግባር አሳየ። ይህ ይሳሳትልናል ብሎ ለሚጠባበቀው የአሜሪካው መንግስት የበለጠ አስደንጋጭም ነበር። ወታደሩ እና ብዙ ጀኔራሎቹም የችሌ ሕዝብ ያላየውን መብት፣ እኩልነት፣ ነጻነት እና ሰብአዊነት መከበር ስለአየ የአየንዴ ተወዳጅነት ጣራ ነካ።

የነጩ ቤተመንግስት ሁሉንም ሙከራወች ጀመረ እናም ለተቃዋሚ ድርጅቶች 8 ሚሊዮን ዶላር መድቦ ሳቦታጅ እንዲጀመር አደረገ። ተቃዋሚ ነን ያሉ ድርጅት መሪወች ሌት ከቀን አየንዴን ሰይጣን አርገው ማቅረቡን ተያያዙት ገንዘብ እንደመና ከዋሽንግተን ይፈስላቸውም ጀመር። ሳቦታጁ ውስጥ አንዳንድ ነጋዴወችም ገቡበት እናም ኢኮኖሚው አሽቆለቆለ። ገበያ ናረ፣ እቃወች ከገበያ መጥፋት ጀመ፥ በእርግጥም ሕዝብ እንዲማረር መደረጉ ትንሽም ቢሆን መሬት እረገጠ። ይህ አጋጣሚ በአየንዴ መንግስት ላይ ከተራ ደሀ ህዝቡ አልፎ አለማቀፍ ተቋማት ሁሉ ተጻራሪ ሆነው እንዲቆሙ ያደረገ ክፉ ስራ ነበር።

እንደሚታወቀው አየንዴ ስልጣን በያዘ በአመቱ ብዙ የአሜሪካ እና የሌሎች የአውሮፓ በዝባዥ ኢንዱስትሪወች ተወርሰው ነበር። እሱም ለሕዝብ የገባውን ቃሉን አሟልቶ ነበር እናም ይህን ግዜ ተቃውሞው እና ጸረ አየንዴ ፕሮፖጋንዳው ከሁሉም አቅጣጫ ቢሆን የሚጠበቅ ሆነ። እናም በ1973 መጀመሪያ ላይ የችሌ ኢኮኖሚ አፈር ከድሜ ገባ።፡ሻጥረኞችም ስለሚከፈላቸው እቃወችን ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ በማበላሸት ገበያውን አጸዱት። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የችሌ የሰራተኛ መደብ እና የችሌ አርሶአደር ከጎኑ አልተለዩም።

በሴፕቴምበር 11/1973 ከዋሽንግተን ስራው ተሰርቶ ስለአለቀ አየንዴን የማስወገድ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ትእዛዝ ተላለፈ እናም ሳትያጎ ከተማ ቀውጢ መሆን ጀመረች። ሶስት ክፍለጦሮች ወረሯት ሆኖም የአየንዴ የክብር ዘብ እና ካቢኔው ከሱጋር ለማለፍ ውጊያውን አጦፉት። በ 11 ሰአት ጠዋት በዚያች ክፉ ቀን ቤተመንግስቱ በታንክ ተከበበ የክብር ዘቡም ብዙወች ወደቁ። አየንዴ የኮሚኒስት ፓርቲውን ሬዲዮ በመጠቀም ሕዝቡን መቀስቀስም ስንብትም አደረገ።

ለቺሌ ሕዝብ ሲል ግንባሩን ያላጠፈው አየንዴ እስከ መጨረሻ የመጣውን የጨቋኝ አለማቀፍ ኢምፔሪያሊዝም በድፍረት እንደሚቀበል አረጋገጠ። ከእኩለ ቀን በፊትም ሁለት ተዋጊ ጀቶች ሳንዲያጎን ቀልብ ነስተው በቤተመንግስትቱ አንዣበው አለፉ። አከታትለውም እና እየተመላለሱ ሚሳየሎችን ወደቤተመንግስቱ ላኩ። ለ20 ደቂቃ በተከታታይ ደበደቡ። ቤተመንግስቱ ነደደ ሆኖም ያሰቡት ሳይሆን አየንዴ ከጥቃቱ ድኖ ነበር።

የችሌ ፍጅት ——ይቀጥላል

 

Souce: https://www.facebook.com/mengistu.musie

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *