ዓለም-አቀፍ-የጠለምት-አማራ
Press Release

በተነኮሱን ቁጥር እየተጣመርንና እየጠነከርን እንሄዳለን !!

ሚያዚያ 162016 /

ትህነግ በወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራየ አማራ ላይ የፈጸመዉ ግፍና መከራ ያንገሽገሸው ማህበረ ሰብ ራሱን ነፃ ለማውጣትና ህልውናዉን ለማስከበር ባደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶና አዋርዶ ወደመጣበት እንዲመለስ ከአደረገ በኋላ ላለፉት ሦስት ዓመታት ቀጠናዉን ሰላም በማስፈን ነፃነቱን ሲያጣጥም ቆይቷል።

ጦርነትን እንደቋሚ መርህ የሚመለከተውንና ካለጦርነት እስትንፋስ የማይኖረዉን በጥቂት ግለሰቦች የሚዘውር ድርጅት ዕድሜና ስልጣን ለማራዘም ሲባል በአማራ ሕዝብ ላይ ለአራተኛ ጊዜ ራያና ቆቦ ወረራ ማካሄዱንና ጠለምትና ወልቃይትን ለመውረር በክፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን አገር አቀፍና አለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ነው።

ራያ በትህነግ ግምባር ቀደምትነትና በአብይ መከለከያ ድጋፍ ስጪነት ከተወረረበት ጊዜ ጀምሮ በሕዝበና በንብረት ላይ ይህ ነው የማይባል ግፍና መከራ እየተፈፀመ ይገኛል።

የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴዎች በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለዉን ከልክ ያለፈ ግፍና መከራ ለዓለም ህብረተሰብ እያስታወቁ ቢሆኑም የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዘብው ትኩረት ስጥተው ሲዘግቡ ግን አይታዩም።

እኛ በውጭ አገር የምንገኝ የጠለምትአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ የትህነግን ወረራና ተስፋፊነት በጥብቅ የምናወግዝ መሆናችንንና አገር ቤት ካለው የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ጎን የምንቆምና ማነኛውንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኞች መሆናችንንና ታሪካዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ለመግለፅ እንወዳለን።

ድል ለአማራ ሕዝብ

telemtamara@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *